የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/93 ገጽ 1
  • “ና!” ማለትህን ቀጥል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ና!” ማለትህን ቀጥል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዴት ብለህ ትመልሳለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ስሜት ቀስቃሽ መልእክት አውጅ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • መልእክቱን ተቀብለው እርምጃ እንዲወስዱ እርዳቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 3/93 ገጽ 1

“ና!” ማለትህን ቀጥል

1 ይሖዋ በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት እንዴት ያለ ግሩም ዝግጅት አድርጎልናል! በዚህ ዝግጅት ላይ ሰዎችን ሁሉ በእውነት ደስተኛ ለማድረግ የሚያስፈልገውን መሠረት እናገኛለን። (ዮሐ. 3:16) የሚያሳዝነው ግን ይህንን እውነት ያወቁና በጽኑ ያመኑበት በጣም ጥቂቶች ናቸው። አሁንም ቢሆን ይሖዋ ለሰው ልጆች ካለው ፍቅራዊ አሳቢነት የተነሳ በየትም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ይህንን የምሥራች እንዲያውቁት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል። በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሰዎች ሁሉ ደስታና የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚያገኙበትን አጋጣሚ ዘርግቶላቸዋል። — ዮሐ. 17:3

2 ሰዎችን ከኃጢአትና ከሞት የሚቤዣቸው ማን እንደሚሆን በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሳይታወቅ ቆይቶ ነበር። ክርስቶስ ኢየሱስ መጥቶ “በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን” እስኪያወጣ ድረስ “ቅዱስ ምሥጢር” ሆኖ ነበር። (ሮሜ 16:25፤ 2 ጢሞ. 1:10) የኢየሱስ ተከታዮች በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይህንን የምሥራች አውጀዋል። አሁን በዘመናችን የምንኖረው እኛም ይህንኑ ምሥራች የማወጅ ከፍ ያለ መብት አለን። የመንግሥቱን መልእክት በምንሰብክበት ጊዜ ከይሖዋ አምላክና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንዲሁም ‘ኑ! . . . የሕይወትን ውኃ በነፃ ውሰዱ’ በማለት በየትኛውም የኑሮ ዘርፍ ያሉትን ሰዎች በመጋበዝ ላይ ከሚገኙት የክርስቶስ ወንድሞች ጋር እየተባበርን ነው። — ራእይ 22:17

3 እርግጥ፣ ይህንን ምሥራች እሺ ብሎ የሚሰማ ሁሉም ሰው አይደለም። ልብ ብለው የሚያዳምጡ በጣም ጥቂቶች ናቸው። አንዳንዶች ሕይወት ሰጪ የሆነውን የእውነት ውኃ ተቀብለው በእርሱ እንዲጠቀሙ የሚጋብዟቸውን የአምላክን አገልጋዮች አክብሮት በጎደለው ሁኔታ ያባርሯቸዋል። ቢሆንም ከይሖዋ በምናገኘው ኃይል በዚህ ሥራ እንገፋበታለን። እውነትን ለመናገርና የሚሰማንን ሁሉ ለመርዳት ያለን ፈቃደኝነት ይሖዋን እንደሚያስደስተው እንዲሁም በረከትን እንደሚያመጣልን እናውቃለን።

4 በመጋቢት በምናከናውነው አገልግሎታችን እውነት ፈላጊዎች ራእይ ታላቁ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ እንዲያነቡትና መጽሐፉ ከፊታችን በሚያስቀምጥልን ተስፋ እንዲደሰቱ እናበረታታቸዋለን። እንዲህ በማድረጋቸው በአጸፋው ብዙ በረከቶችን ያገኛሉ። የራእይ መጽሐፍ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ማለትም ስለ እነርሱም ሆነ ስለ እኛ የወደፊት ሁኔታ የሚናገር ነው። አሁን ራሳቸውን የወሰኑ የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑ አንዳንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እውነት ሊሳቡ የቻሉት ከማኅበር ጽሑፎች በአንዱ ውስጥ ስለ ራእይ መጽሐፍ የተሰጠውን ማብራሪያ ካነበቡ በኋላ ነው። ራእይ ታላቁ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ ራሳችን አንድ በአንድ ካጠናነው በኋላ መጽሐፉ እውነትን እየተራቡ ላሉ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ያለውን አስፈላጊነት ለመረዳት እንችላለን። በአገልግሎታችን እንዲህ ዓይነት ሰዎችን በምናገኝበት ጊዜ የመጽሐፉን ጠቃሚነት ለማሳየት ራእይ ታላቁ መደምደሚያው ከተባለው መጽሐፍ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ጎላ ያሉ ነጥቦችን ልንጠቅስላቸው ጥረት እናደርጋለን። ከሌሎች ነጥቦች በተጨማሪ በዚህ በ20ኛው መቶ ዘመን ስለተፈጸሙት ለምሳሌ በስድስተኛው የራእይ ምዕራፍ ላይ እንደ ተገለጹት ምሳሌያዊ ፈረሶች አስደናቂ ግልቢያ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የሚሰጠውን ግልጽ ማብራሪያ ልንጠቅስላቸው እንችላለን።

5 ሚያዝያ 6 ቀን የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ በዓል ልናከብር እየተዘጋጀን ባለንበት ወቅት ይሖዋ ለሰው ዘሮች ስላደረጋቸው ፍቅራዊ ዝግጅቶች መናገራችን በጣም ተገቢ ነው። ሰዎች እሺ ብለው ለመስማት ቢመርጡም ባይመርጡ ለሚፈልግ ሁሉ ‘ና! . . . የሕይወትን ውኃ በነፃ ውሰድ’ የሚለውን የሚያበረታታ ግብዣ እንድናቀርብ ከአምላክ የተሰጠንን ሥራ መሥራታችንን እንገፋበታለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ