አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኢዮብ የመጽሐፉ ይዘት ኢዮብ የመጽሐፉ ይዘት 1 የኢዮብ ንጹሕ አቋምና የነበረው ሀብት (1-5) ሰይጣን የኢዮብን የልብ ዝንባሌ በተመለከተ ጥያቄ አነሳ (6-12) ኢዮብ ንብረቱንና ልጆቹን አጣ (13-19) ኢዮብ አምላክን አላማረረም (20-22) 2 ሰይጣን የኢዮብን የልብ ዝንባሌ በተመለከተ በድጋሚ ጥያቄ አነሳ (1-5) ሰይጣን ኢዮብን በቁስል እንዲመታው ተፈቀደለት (6-8) የኢዮብ ሚስት “አምላክን እርገምና ሙት!” አለችው (9, 10) የኢዮብ ሦስት ጓደኞች መጡ (11-13) 3 ኢዮብ የተወለደበትን ቀን ረገመ (1-26) መከራ የደረሰበት ለምን እንደሆነ ጠየቀ (20, 21) 4 የኤሊፋዝ የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-21) የኢዮብን ንጹሕ አቋም አጣጣለ (7, 8) መንፈስ ሹክ ያለውን መልእክት ተናገረ (12-17) ‘አምላክ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት የለውም’ (18) 5 ኤሊፋዝ ንግግሩን ቀጠለ (1-27) ‘አምላክ ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል’ (13) ‘ኢዮብ የአምላክን ተግሣጽ መናቅ አይኖርበትም’ (17) 6 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-30) ማማረሩ ስህተት እንዳልሆነ ገለጸ (2-6) አጽናኞቹ ከዳተኞች ሆኑበት (15-18) “በሐቀኝነት የተነገረ ቃል አያቆስልም!” (25) 7 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-21) ሕይወት እንደ ግዳጅ አገልግሎት ነው (1, 2) “ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው?” (20) 8 የበልዳዶስ የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-22) የኢዮብ ልጆች ኃጢአት ሠርተው ሊሆን እንደሚችል ጠቆመ (4) ‘ንጹሕ ብትሆን ኖሮ አምላክ ይጠብቅህ ነበር’ (6) ኢዮብ አምላክ የለሽ እንደሆነ ጠቆመ (13) 9 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-35) ሟች ሰው ከአምላክ ጋር ሊሟገት አይችልም (2-4) ‘‘አምላክ የማይመረመሩ ነገሮችን ያደርጋል’ (10) ሰው ከአምላክ ጋር ሊከራከር አይችልም (32) 10 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-22) ‘አምላክ ከእኔ ጋር የሚሟገተው ለምንድን ነው?’ (2) ሟች የሆነው ኢዮብ ራሱን ከአምላክ ጋር አነጻጸረ (4-12) ‘ትንሽ ፋታ ላግኝ’ (20) 11 የሶፋር የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-20) ‘ከንቱ ንግግር ተናግረሃል’ ብሎ ኢዮብን ወቀሰው (2, 3) ክፉ ነገር ከማድረግ እንዲቆጠብ ኢዮብን አሳሰበው (14) 12 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-25) “ከእናንተ አላንስም” (3) “መሳለቂያ ሆኛለሁ” (4) ‘በአምላክ ዘንድ ጥበብ አለ’ (13) አምላክ ከፈራጆችና ከነገሥታት በላይ ነው (17, 18) 13 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-28) ‘አምላክን ባነጋግር እመርጣለሁ’ (3) “ሁላችሁም የማትረቡ ሐኪሞች ናችሁ” (4) “ትክክል እንደሆንኩ አውቃለሁ” (18) አምላክ እንደ ጠላት የቆጠረው ለምን እንደሆነ ጠየቀ (24) 14 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-22) የሰው ሕይወት አጭርና በመከራ የተሞላ ነው (1) “ዛፍ እንኳ ተስፋ አለው” (7) “ምነው በመቃብር ውስጥ በሰወርከኝ!” (13) “ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?” (14) አምላክ የእጁን ሥራ ይናፍቃል (15) 15 የኤሊፋዝ ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-35) ኢዮብ ፈሪሃ አምላክ እንደሌለው ተናገረ (4) ኢዮብ እብሪተኛ እንደሆነ ገለጸ (7-9) ‘አምላክ በቅዱሳኑ ላይ እምነት የለውም’ (15) ‘ሥቃይ የሚደርስበት ሰው ክፉ ነው’ (20-24) 16 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-22) “ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!” (2) አምላክ እሱን ዒላማ እንዳደረገው ተናገረ (12) 17 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-16) “ፌዘኞች ከበውኛል” (2) “አምላክ የሰዎች መቀለጃ አደረገኝ” (6) “መቃብር፣ ቤቴ ይሆናል” (13) 18 የበልዳዶስ ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-21) የኃጢአተኞችን ዕጣ ፋንታ ገለጸ (5-20) ኢዮብ አምላክን እንደማያውቅ ጠቆመ (21) 19 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-29) “የጓደኞቹን” ተግሣጽ ተቃወመ (1-6) ሰዎች እንደራቁት ተናገረ (13-19) ‘የሚዋጀኝ ሕያው ነው’ (25) 20 የሶፋር ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-29) ኢዮብ እንደዘለፈው ተሰማው (2, 3) ኢዮብ ክፉ እንደሆነ የሚጠቁም ቃል ተናገረ (5) ኢዮብ በኃጢአት እንደሚደሰት ተናገረ (12, 13) 21 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-34) ‘ክፉዎች የሚሳካላቸው ለምንድን ነው?’ (7-13) “የአጽናኞቹን” ክፋት አጋለጠ (27-34) 22 የኤሊፋዝ ሦስተኛ ዙር ንግግር (1-30) “ሰው አምላክን ሊጠቅመው ይችላል?” (2, 3) ኢዮብን በስግብግብነትና ፍትሕ በማዛባት ወነጀለው (6-9) ‘ወደ አምላክ ብትመለስ ትታደሳለህ’ (23) 23 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-17) ጉዳዩን በአምላክ ፊት ማቅረብ ፈለገ (1-7) አምላክን ማግኘት እንደማይችል ተናገረ (8, 9) “ምንም ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ” (11) 24 ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-25) “አምላክ ለምን ጊዜ አልወሰነም?” (1) አምላክ ክፋትን እንደሚፈቅድ ተናገረ (12) ኃጢአተኞች ጨለማን ይወዳሉ (13-17) 25 የበልዳዶስ ሦስተኛ ዙር ንግግር (1-6) ‘‘ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’ (4) ሰው ንጹሕ አቋሙን ቢጠብቅ ዋጋ እንደሌለው ተናገረ (5, 6) 26 ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-14) “ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!” (1-4) ‘አምላክ ምድርን ያለምንም ነገር አንጠልጥሏል’ (7) ‘የአምላክ መንገድ ዳር ዳር ናቸው’ (14) 27 ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን ለመጠበቅ ወሰነ (1-23) “ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!” (5) አምላክ የለሽ ሰው ተስፋ የለውም (8) “ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው?” (12) ክፉዎች ባዷቸውን ይቀራሉ (13-23) 28 ኢዮብ የምድርን ውድ ሀብት ከጥበብ ጋር አነጻጸረ (1-28) ሰው ማዕድን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት (1-11) ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለች (18) ይሖዋን መፍራት እውነተኛ ጥበብ ነው (28) 29 ኢዮብ መልካሙን ዘመን አስታወሰ (1-25) በከተማዋ በር ላይ የተከበረ ሰው ነበር (7-10) የተከተለው የፍትሕ ጎዳና (11-17) ሰው ሁሉ ምክሩን ይሰማ ነበር (21-23) 30 ኢዮብ የደረሰበትን ሁኔታ ገለጸ (1-31) የማይረቡ ሰዎች አፌዙበት (1-15) አምላክ ምንም እየረዳው እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበር (20, 21) ‘ቆዳዬ ጠቆረ’ (30) 31 ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን እንዳላጎደፈ በመግለጽ ተሟገተ (1-40) “ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ” (1) አምላክ እንዲመዝነው ጠየቀ (6) አመንዝራ አልነበረም (9-12) የገንዘብ ፍቅር አልነበረውም (24, 25) ጣዖት አምላኪ አልነበረም (26-28) 32 ወጣቱ ኤሊሁ በውይይቱ መሳተፍ ጀመረ (1-22) በኢዮብና በኢዮብ ጓደኞች ላይ ተቆጣ (2, 3) በአክብሮት ዝም ብሎ ቆየ (6, 7) “ዕድሜ በራሱ ሰውን ጥበበኛ አያደርገውም” (9) ኤሊሁ ለመናገር ተነሳሳ (18-20) 33 ኤሊሁ፣ ኢዮብ ራሱን በማመጻደቁ ወቀሰው (1-33) “ቤዛ አግኝቻለሁ!” (24) ወደ ወጣትነቱ ዘመን ይመለስ (25) 34 ኤሊሁ፣ የአምላክ ፍትሕና መንገድ ትክክል መሆኑን ገለጸ (1-37) ኢዮብ፣ አምላክ ፍትሕ እንደነፈገው ተናግሯል (5) እውነተኛው አምላክ ክፋት አይሠራም (10) ኢዮብ እውቀት ይጎድለዋል (35) 35 ኤሊሁ፣ ኢዮብ ያቀረበው ሐሳብ የተሳሳተ መሆኑን ጠቆመ (1-16) ኢዮብ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ እንደሆነ ተናግሯል (2) አምላክ እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ሰው የሚሠራው ኃጢአት ሊጎዳው አይችልም (5, 6) ኢዮብ አምላክን መጠባበቅ አለበት (14) 36 ኤሊሁ የአምላክን ታላቅነት ከፍ ከፍ አደረገ (1-33) ታዛዦች ይበለጽጋሉ፤ አምላክ የለሾች ግን ተቀባይነት አያገኙም (11-13) ‘እንደ አምላክ ያለ አስተማሪ ማን ነው?’ (22) ኢዮብ አምላክን ከፍ ከፍ ማድረግ ይጠበቅበታል (24) “አምላክ እኛ ልናውቀው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው” (26) አምላክ ዝናብንና መብረቅን ይቆጣጠራል (27-33) 37 የተፈጥሮ ኃይሎች የአምላክን ታላቅነት ይገልጣሉ (1-24) አምላክ የሰውን ሥራ መግታት ይችላል (7) “የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በጥሞና አስብ” (14) “አምላክ ከመረዳት ችሎታችን በላይ ነው” (23) ማንም ሰው ጥበበኛ ነኝ ብሎ አያስብ (24) 38 ይሖዋ፣ ሰው አነስተኛ ፍጡር መሆኑን ገለጸ (1-41) ‘ምድር ስትፈጠር አንተ የት ነበርክ?’ (4-6) የአምላክ ልጆች በደስታ እልል አሉ (7) የተፈጥሮ ክስተቶችን በተመለከተ የቀረቡ ጥያቄዎች (8-32) ‘ሰማያት የሚመሩባቸው ሕጎች’ (33) 39 እንስሳት የሰውን አላዋቂነት ያሳያሉ (1-30) የተራራ ፍየሎችና ርኤሞች (1-4) የዱር አህያ (5-8) የዱር በሬ (9-12) ሰጎን (13-18) ፈረስ (19-25) ሲላ እና ንስር (26-30) 40 ይሖዋ ያቀረባቸው ተጨማሪ ጥያቄዎች (1-24) ኢዮብ መልስ እንደሌለው አምኖ ተቀበለ (3-5) “የእኔን ፍትሕ ትጠራጠራለህ?” (8) አምላክ የብሄሞትን ጉልበት ገለጸ (15-24) 41 አምላክ የሌዋታንን አስደናቂ አፈጣጠር ገለጸ (1-34) 42 ኢዮብ ለይሖዋ የሰጠው መልስ (1-6) ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች ተወገዙ (7-9) ይሖዋ ኢዮብን መልሶ ባረከው (10-17) የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች (13-15)