ዓመታዊ ስብሰባ—ጥቅምት 5, 1991
የፔንሲልቫኒያ የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና የትራክት ማኅበር አባሎች ዓመታዊ ስብሰባ ጥቅምት 5, 1991 ኒው ጄርሲ ውስጥ በጄርሲ ከተማ 2932 ኬኔዲ ቦሊቫርድ በይሖዋ ምስክሮች ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ይደረጋል። የአባሎቹ የመጀመሪያ ደረጃ ስብሰባው ከጧቱ በ3:30 ይደረግና የ4 ሰዓቱ አጠቃላይ ዓመታዊ ስብሰባ ይከተላል።
የማኅበሩ አባሎች ባለፈው ዓመት ወቅት የተደረገ ማንኛውም የፖስታ አድራሻ ለውጥ ካለ የማስታወቂያ ደብዳቤዎችና ውክልናዎች ከነሐሴ 1 በኋላ ይደርሷቸው ዘንድ አሁንኑ ለጸሐፊው ቢሮ ማስታወቅ አለባቸው።
ለአባሎቹ ከዓመታዊ ስብሰባው ማስታወቂያ ጋር የሚላኩላቸው ውክልናዎች ከነሐሴ 15 ባልበጠ ጊዜ ለማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ይደርሱ ዘንድ ተመላሽ መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ በግል ይገኝ ወይም አይገኝ እንደሆነ በመግለጽ ውክልናውን ወዲያውኑ ሞልቶ መመለስ አለበት። በእያንዳንዱ የውክልና ቅጽ ላይ የሚሰጠው መረጃ በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ መሆን አለበት ምክንያቱም ማን በግል እንደሚገኝ ለመወሰን መተማመኛው እሱ ስለሆነ ነው።
ጠቅላላው ስብሰባ የመደበኛው ጉዳይ ስብሰባና ሪፖርትም ጭምር ከቀኑ እስከ ሰባት ሰዓት ወይም ከዚያ ትንሽ እልፍ ብሎ እንደሚያበቃ ይጠበቃል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ መግባት የሚቻለው በቲኬት ብቻ ይሆናል። ዓመታዊ ስብሰባውን ወደ ሌሎች የጉባኤ አዳራሾች በስልክ መስመሮች ለማገናኘት ዝግጅት አይደረግም።