የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 82 (183)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- “የምታመሰግኑ ሁኑ።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
20 ደቂቃ:- “ያዘኑትን አጽናኗቸው።”* የሚወደውን ሰው በሞት ያጣን ግለሰብ ማጽናናት አስደሳች ውጤት እንደሚያስገኝ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 18 (42)
ሚያዝያ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19 (43)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አድማጮች በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው፤ እንዲሁም ክፍሉ ሲቀርብ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ ለክልላችሁ የሚስማሙ የመግቢያ ሐሳቦችን እንዲዘጋጁ ንገራቸው።
10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም “ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?” የሚለውን ማቅረብ ትችላላችሁ። (km 10/02 ገጽ 8)
25 ደቂቃ:- መጽሐፍ ቅዱስ ልጆችህን ለማሠልጠን ይረዳህ ይሆን? በሰኔ 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 4-7 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አንቀጽ 6 ላይ ስትደርስ መልካም ባሕርይ አስፈላጊ መሆኑን ጎላ አድርገህ ተናገር። በገጽ 6 ላይ ከሚገኙት ነጥቦች በተጨማሪ ልጆችን ለመስክ አገልግሎት ማሠልጠን ያለውን ጥቅም ግለጽ።
መዝሙር 57 (136)
ሚያዝያ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 14 (34)
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሚያዝያ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊጠቀሙባቸው ላሰቧቸው ርዕሶች የተዘጋጇቸውን መግቢያዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? ከዚያስ በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? የሚነበበው ጥቅስ ለተነሳው ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ የሚደግፈው እንዴት ነው? አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች አሊያም በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኙትን የናሙና መግቢያዎች በመጠቀም መጽሔቶቹ ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ:- “የእሱን ፈለግ ተከተሉ።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
መዝሙር 66 (155)
ግንቦት 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ይሖዋ በፍጹም አይተውህም። በጥቅምት 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-11 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር፤ አበረታች በሆነ መንገድ አቅርበው።
20 ደቂቃ:- “በስብከቱ ሥራ እድገት የምታደርግ ሁን።”* አንቀጽ 2ን ስትወያዩ እድገት የሚያደርግ አንድ የምሥራቹ ሰባኪ፣ “ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብንወያይ ደስ ይለኛል። ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነህ?” ከማለት ይልቅ ትኩረት የሚስብ መግቢያ እንደሚጠቀም ጎላ አድርገህ ተናገር። በተጨማሪም እድገት የሚያደርግ የወንጌል ሰባኪ ከዚህ በፊት ጽሑፍ ወደሰጠው ግለሰብ ተመልሶ ሲሄድ “የሰጠሁህን ጽሑፍ አነበብከው? ጥያቄስ አለህ?” ከማለት ይልቅ በመጀመሪያው ቀን ላይ በቀጣዩ ውይይታቸው መልስ የሚሰጥበትን አንድ ጥያቄ በማንሳት ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ይጥላል። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 6-8 ላይ ከሚገኘው “ከሥልጠናው ሙሉ ጥቅም ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 44 (105)
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።