‘ማን ይሄድልናል?’
ይሖዋ ይህን ጥያቄ ባነሳበት ጊዜ ኢሳይያስ ወዲያውኑ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” በማለት መልስ ሰጥቷል። (ኢሳ. 6:8) ዛሬም መከሩ ታላቅ በመሆኑ ምክንያት ተመሳሳይ የሆነ ጥሪ እያስተጋባ ነው። ተጨማሪ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ማለትም የዘወትር አቅኚዎች በአስቸኳይ ይፈለጋሉ! (ማቴ. 9:37) ራስህን በፈቃደኝነት ለማቅረብ ትፈልጋለህ? የምትፈልግ ከሆነ የ1998 አገልግሎት ዓመት መጀመሪያ የሆነው መስከረም 1 የአቅኚነት አገልግሎት ለመጀመር ጥሩ ጊዜ ነው። ሽማግሌዎች የአቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ እንዲሰጡህ ለምን አትጠይቃቸውም?