የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/09 ገጽ 2
  • ለማስተማር ጥሩ ዝግጅት አድርግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለማስተማር ጥሩ ዝግጅት አድርግ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ተጠምቀው ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህን ልብ ለመንካት ጣር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 6/09 ገጽ 2

ለማስተማር ጥሩ ዝግጅት አድርግ

1. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በምንመራበት ወቅት ተማሪው አድናቆት እንዲያዳብር ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

1 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በምንመራበት ወቅት የምናስጠናው ሰው ይሖዋን ለማገልገል እንዲነሳሳ የምንፈልግ ከሆነ ጥሩ አድርገን መዘጋጀት ይኖርብናል። ጥሩ ውጤት ለማግኘት ተማሪው ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አድናቆት እንዲያዳብር መርዳት ይኖርብናል። ተማሪው ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አድናቆት ካለው ለተግባር ይነሳሳል። (ዘዳ. 6:5፤ ምሳሌ 4:23፤ 1 ቆሮ. 9:26) ታዲያ ተማሪው አድናቆት እንዲያዳብር መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

2. ጥሩ ዝግጅት ለማድረግ ጸሎት ምን ሚና ይጫወታል?

2 ጸሎት የታከለበት ዝግጅት፦ በተማሪው ልብ ውስጥ የተዘራውን የእውነት ዘር የሚያሳድገው ይሖዋ እንደመሆኑ መጠን ተማሪውን ለማስጠናት የምናደርገውን ዝግጅት ከመጀመራችን በፊት ተማሪውንም ሆነ እሱ ያለበትን ሁኔታ ጠቅሰን መጸለያችን ተገቢ ነው። (1 ቆሮ. 3:6፤ ያዕ. 1:5) እንዲህ ያለው ጸሎት የተማሪው ልብ ስለ ይሖዋ ፈቃድ በሚናገረው “ትክክለኛ እውቀት” እንዲሞላ ምን ተጨማሪ ነገር ማድረግ እንደምንችል እንድናውቅ ያግዘናል።—ቆላ. 1:9, 10

3. ተማሪውን በአእምሯችን ይዘን መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

3 የተማሪውን ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገባ፦ ኢየሱስ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተማር አድማጮችን ግምት ውስጥ ማስገባትን እንደሚጨምር ያውቅ ነበር። ኢየሱስ፣ ቢያንስ ሁለት ጊዜ “የዘላለም ሕይወት መውረስ የምችለው ምን ባደርግ ነው?” የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። ለዚህ ጥያቄ መልስ በሰጠበት ጊዜ ሁሉ የተለያየ አቀራረብ ተጠቅሟል። (ሉቃስ 10:25-28፤ 18:18-20) በመሆኑም ዝግጅት በምናደርግበት ጊዜ ተማሪውን በአእምሯችን መያዝ ይኖርብናል። ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ ከተሰጡት ጥቅሶች መካከል የምናነበው የትኞቹን ነው? የምናጠናው ምን ያህል አንቀጾችን ነው? ተማሪው ከትምህርቱ ውስጥ ለመረዳት ወይም ለመቀበል አስቸጋሪ የሚሆንበት ሐሳብ የትኛው ነው? ተማሪው ሊያነሳቸው የሚችላቸውን ጥያቄዎች አስቀድመን መገመታችን ጥሩ መልስ ለመስጠት በሚገባ እንድንዘጋጅ ያስችለናል።

4. ጥሩ ዝግጅት ማድረግ ምን ይጨምራል?

4 ትምህርቱን ከልስ፦ መጽሐፉን ከዚህ ቀደም ምንም ያህል ጊዜ ያነበብነው ቢሆንም ከዚህ ጥናታችን ጋር የምናጠናው ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ መዘንጋት አይኖርብንም። የተማሪውን ልብ መንካት የምንፈልግ ከሆነ ለእያንዳንዱ ጥናት ጥሩ ዝግጅት ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ተማሪውንም ቢሆን የምናበረታታው እንዲሁ እንዲያደርግ ነው። ተማሪውን በአእምሮህ ይዘህ ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን ጨምሮ አጠቃላይ ትምህርቱን ከልስ፤ ምናልባትም ቁልፍ ነጥቦች ላይ ማስመር ያስፈልግህ ይሆናል።—ሮም 2:21, 22

5. ይሖዋን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

5 ይሖዋ የእያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እድገት በጉጉት ይከታተላል። (2 ጴጥ. 3:9) ለእያንዳንዱ ጥናት ጥሩ ዝግጅት ለማድረግ በቂ ጊዜ በመመደብ እኛም ተመሳሳይ ጉጉት እንዳለን እናሳይ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ