የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ቆሮንቶስ 9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለጋሶች እንዲሆኑ የተሰጠ ማበረታቻ (1-15)

        • ‘አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል’ (7)

2 ቆሮንቶስ 9:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እርዳታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:26፤ 1ቆሮ 16:1፤ 2ቆሮ 9:12

2 ቆሮንቶስ 9:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ 22:9፤ መክ 11:1፤ ሉቃስ 6:38

2 ቆሮንቶስ 9:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ያለፍላጎቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:29፤ ምሳሌ 11:25፤ ሥራ 20:35፤ ዕብ 13:16
  • +ዘዳ 15:7, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 155

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 55

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 196

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2013፣ ገጽ 13

    12/1/2012፣ ገጽ 5

    11/1/1998፣ ገጽ 26

    ንቁ!፣

    5/2008፣ ገጽ 21

2 ቆሮንቶስ 9:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 28:27፤ ሚል 3:10፤ ፊልጵ 4:18, 19

2 ቆሮንቶስ 9:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በልግስና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 112:9

2 ቆሮንቶስ 9:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 210-212

2 ቆሮንቶስ 9:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እርዳታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:26, 27፤ 2ቆሮ 8:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 210-216

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2000፣ ገጽ 11-12

2 ቆሮንቶስ 9:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:16፤ ዕብ 13:16፤ ያዕ 1:27፤ 1ዮሐ 3:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 210-212

2 ቆሮንቶስ 9:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 210-212, 216-217

2 ቆሮንቶስ 9:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 2 2017፣ ገጽ 4

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2016፣ ገጽ 12-13

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2015፣ ገጽ 14

    12/1/1993፣ ገጽ 28

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 210-212

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ቆሮ. 9:1ሮም 15:26፤ 1ቆሮ 16:1፤ 2ቆሮ 9:12
2 ቆሮ. 9:6ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ 22:9፤ መክ 11:1፤ ሉቃስ 6:38
2 ቆሮ. 9:7ዘፀ 22:29፤ ምሳሌ 11:25፤ ሥራ 20:35፤ ዕብ 13:16
2 ቆሮ. 9:7ዘዳ 15:7, 10
2 ቆሮ. 9:8ምሳሌ 28:27፤ ሚል 3:10፤ ፊልጵ 4:18, 19
2 ቆሮ. 9:9መዝ 112:9
2 ቆሮ. 9:12ሮም 15:26, 27፤ 2ቆሮ 8:14
2 ቆሮ. 9:13ማቴ 5:16፤ ዕብ 13:16፤ ያዕ 1:27፤ 1ዮሐ 3:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ቆሮንቶስ 9:1-15

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ

9 ለቅዱሳን የሚደረገውን አገልግሎት* በተመለከተ+ ልጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ 2 እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል። 3 ይሁንና በዚህ ረገድ በእናንተ ላይ ያለን ትምክህት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር አስቀድሞ ስለ እናንተ እንደተናገርኩት ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ ወንድሞችን እልካለሁ። 4 አለዚያ የመቄዶንያ ወንድሞች ከእኔ ጋር መጥተው ዝግጁ ሳትሆኑ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም በእናንተ በመተማመናችን እናፍራለን። 5 ስለዚህ ቀደም ሲል ልትሰጡ ቃል የገባችሁትን የልግስና ስጦታ አስቀድመው ያዘጋጁ ዘንድ ወንድሞች ቀደም ብለው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማበረታታት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እንዲህ ከሆነ ስጦታው ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል፤ ይህ ደግሞ ስጦታ የሰጣችሁት አስገድደናችሁ ሳይሆን በልግስና እንደሆነ ያሳያል።

6 ይሁንና ጥቂት የሚዘራ ሁሉ ጥቂት ያጭዳል፤ በብዛት የሚዘራ ሁሉ ደግሞ በብዛት ያጭዳል።+ 7 አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ+ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው* ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።+

8 በተጨማሪም ምንጊዜም የሚያስፈልጋችሁ ነገር በበቂ ሁኔታ እንዲኖራችሁ እንዲሁም መልካም ሥራን ሁሉ ለመሥራት የሚያስችላችሁን ነገር በብዛት እንድታገኙ አምላክ ጸጋውን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።+ 9 (ይህም “በብዛት* አከፋፈለ፤ ለድሆችም ሰጠ። ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+ 10 እንግዲህ ለዘሪ ዘርን፣ ለመብል እህልን አትረፍርፎ የሚሰጠው እሱ የምትዘሩትን ዘር አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ እንዲሁም የጽድቃችሁን ፍሬ ያበዛላችኋል።) 11 በሁሉም መንገድ በልግስና መስጠት እንድትችሉ አምላክ አትረፍርፎ ይባርካችኋል፤ እኛ በምናከናውነው ሥራ የተነሳ እንዲህ ያለው ልግስና ሰዎች ለአምላክ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያነሳሳቸዋል፤ 12 ምክንያቱም ይህ የምታከናውኑት ሕዝባዊ አገልግሎት* ቅዱሳን የሚያስፈልጓቸው ነገሮች በሚገባ እንዲሟሉላቸው+ ከማድረጉም በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ለአምላክ ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋል። 13 በዚህ የእርዳታ አገልግሎት አማካኝነት የሚያዩት ማስረጃ አምላክን እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል፤ ምክንያቱም እናንተ በይፋ ለምታውጁት ስለ ክርስቶስ ለሚገልጸው ምሥራች ተገዢዎች ናችሁ፤ እንዲሁም ለእነሱም ሆነ ለሁሉም በምታደርጉት መዋጮ ለጋሶች ናችሁ።+ 14 ደግሞም አምላክ ከሰጣችሁ የላቀ ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ምልጃ እያቀረቡ ለእናንተ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ።

15 በቃላት ሊገለጽ ለማይችለው ነፃ ስጦታው አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ