በጽሑፍ መደርደሪያዎች ተጠቅሞ መመሥከር የሚቻለው እንዴት ነው?
ጋሪ ወይም ጠረጴዛ በመጠቀም የሚሰጠው ምሥክርነት ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ወደ እውነት እንዲሳቡ በመርዳት ረገድ በጣም ውጤታማ መሆኑ እየታየ ነው። (ዮሐ. 6:44) በመሆኑም ሽማግሌዎች ከፍተኛ የእግረኛ ፍሰት ባለባቸው የጉባኤያቸው ክልሎች ውስጥ የአደባባይ ምሥክርነት ለመስጠት ዝግጅት እንዲያደርጉ ተበረታትተዋል። ተንቀሳቃሽ የጽሑፍ መደርደሪያዎች በአንድ ቦታ ስለማይቀመጡ በአጠቃላይ ሲታይ የባለሥልጣናትን ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልግም። በዚህ ሥራ ለመካፈል ብቃት ያላቸው እነማን ናቸው? ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ፣ የሚያስከብር አቋምና ከሰዎች ጋር ውይይት የማድረግ ችሎታ ያላቸው አስፋፊዎች በዚህ ሥራ ሊካፈሉ ይችላሉ። አስፋፊዎች በሥራው ይበልጥ ውጤታማ መሆን ከፈለጉ ሊያደርጓቸው የሚገቡና ሊያደርጓቸው የማይገቡ ነገሮች ከዚህ በታች ቀርበዋል።