የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዮሐንስ 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዮሐንስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ (1-14)

      • ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደሚወደው አረጋገጠለት (15-19)

        • “ግልገሎቼን መግብ” (17)

      • ኢየሱስ የሚወደው ደቀ መዝሙር ወደፊት የሚያጋጥመው ሁኔታ (20-23)

      • መደምደሚያ (24, 25)

ዮሐንስ 21:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ማቴ 4:18 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

  • *

    ወይም “ታየ።”

ዮሐንስ 21:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መንትያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:16፤ 20:24
  • +ዮሐ 1:45
  • +ማቴ 4:21

ዮሐንስ 21:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 5:4, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 202-203

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 25

ዮሐንስ 21:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 24:15, 16፤ ዮሐ 20:11, 14

ዮሐንስ 21:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዓሣ።”

ዮሐንስ 21:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 5:4, 6

ዮሐንስ 21:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከውስጥ በለበሳት ልብስ ብቻ።”

  • *

    ወይም “ታጠቀና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:23፤ 19:26፤ 20:2

ዮሐንስ 21:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “200 ክንድ ገደማ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ዮሐንስ 21:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2009፣ ገጽ 20

ዮሐንስ 21:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 20:19, 26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/1991፣ ገጽ 8

ዮሐንስ 21:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 22:32፤ ሥራ 20:28፤ 1ጴጥ 5:2, 3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 30

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2017፣ ገጽ 13

    5/2017፣ ገጽ 22-23, 26

    ከመጽሐፍ ቅዱስ ምን ትማራለህ?፣ ገጽ 215

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 204

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 25-26

    6/1/2008፣ ገጽ 23

    4/15/2008፣ ገጽ 32

    4/15/2007፣ ገጽ 25

    4/15/1991፣ ገጽ 8

ዮሐንስ 21:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 1:15፤ ዕብ 13:20፤ 1ጴጥ 2:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 204

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 25-26

    6/1/2008፣ ገጽ 23

    4/15/2007፣ ገጽ 25

ዮሐንስ 21:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 10:14, 15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2013፣ ገጽ 16

    4/1/2010፣ ገጽ 25-26

    6/1/2008፣ ገጽ 23

    4/15/2007፣ ገጽ 25

    4/15/1991፣ ገጽ 8

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 204

ዮሐንስ 21:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/1991፣ ገጽ 8

ዮሐንስ 21:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 19:28፤ ዮሐ 12:26፤ ራእይ 14:4

ዮሐንስ 21:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:23፤ 20:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2015፣ ገጽ 15

ዮሐንስ 21:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308

ዮሐንስ 21:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 308, 313

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2005፣ ገጽ 13

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 16፣ ገጽ 12

ዮሐንስ 21:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:23፤ 19:26፤ 20:2፤ 21:7

ዮሐንስ 21:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 20:30, 31

ተዛማጅ ሐሳብ

ዮሐ. 21:2ዮሐ 11:16፤ 20:24
ዮሐ. 21:2ዮሐ 1:45
ዮሐ. 21:2ማቴ 4:21
ዮሐ. 21:3ሉቃስ 5:4, 5
ዮሐ. 21:4ሉቃስ 24:15, 16፤ ዮሐ 20:11, 14
ዮሐ. 21:6ሉቃስ 5:4, 6
ዮሐ. 21:7ዮሐ 13:23፤ 19:26፤ 20:2
ዮሐ. 21:14ዮሐ 20:19, 26
ዮሐ. 21:15ሉቃስ 22:32፤ ሥራ 20:28፤ 1ጴጥ 5:2, 3
ዮሐ. 21:16ሥራ 1:15፤ ዕብ 13:20፤ 1ጴጥ 2:25
ዮሐ. 21:17ዮሐ 10:14, 15
ዮሐ. 21:19ማቴ 19:28፤ ዮሐ 12:26፤ ራእይ 14:4
ዮሐ. 21:20ዮሐ 13:23፤ 20:2
ዮሐ. 21:24ዮሐ 13:23፤ 19:26፤ 20:2፤ 21:7
ዮሐ. 21:25ዮሐ 20:30, 31
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዮሐንስ 21:1-25

የዮሐንስ ወንጌል

21 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ* ባሕር እንደገና ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ።* የተገለጠውም በዚህ መንገድ ነበር፤ 2 ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ፣+ የገሊላ ቃና ሰው የሆነው ናትናኤል፣+ የዘብዴዎስ ልጆችና+ ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ። 3 ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነሱም “እኛም አብረንህ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተው ሄዱና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፤ በዚያ ሌሊት ግን አንድም ዓሣ አልያዙም።+

4 ይሁን እንጂ ጎህ ሲቀድ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም ነበር።+ 5 ከዚያም ኢየሱስ “ልጆቼ፣ የሚበላ ነገር* አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “የለንም!” ብለው መለሱለት። 6 እሱም “መረቡን ከጀልባዋ በስተ ቀኝ ጣሉት፤ ዓሣ ታገኛላችሁ” አላቸው። እነሱም መረቡን ጣሉ፤ ከዓሣውም ብዛት የተነሳ መረቡን መጎተት አቃታቸው።+ 7 በዚህ ጊዜ፣ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር+ ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን ሲሰማ ከወገቡ በላይ ራቁቱን* ስለነበር መደረቢያውን ለበሰና* ዘሎ ባሕሩ ውስጥ ገባ። 8 ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከባሕሩ ዳርቻ ብዙም ሳይርቁ 90 ሜትር ገደማ* ርቀት ላይ ስለነበሩ በዓሣዎች የተሞላውን መረብ እየጎተቱ በትንሿ ጀልባ መጡ።

9 ወደ ባሕሩ ዳርቻ በደረሱ ጊዜ በከሰል ፍም ላይ የተቀመጠ ዓሣ እንዲሁም ዳቦ አዩ። 10 ኢየሱስ “አሁን ከያዛችሁት ዓሣ የተወሰነ አምጡ” አላቸው። 11 ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጀልባዋ ላይ ወጥቶ በትላልቅ ዓሣዎች የተሞላውን መረብ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ጎተተው፤ የዓሣዎቹም ብዛት 153 ነበር። መረቡ ይህን ያህል ብዙ ዓሣ ቢይዝም አልተቀደደም። 12 ኢየሱስ “ኑ፣ ቁርሳችሁን ብሉ” አላቸው። ጌታ መሆኑን አውቀው ስለነበር ከደቀ መዛሙርቱ መካከል “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። 13 ኢየሱስም መጥቶ ዳቦውን አነሳና ሰጣቸው፤ ዓሣውንም አንስቶ እንዲሁ አደረገ። 14 ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር።+

15 ቁርስ በልተው ከጨረሱም በኋላ ኢየሱስ፣ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን መግብ” አለው።+ 16 ደግሞም ለሁለተኛ ጊዜ “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ግልገሎቼን ጠብቅ” አለው።+ 17 ለሦስተኛ ጊዜም “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ በጣም ትወደኛለህ?” አለው። ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ “በጣም ትወደኛለህ?” ብሎ ስለጠየቀው አዘነ። በመሆኑም “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ግልገሎቼን መግብ።+ 18 እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት ሳለህ ራስህ ለብሰህ ወደፈለግክበት ቦታ ትሄድ ነበር። ስታረጅ ግን እጅህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያለብስሃል፤ ወደማትፈልግበትም ቦታ ይወስድሃል።” 19 ይህን የተናገረው፣ ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት አምላክን እንደሚያከብር ለማመልከት ነበር። ይህን ካለ በኋላ “እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው።+

20 ጴጥሮስ ዞር ሲል ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር+ ሲከተላቸው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር ራት በበሉ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ፣ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው። 21 ጴጥሮስም ባየው ጊዜ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ ይህስ ሰው ምን ይሆናል?” አለው። 22 ኢየሱስም “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ? አንተ እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። 23 በመሆኑም ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚል ወሬ በወንድሞች መካከል ተሰራጨ። ይሁንና ኢየሱስ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ?” አለው እንጂ አይሞትም አላለውም።

24 ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረውና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤+ እሱ የሚሰጠው ምሥክርነትም እውነት እንደሆነ እናውቃለን።

25 እርግጥ ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮችም አሉ፤ እነዚህ ሁሉ በዝርዝር ቢጻፉ ዓለም ራሱ የተጻፉትን ጥቅልሎች ለማስቀመጥ የሚበቃ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ