ዓመታዊ ስብሰባ—ጥቅምት 3, 1992
የፔንስልቫንያ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማህበር አባሎች ዓመታዊ ስብሰባ በኬኔዲ ቡልቫርድ 2932 ጀርሲ ሲቲ፣ ኒው ጀርሲ በሚገኘው የይሖዋ ምስክሮች የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ጥቅምት 3, 1992 ይካሄዳል። በመጀመሪያው የማህበሩ አባላት ብቻ የሚገኙበት ስብሰባ በ3:30 ይጀምራል። ከዚያ በኋላ አጠቃላዩ ዓመታዊ ስብሰባው በ4:00 ሰዓት ይጀምራል።
የማህበሩ አባላት ከነሐሴ 1 በኋላ የሚላክላቸው ተከታታይ ደብዳቤና መልእክት እንዲደርሳቸው ካለፈው ዓመት ወዲህ ቋሚ አድራሻቸውን ለውጠው ከሆነ አሁኑኑ ለማህበሩ ጸሐፊ ቢሮ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።
ለአባላቱ የሚላከው የዓመታዊው ስብሰባ የማስታወቂያና የውክልና ደብዳቤ ለማህበሩ ጸሐፊ ቢሮ ከነሐሴ 15 ቀን በፊት እንዲደርስ ሳይዘገይ መመለስ ይኖርበታል። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ ይገኝ እንደሆነና እንዳልሆነ በመግለጽ የውክልናውን ሰነድ ወዲያውኑ አጠናቅቆ መሙላትና መመለስ ይኖርበታል። በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የሚሰጠው መረጃ የማያሻማ መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም በስብሰባው ላይ የሚገኙትንና የማይገኙትን ለማወቅ የሚቻለው በዚህ መረጃ አማካኝነት ብቻ ነው።
አጠቃላዩ ስብሰባ የማህበሩን የአሠራር ጉዳዮችንና ሪፖርቶችን ጨምሮ በ7:00 ሰዓት ላይ ወይም ከዚያ ትንሽ ዘግየት ብሎ ይጠናቀቃል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ የተወሰነ ስለሆነ ወደ ስብሰባው መግባት የሚፈቀደው ትኬት ለያዙ ብቻ ነው። የስብሰባውን ሂደት ከስልክ መስመሮች ጋር አገናኝቶ ለሌሎች አካባቢዎች ለማስተላለፍ የተደረገ ምንም ዓይነት ዝግጅት የለም።