መዝሙር
አምስተኛ መጽሐፍ
(መዝሙር 107-150)
4 በምድረ በዳ፣ በበረሃም ተቅበዘበዙ፤
ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ የሚወስድ መንገድ አላገኙም።
5 ተርበውና ተጠምተው ነበር፤
ኃይላቸው ከመሟጠጡ የተነሳ ተዝለፈለፉ።*
10 አንዳንዶች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖሩ፣
በመከራ ውስጥ ያሉና በሰንሰለት የተጠፈሩ እስረኞች ነበሩ።
11 በአምላክ ቃል ላይ ዓምፀዋልና፤
የልዑሉን አምላክ ምክር ንቀዋል።+
12 ስለዚህ በደረሰባቸው መከራ ልባቸው እንዲለሰልስ አደረገ፤+
ተሰናከሉ፤ የሚረዳቸውም አንዳች ሰው አልነበረም።
13 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ተጣሩ፤
እሱም ከደረሰባቸው መከራ አዳናቸው።
14 ከድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው፤
የታሰሩበትንም ሰንሰለት በጠሰ።+
15 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና
ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+
16 እሱ የመዳብ በሮችን ሰብሯልና፤
የብረት መወርወሪያዎችንም ቆርጧል።+
18 የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ጠፋ፤*
ወደ ሞት ደጆች ቀረቡ።
19 በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤
እሱም ከደረሰባቸው መከራ ያድናቸው ነበር።
20 ቃሉን ልኮ ይፈውሳቸው፣+
ከተያዙበትም ጉድጓድ ይታደጋቸው ነበር።
21 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና
ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።
22 የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡ፤+
በእልልታም ሥራዎቹን ያስታውቁ።
23 በባሕር ላይ በመርከቦች የሚጓዙ፣
በሰፋፊ ውኃዎች ላይ ንግድ የሚያካሂዱ፣+
24 እነሱ የይሖዋን ሥራዎች፣
በጥልቁም ውስጥ ያከናወናቸውን አስደናቂ ነገሮች+ ተመልክተዋል፤
25 እሱ በቃሉ አውሎ ነፋስ ሲያስነሳ፣+
የባሕሩንም ማዕበል ሲያናውጥ አይተዋል።
26 ወደ ሰማይ ይወጣሉ፣
ወደ ጥልቆችም ይወርዳሉ።
እየመጣባቸው ካለው መከራ የተነሳ ሐሞታቸው ፈሰሰ።*
28 በዚህ ጊዜ ከጭንቀታቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤+
እሱም ከደረሰባቸው መከራ ይታደጋቸዋል።
29 አውሎ ነፋሱ እንዲቆም ያደርጋል፤
የባሕሩም ሞገዶች ጸጥ ይላሉ።+
30 ሞገዶቹ ጸጥ ሲሉ ሰዎቹ ሐሴት ያደርጋሉ፤
እሱም ወዳሰቡት ወደብ ይመራቸዋል።
31 ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩና
ለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።+
33 እሱ ወንዞችን ወደ በረሃ፣
የውኃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ መሬት ይለውጣል፤+
34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሳ
ፍሬያማዋን አገር ጨዋማ የሆነ ጠፍ ምድር ያደርጋታል።+
35 በረሃውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣
ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጭ ያደርጋል።+
38 እሱ ይባርካቸዋል፤ እነሱም እጅግ ይበዛሉ፤
የከብቶቻቸው ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።+
39 ሆኖም ከደረሰባቸው ጭቆና፣ መከራና ሐዘን የተነሳ
ዳግመኛ ቁጥራቸው ተመናመነ፤ ተዋረዱም።
40 በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤
መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።+