‘በተገቢው ጊዜ የቀረበ ምግብ’
1. በቅርቡ የተደረገው የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም አንተንም ሆነ ሌሎችን የጠቀመው እንዴት ነው?
1 በልዩ ስብሰባዎቻችን ላይ ከተገኘን በኋላ አብዛኛውን ጊዜ “እንዲህ ዓይነት ትምህርት ያስፈልገን ነበር!” እንላለን። አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች በወረዳው ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወንድሞች ስብሰባውን ከተካፈሉ በኋላ በአገልግሎት ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት እንደገለጹ ሪፖርት አድርጓል። አንድ ተጓዥ የበላይ ተመልካች “ስብሰባው በጊዜ ሂደት ውስጥ የት ቦታ ላይ እንደምንገኝ በግልጽ ተገንዝበን በሕይወታችን ውስጥ ያደረግናቸውን ምርጫዎች መለስ ብለን እንድንገመግም ረድቶናል” በማለት ተናግሯል። ሌላ ተጓዥ የበላይ ተመልካች ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “በርካታ አስፋፊዎች ስብሰባው በጣም አስፈላጊ ለሆነው ነገር ይኸውም ለአገልግሎት ትኩረት እንዲሰጡ እንዳነቃቸው ሐሳብ ሰጥተዋል።” አንተስ የልዩ ስብሰባ ቀን የጠቀመህ እንዴት ነው?
2. በሚቀጥለው የአገልግሎት ዓመት የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የትኞቹ ንግግሮች ይቀርባሉ?
2 በቀጣዩ የአገልግሎት ዓመት በሚደረገው የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም ላይም በወቅቱ የሚያስፈልገን ትምህርት ይቀርባል። የስብሰባው ጭብጥ ‘ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጉት’ የሚል ሲሆን የተመሠረተው በመዝሙር 118:8, 9 NW ላይ ነው። በስብሰባው ላይ ከሚቀርቡት ንግግሮች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ “ይሖዋ በመከራ ወቅት ምሽግ የሚሆነው እንዴት ነው?” “ሌሎች ሰዎች በይሖዋ ክንፎች ውስጥ መጠጊያ እንዲያገኙ እርዷቸው፣” “መጠጊያ በመሆን ረገድ ይሖዋን ምሰሉ፣” “እናንተ ወጣቶች ይሖዋን መታመኛችሁ አድርጉት!” እና “ይሖዋ መጠጊያ እንድናገኝ ሲል ያዘጋጀልን መንፈሳዊ ገነት።”
3. ከስብሰባው የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?
3 ከፕሮግራሙ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?፦ የስብሰባው ቀን እንደታወቀ እዚያ ለመገኘት ቁርጥ ያለ እቅድ አውጣ፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችህ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ጋብዝ። ‘በጽናት ፍሬ ለማፍራት’ እንድንችል የሰማነውን ነገር መርሳት የለብንም። (ሉቃስ 8:15) ስለዚህ ስብሰባውን በጥሞና አዳምጥ፤ ዋና ዋና ነጥቦችን እንዲሁም በግል ሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ልትሠራባቸው ያሰብካቸውን ነጥቦች በማስታወሻህ ላይ አጠር አድርገህ አስፍር። ከስብሰባው በኋላ ደግሞ ስብሰባውን በቤተሰብ ደረጃ ለመከለስና አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ተግባራዊ ልታደርጓቸው ስለምትችሏቸው ነጥቦች ለመወያየት ጊዜ መድብ።
4. መጪውን የልዩ ስብሰባ ቀን በጉጉት የምንጠብቀው ለምንድን ነው?
4 ታማኝና ልባም ባሪያ በፍቅር በመነሳሳት ልክ እንደ ጣፋጭና ገንቢ ምግብ ሁሉ የዚህን ዓመት ልዩ ስብሰባም በሚገባ አስቦበት አዘጋጅቶልናል። በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ለክርስቲያን አገልጋዮች ‘በተገቢው ጊዜ ከቀረበው’ ከዚህ መንፈሳዊ “ምግብ” ሙሉ ጥቅም ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ይሖዋ እንዲባርክልህ እንመኛለን።—ማቴ. 24:45