የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g98 9/8 ገጽ 3-4
  • ጥላቻ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥላቻ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?
  • ንቁ!—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩና መጥፎ ጎን ያላቸው ጥላቻዎች
  • ጥላቻ የተስፋፋው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ጥላቻን ድል ማድረግ እንችላለን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
  • ጥላቻ የሚወገድበት ጊዜ ይኖር ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ጥላቻ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1998
g98 9/8 ገጽ 3-4

ጥላቻ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?

ጀርመን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

“ለምን?”—አጭር ግን ምላሽ የሚጠይቅ ቃል። ለምሳሌ ያህል በደንብሌን ስኮትላንድ በመጋቢት ወር 1996 በአንድ ትምህርት ቤት ደጃፍ ላይ በተቀመጠ የአበባና የአሻንጉሊቶች ክምር ላይ ተለጥፎ ለነበረው “ለምን?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የማይፈልግ ሰው አይኖርም። ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ሰው ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ዘው ብሎ ገብቶ 16 ሕፃናትንና አስተማሪያቸውን በጥይት ገድሎ ነበር። ሌሎች በርካታ ሰዎችን ካቆሰለ በኋላ የጠመንጃውን አፈሙዝ ወደ ራሱ አዞረ። ይህ ሰው ለራሱም ሆነ ለሌሎች እንዲሁም ለጠቅላላው ኅብረተሰብ ከፍተኛ ጥላቻ እንደነበረው ግልጽ ነው። የሕፃናቱ ሞት ያሳዘናቸው ወላጆች፣ ጓደኞችና በመላው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ‘ምንም የማያውቁ ንጹሐን ሕፃናት በዚህ መንገድ ለምን ይሞታሉ? ለምን?’ ሲሉ ጠይቀዋል።

አንተም ብትሆን ዓለም እንዲህ ባለው ግራ የሚያጋባ ጭፍን ጥላቻ እንደተሞላ ልብ ሳትል አትቀርም። እንዲያውም አንተ ራስህ በአንድ የሆነ ምክንያት የዚህ ዓይነቱ ጥላቻ ዒላማ ሆነህ ይሆናል። አንተም ምናልባት ለበርካታ ጊዜያት ‘ለምን?’ ብለህ ሳትጠይቅ አትቀርም።

ጥሩና መጥፎ ጎን ያላቸው ጥላቻዎች

“መጥላት” ወይም “ጥላቻ” “የከረረ ጥል ወይም ባላጋራነት” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። እርግጥ ነው፣ ጎጂ ለሆኑ ወይም የግለሰቦችን ወዳጅነት ሊያሻክሩ ለሚችሉ ነገሮች “የከረረ ጥል ወይም ባላጋራነት” ማዳበር ጠቃሚነት አለው። ሰው ሁሉ እንዲህ ያለውን ጥላቻ ቢያዳብር ኖሮ ዓለማችን አሁን ካለችበት በጣም በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኝ ነበር። የሚያሳዝነው ግን ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች ትክክል ባልሆኑ ምክንያቶች ተነሳስተው ትክክለኛ ያልሆነ ጥላቻ ያዳብራሉ።

አንድ ትርጉም ጎጂ የሆነ ጥላቻ የሚመሠረተው በጭፍን አስተሳሰብ፣ ባለማወቅ ወይም በተሳሳተ መረጃ ላይ እንደሆነና እንዲህ ዓይነቱም ጥላቻ አብዛኛውን ጊዜ “በፍርሐት፣ በቁጣ ወይም በደል ደርሶብኛል በሚል ስሜት” እንደሚቀጣጠል ይገልጻል። ይህ ዓይነቱ ጥላቻ ትክክለኛ የሆነ መሠረት ስለ ሌለው መጥፎ ውጤት ያስከትላል፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ ‘ለምን?’ የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

ሁላችንም ጠባያቸው ወይም ልማዳቸው የሚያናድድና አንዳንድ ጊዜም አብሮ ለመኖር አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎች ያጋጥሙናል። ይሁን እንጂ መናደድ አንድ ነገር ሲሆን በሌላ ሰው ላይ አካላዊ ጉዳት ለማድረስ መፈለግ ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ለአንድ የሰዎች ቡድን በጅምላ፣ ብዙውን ጊዜም ጨርሶ ለማያውቃቸው ሰዎች የከረረ ጥላቻ ሊያድርበት የሚችለው እንዴት እንደሆነ መረዳት ያዳግተናል። እነዚህ ሰዎች ከእርሱ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ሊኖራቸው፣ የተለየ ሃይማኖት ተከታዮች ወይም የተለየ ጎሣ አባል ሊሆኑ ይችላሉ። ታዲያ እነዚህ ምክንያቶች ሰዎቹን ለመጥላት በቂ ምክንያቶች ይሆናሉ?

በጊዜያችን ግን ይህን የመሰለ ጥላቻ አለ! በ1994 አፍሪካ ውስጥ በምትገኘው በሩዋንዳ፣ የሁቱና የቱትሲ ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ያደረገው ይህ ዓይነቱ ጥላቻ ነው። ይህን የተመለከተች አንዲት ጋዜጠኛ “ይህችን በምታክል ትንሽ አገር ውስጥ ይህን ያክል ጥላቻ ሊነግሥ የቻለው እንዴት ነው?” ስትል ጠይቃለች። በመካከለኛው ምሥራቅ በአረቦችና በእስራኤላውያን ለሚከሰተው የሽብርተኝነት ጥቃት ዋነኛው መነሻ ይኸው የጥላቻ ስሜት ነው። በአውሮፓ የምትገኘው የቀድሞዋ ዩጎዝላቭያ የተገነጣጠለችው በዚሁ የጥላቻ ስሜት የተነሳ ነው። አንድ ጋዜጣ ላይ የሰፈረ ዘገባ እንደሚያመለክተው በዩናይትድ ስቴትስም “250 የሚያክሉ የጥላቻ ቡድኖች” የዘረኝነት አስተሳሰቦችን እያሰራጩ ናቸው። ጥላቻ ይህን ያህል የተስፋፋው ለምንድን ነው? ለምን?

ጥላቻ በጣም ሥር ስለሚሰድ በጥላቻው ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት እልባት ካገኘ በኋላ እንኳን አይወገድም። በጦርነት በፈራረሱና በአሸባሪዎች በወደሙ አገሮች ሰላምና የተኩስ አቁም ስምምነት ማስከበር አስቸጋሪ የሚሆንበት ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? በ1995 መጨረሻ ላይ የሳራዬቮ ከተማ በቦስንያና በሄርዞጎቪና-ክሮአት ፌዴሬሽን ተዋህዳ እንድትተዳደር በፓሪስ ከተማ ውል ከተፈረመ በኋላ ያን የሚያክል ችግር የደረሰው በምን ምክንያት ሊሆን ይችላል? በዚያ ይኖሩ ከነበሩት ሰርቦች አብዛኞቹ የአጸፋ እርምጃ ይወሰድብናል ብለው በመፍራት ከተማዋንና አካባቢዋን ጥለው ሸሽተዋል። ታይም መጽሔት ሰዎች ጥለዋቸው የሚሄዱትን ሕንጻዎች እንዳፈራረሱና እንዳቃጠሉ ከዘገበ በኋላ “ሳራዬቮ ዳግመኛ አንድ ልትሆን ብትችልም ሕዝቦቿ ግን አንድ ለመሆን አልቻሉም” በማለት ደምድሟል።

የሃሰት የብር ኖቶች ዋጋ እንደሌላቸው ሁሉ እርስ በርሳቸው በሚጠላሉ ሕዝቦች መካከል የሚፈጠር የይስሙላ ሰላምም እንዲሁ ዋጋ አይኖረውም። ከበስተጀርባው ምንም ዓይነት ዋስትና የሚሰጥ ኃይል ስለማይኖረው ትንሽ ግፊት ሲያጋጥመው ይናዳል። አዎን፣ በዓለማችን ውስጥ ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ነግሷል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ጎጂ የሆነ ጥላቻ የሚመሠረተው በጭፍን አስተሳሰብ፣ ባለማወቅ ወይም በተሳሳተ መረጃ ነው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ