የማቴዎስ ወንጌል
1 የዳዊት ልጅ፣+ የአብርሃም ልጅ+ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን* ታሪክ* የያዘ መጽሐፍ፦
ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤+
ያዕቆብ ይሁዳንና+ ወንድሞቹን ወለደ፤
ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤+
ኤስሮን ራምን ወለደ፤+
4 ራም አሚናዳብን ወለደ፤
አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤+
ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤
ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤+
ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤+
ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ፤+
ሮብዓም አቢያህን ወለደ፤
አቢያህ አሳን ወለደ፤+
ኢዮሳፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤+
ኢዮራም ዖዝያን ወለደ፤
ኢዮዓታም አካዝን ወለደ፤+
አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤+
ምናሴ አምዖንን ወለደ፤+
አምዖን ኢዮስያስን ወለደ፤+
11 ኢዮስያስ+ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በተጋዙበት ዘመን+ ኢኮንያንን+ እና ወንድሞቹን ወለደ።
12 ወደ ባቢሎን ከተጋዙ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤
ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤+
13 ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤
አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤
ኤልያቄም አዞርን ወለደ፤
14 አዞር ሳዶቅን ወለደ፤
ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤
አኪም ኤልዩድን ወለደ፤
15 ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤
አልዓዛር ማታንን ወለደ፤
ማታን ያዕቆብን ወለደ፤
16 ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደችው የማርያም ባል ነበር።+
17 ስለዚህ ጠቅላላው ትውልድ፣ ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ፣ ከዳዊት አንስቶ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን እስከተጋዙበት ጊዜ ድረስ 14 ትውልድ እንዲሁም ወደ ባቢሎን ከተጋዙበት ዘመን እስከ ክርስቶስ ድረስ 14 ትውልድ ነው።
18 ይሁንና ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፦ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ በነበረበት ጊዜ፣ አብረው መኖር ከመጀመራቸው በፊት በመንፈስ ቅዱስ* ፀንሳ ተገኘች።+ 19 ይሁን እንጂ ባሏ* ዮሴፍ ጻድቅ ስለሆነና በይፋ ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊፈታት አሰበ።+ 20 ሆኖም ይህን ለማድረግ አስቦ ሳለ የይሖዋ* መልአክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፦ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ሚስትህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ+ እሷን ወደ ቤት ለመውሰድ አትፍራ። 21 ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እሱንም ኢየሱስ* ብለህ ትጠራዋለህ፤+ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና።”+ 22 ይህ ሁሉ የሆነው ይሖዋ* በነቢዩ በኩል እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ 23 “እነሆ! ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል+ ይሉታል”፤ ትርጉሙም “አምላክ ከእኛ ጋር ነው”+ ማለት ነው።
24 ከዚያም ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፤ የይሖዋ* መልአክ ባዘዘውም መሠረት ሚስቱን ወደ ቤቱ ወሰዳት። 25 ሆኖም ልጁን እስክትወልድ ድረስ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም፤+ ልጁንም ኢየሱስ ብሎ ጠራው።+