ኢሳይያስ
46 ቤል ያጎነብሳል፤+ ነቦ አንገቱን ይደፋል።
ጣዖቶቻቸው በደከሙ እንስሳት ላይ እንደሚጫን ከባድ ጭነት
በእንስሳት ይኸውም በጋማ ከብቶች ላይ ተጭነዋል።+
3 “የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ከእስራኤልም ቤት የቀራችሁት ሁሉ፣+
ከተወለዳችሁበት ጊዜ አንስቶ የረዳኋችሁ፣ በማህፀን ከነበራችሁበት ጊዜም አንስቶ የተሸከምኳችሁ+ ስሙኝ።
4 እስከ እርጅናችሁ ዘመን ድረስ እኔ ያው ነኝ፤+
ፀጉራችሁ እስኪሸብትም ድረስ እሸከማችኋለሁ።
ከዚህ ቀደም እንዳደረግኩት እሸከማችኋለሁ፣ እደግፋችኋለሁ እንዲሁም እታደጋችኋለሁ።+
6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤
ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ።
አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+
7 አንስተው ትከሻቸው ላይ ያደርጉታል፤+
ተሸክመው ወስደው ቦታው ላይ ያኖሩታል፤ በዚያም ዝም ብሎ ይቆማል።
ካለበት ቦታ አይንቀሳቀስም።+
ወደ እሱ ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስም፤
ማንንም ከጭንቀት ሊታደግ አይችልም።+
8 ይህን አስታውሱ፤ ደግሞም አይዟችሁ።
እናንተ ሕግ ተላላፊዎች ይህን ልብ በሉ።
እኔ አምላክ ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።+
10 ከመጀመሪያ መጨረሻውን፣
ገና ያልተከናወኑትንም ነገሮች ከረጅም ጊዜ በፊት አስቀድሜ እናገራለሁ።+
ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም እፈጽመዋለሁ።
ይህን ለማድረግ አስቤአለሁ፤ አደርገዋለሁም።+
12 እናንተ ልበ ደንዳኖች፣*
እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ ሰዎች ስሙኝ።
በጽዮን መዳን አስገኛለሁ፤ ለእስራኤልም ግርማዬን አጎናጽፋለሁ።”+