የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ማሳሰቢያ፦ የመንግሥት አገልግሎታችን የአውራጃ ስብሰባ በሚደረግባቸው ወራት የእያንዳንዱን ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ጉባኤዎች “አምላካዊ ታዛዥነት” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ በሚገኙበት ሳምንት የሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም እንዳያመልጣቸው እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ። የሚቻል ከሆነ ከአውራጃ ስብሰባው በፊት ባለው ሳምንት በምታደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ 15 ደቂቃ ወስዳችሁ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 እና 4 ላይ ከወጡት ምክሮችና ማሳሳቢያዎች መካከል ለጉባኤው ያስፈልጋሉ የምትሏቸውን ከልሱ። ከስብሰባው አንድ ወይም ሁለት ወር በኋላ በአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ (ምናልባትም ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል ሊሆን ይችላል) ወስዳችሁ አስፋፊዎች ለአገልግሎት የሚጠቅም ምን ነገር እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ በማድረግ የአውራጃ ስብሰባውን ጎላ ያሉ ነጥቦች ከልሱ። በዚህ የክለሳ ውይይት ላይ ጥሩ ተሳትፎ ለማድረግ ሁላችንም በመስክ አገልግሎት ላይ ልንሠራባቸው የምንፈልጋቸውን ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦች በማስታወሻ መያዝ ይገባናል። ይህ ልዩ የአገልግሎት ስብሰባ ክፍል በስብሰባው ላይ የተማርነውን እንዴት እየሠራንበት እንዳለ ለማብራራት አጋጣሚ ከመስጠቱም በተጨማሪ አገልግሎታችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን እንዴት እንደረዳን ሐሳብ ለመስጠትም ያስችላል። አንዳንዶች ስብሰባው ላይ የተሰጠውን ትምህርት በደንብ እንደተጠቀሙበት መስማት የሚገነባ ከመሆኑም በላይ ሌሎች በስብሰባው ፕሮግራም ላይ የተሰጡትን ምክሮችና ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርጉም ያበረታታል።
ነሐሴ 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 (85)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ:- “የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶችን ትጠቀማላችሁ?” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች የመጋበዣ ወረቀት በመጠቀም ያገኙት ጥሩ ውጤት ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ አስፋፊ ፍላጎት ያሳየን ሰው የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ተጠቅሞ ወደ ጉባኤ እንዲመጣ ሲጋብዘው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
25 ደቂቃ:- “ለመስበክ ጊዜው አሁን ነው!” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የዘወትር አቅኚ ለመሆን ሲሉ ያደረጓቸውን ማስተካከያዎችና በውጤቱም ያገኟቸውን በረከቶች እንዲናገሩ አንድ ወይም ሁለት የዘወትር አቅኚዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ) የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ታስታውሳለህ? በሚያዝያ 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 30 ላይ ተመስርቶ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በእያንዳንዱ ጥያቄ ላይ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። የትምህርቱን ተግባራዊ ጠቀሜታ አጉላ። ሁሉም እያንዳንዱን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! እትም በትኩረት እንዲያነቡ አበረታታ።
20 ደቂቃ:- “ሰዎችን በራቸው ላይ እንደቆምን አሊያም በስልክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በመጀመሪያው ቀን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር አንድ ወይም ሁለት አንቀጽ ብቻ በመጠቀም እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 94 (212)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።
20 ደቂቃ:- “በታላቅ ጉባኤ መካከል ይሖዋን አመስግኑ።” በጉባኤው ጸሐፊ የሚቀርብ። ጉባኤው የተመደበበትን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ተናገር። ተራ ቁጥር የተሰጣቸውን አንቀጾች መጠበቂያ ግንብ በሚጠናበት መልክ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአንቀጽ 3-7 ያለውን አንድ ሰው እንዲያነብልህ አድርግ።
17 ደቂቃ:- “የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ ውድ መብት ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ አራትን ስትወያዩ በጤና እክል አሊያም በዕድሜ መግፋት ምክንያት ብዙ ማገልገል ለማይችሉ አስፋፊዎች የ15 ደቂቃ ድምሮችን ሪፖርት ማድረግ እንዲችሉ የተደረገውን ልዩ ዝግጅት አስታውሳቸው።—የጥቅምት 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 አንቀጽ 6ን ተመልከት።
መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ) የሰኔ 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው የመጽሔት ደንበኛ ለሆነ ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግለት የሚያሳይ ይሁን።
15 ደቂቃ:- “ያለ ቃል የሚሰጥ ምሥክርነት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የአምላክ ሕዝቦች ያላቸውን ጥሩ ምግባር ማየታቸው የይሖዋ አገልጋይ እንዲሆኑ እንዴት እንደረዳቸው እንዲናገሩ አንዳንድ አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ።
20 ደቂቃ:- በመጀመሪያው ውይይት ላይ መጽሐፍ ቅዱስ መጠቀም። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመስከረም 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 አንቀጽ 2 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኛችሁትን ሰው ስታነጋግሩ በአምላክ ቃል ስለመጠቀም የቀረቡትን ሐሳቦች ከልስ። ከቀረቡት የመግቢያ ሐሳቦች መካከል አንድ ወይም ሁለቱን ተጠቅሞ በመስከረም ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በጥር 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ካሉት የመግቢያ ሐሳቦች መካከል አንዳንዶቹን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል መናገር እንዲሁም በሠርቶ ማሳያ ማቅረብ ትችላለህ።
መዝሙር 3 (6) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች።”
15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 12።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጥናት በማስጀመርም ሆነ በመምራት ረገድ እድገት እንዲያደርጉ የረዳቸው ነገር ምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
20 ደቂቃ:- አረጋውያንን ለመርዳት መደራጀት። በነሐሴ 15, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-29 ላይ በሚገኘው “በተደራጀ መልክ መሥራት ጠቃሚ ነው” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በቀረበው ሐሳብ ላይ ተመስርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው አረጋውያንንና የታመሙትን ለመርዳት ያደረገውን ዝግጅት ተናገር።
መዝሙር 72 (164) እና የመደምደሚያ ጸሎት።