የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 29
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • ለቤተ መቅደሱ ግንባታ የተሰጡ መዋጮዎች (1-9)

      • ዳዊት ያቀረበው ጸሎት (10-19)

      • ሕዝቡ ተደሰተ፤ የሰለሞን ንግሥና (20-25)

      • ዳዊት ሞተ (26-30)

1 ዜና መዋዕል 29:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አልበሰለም።”

  • *

    ወይም “ግንቡ፤ ቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:5
  • +1ነገ 3:7
  • +2ዜና 2:4

1 ዜና መዋዕል 29:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 22:3, 16
  • +1ዜና 22:4, 14

1 ዜና መዋዕል 29:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 26:8፤ 27:4፤ 122:1
  • +1ዜና 21:24

1 ዜና መዋዕል 29:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 28:16

1 ዜና መዋዕል 29:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 35:5

1 ዜና መዋዕል 29:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:25
  • +1ዜና 27:25, 29, 31

1 ዜና መዋዕል 29:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዳሪክ የፋርስ የወርቅ ሳንቲም ነበር። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1651, 1730

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2009፣ ገጽ 30

1 ዜና መዋዕል 29:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 6:1
  • +1ዜና 26:22

1 ዜና መዋዕል 29:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 9:7

1 ዜና መዋዕል 29:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ክብር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 145:3፤ 1ጢሞ 1:17
  • +ራእይ 5:13
  • +1ዜና 16:27፤ መዝ 8:1
  • +መዝ 24:1፤ ኢሳ 42:5
  • +መዝ 103:19፤ ማቴ 6:10

1 ዜና መዋዕል 29:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:18፤ ምሳሌ 10:22፤ ፊልጵ 4:19
  • +2ዜና 20:6
  • +ኢሳ 40:26
  • +ዘዳ 3:24፤ ኤፌ 1:19፤ ራእይ 15:3
  • +2ዜና 1:11, 12
  • +2ዜና 16:9፤ መዝ 18:32፤ ኢሳ 40:29

1 ዜና መዋዕል 29:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2018፣ ገጽ 18

1 ዜና መዋዕል 29:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:23፤ ዕብ 11:13
  • +ኢዮብ 14:1, 2፤ ያዕ 4:13, 14

1 ዜና መዋዕል 29:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በታማኝነት፤ በቅንነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:9
  • +ምሳሌ 11:20፤ 15:8፤ ዕብ 1:9

1 ዜና መዋዕል 29:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 10:17፤ 86:11

1 ዜና መዋዕል 29:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሙሉ በሙሉ ለአንተ ያደረ።”

  • *

    ወይም “ግንብ፤ ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 6:12
  • +ማር 12:30
  • +1ዜና 22:14

1 ዜና መዋዕል 29:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 1:3
  • +ዘሌ 23:12, 13፤ ዘኁ 15:5
  • +1ነገ 8:63, 64

1 ዜና መዋዕል 29:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:7፤ 2ዜና 7:10፤ ነህ 8:12
  • +1ነገ 1:38-40፤ 1ዜና 23:1
  • +1ነገ 2:35

1 ዜና መዋዕል 29:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 32

1 ዜና መዋዕል 29:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 22:17
  • +1ዜና 28:1
  • +1ዜና 3:1-9

1 ዜና መዋዕል 29:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 3:12፤ 2ዜና 1:1, 12፤ መክ 2:9

1 ዜና መዋዕል 29:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:11
  • +2ሳሙ 5:4, 5

1 ዜና መዋዕል 29:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቀናት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:1
  • +1ነገ 2:10-12

1 ዜና መዋዕል 29:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የዕብራይስጡ ቃል በአምላክ እርዳታ መለኮታዊውን ፈቃድ ማስተዋል የቻለን ሰው ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:2፤ 12:1
  • +1ዜና 21:9, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2009፣ ገጽ 32

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 29:11ዜና 28:5
1 ዜና 29:11ነገ 3:7
1 ዜና 29:12ዜና 2:4
1 ዜና 29:21ዜና 22:3, 16
1 ዜና 29:21ዜና 22:4, 14
1 ዜና 29:3መዝ 26:8፤ 27:4፤ 122:1
1 ዜና 29:31ዜና 21:24
1 ዜና 29:4ኢዮብ 28:16
1 ዜና 29:5ዘፀ 35:5
1 ዜና 29:6ዘፀ 18:25
1 ዜና 29:61ዜና 27:25, 29, 31
1 ዜና 29:81ዜና 6:1
1 ዜና 29:81ዜና 26:22
1 ዜና 29:92ቆሮ 9:7
1 ዜና 29:11መዝ 145:3፤ 1ጢሞ 1:17
1 ዜና 29:11ራእይ 5:13
1 ዜና 29:111ዜና 16:27፤ መዝ 8:1
1 ዜና 29:11መዝ 24:1፤ ኢሳ 42:5
1 ዜና 29:11መዝ 103:19፤ ማቴ 6:10
1 ዜና 29:12ዘዳ 3:24፤ ኤፌ 1:19፤ ራእይ 15:3
1 ዜና 29:122ዜና 1:11, 12
1 ዜና 29:122ዜና 16:9፤ መዝ 18:32፤ ኢሳ 40:29
1 ዜና 29:12ዘዳ 8:18፤ ምሳሌ 10:22፤ ፊልጵ 4:19
1 ዜና 29:122ዜና 20:6
1 ዜና 29:12ኢሳ 40:26
1 ዜና 29:15ዘሌ 25:23፤ ዕብ 11:13
1 ዜና 29:15ኢዮብ 14:1, 2፤ ያዕ 4:13, 14
1 ዜና 29:171ዜና 28:9
1 ዜና 29:17ምሳሌ 11:20፤ 15:8፤ ዕብ 1:9
1 ዜና 29:18መዝ 10:17፤ 86:11
1 ዜና 29:191ነገ 6:12
1 ዜና 29:19ማር 12:30
1 ዜና 29:191ዜና 22:14
1 ዜና 29:21ዘሌ 1:3
1 ዜና 29:21ዘሌ 23:12, 13፤ ዘኁ 15:5
1 ዜና 29:211ነገ 8:63, 64
1 ዜና 29:22ዘዳ 12:7፤ 2ዜና 7:10፤ ነህ 8:12
1 ዜና 29:221ነገ 1:38-40፤ 1ዜና 23:1
1 ዜና 29:221ነገ 2:35
1 ዜና 29:231ዜና 28:5
1 ዜና 29:241ዜና 22:17
1 ዜና 29:241ዜና 28:1
1 ዜና 29:241ዜና 3:1-9
1 ዜና 29:251ነገ 3:12፤ 2ዜና 1:1, 12፤ መክ 2:9
1 ዜና 29:272ሳሙ 2:11
1 ዜና 29:272ሳሙ 5:4, 5
1 ዜና 29:281ነገ 1:1
1 ዜና 29:281ነገ 2:10-12
1 ዜና 29:292ሳሙ 7:2፤ 12:1
1 ዜና 29:291ዜና 21:9, 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 29:1-30

አንደኛ ዜና መዋዕል

29 ንጉሥ ዳዊትም ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “አምላክ የመረጠው+ ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤*+ ሥራው ደግሞ ታላቅ ነው፤ ቤተ መቅደሱ* የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ አምላክ ነውና።+ 2 እኔም አቅሜ በፈቀደው መጠን ለአምላኬ ቤት በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ በመዳብ ለሚሠራው መዳብ፣ በብረት ለሚሠራው ብረትና+ በሳንቃ ለሚሠራው ሳንቃ+ እንዲሁም ኦኒክስ ድንጋዮች፣ በማያያዣ የሚጣበቁ ድንጋዮች፣ እንደ ጌጥ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ሕብር ያላቸው ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዓይነት የከበረ ድንጋይና የአልባስጥሮስ ድንጋይ በብዛት አዘጋጅቻለሁ። 3 ከዚህም በላይ ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር+ የተነሳ ለቅዱሱ ቤት አስቀድሞ ካዘጋጀሁት በተጨማሪ የግል ሀብቴ+ የሆነውን ወርቅና ብርም ለአምላኬ ቤት እሰጣለሁ፤ 4 ከዚህም ሌላ የቤቶቹን ግድግዳ ለመለበጥ 3,000 ታላንት* የኦፊር ወርቅና+ 7,000 ታላንት የተጣራ ብር፣ 5 በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ለሚሠሩትም ሥራ ሁሉ የሚያስፈልገውን እሰጣለሁ። ታዲያ ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጁ ይዞ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ማን ነው?”+

6 በመሆኑም የአባቶች ቤቶች አለቆች፣ የእስራኤል ነገዶች አለቆች፣ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆችና+ የንጉሡን ጉዳይ የሚያስፈጽሙት አለቆች+ በፈቃደኝነት ቀረቡ። 7 ደግሞም ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት የሚውል 5,000 ታላንት ወርቅ፣ 10,000 ዳሪክ፣* 10,000 ታላንት ብር፣ 18,000 ታላንት መዳብና 100,000 ታላንት ብረት ሰጡ። 8 የከበሩ ድንጋዮች ያለው ሰው ሁሉ ጌድሶናዊው+ የሂኤል+ በኃላፊነት ለሚያስተዳድረው በይሖዋ ቤት ላለው ግምጃ ቤት ሰጠ። 9 ሕዝቡ በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና፤+ ንጉሥ ዳዊትም እጅግ ደስ አለው።

10 ከዚያም ዳዊት በጉባኤው ሁሉ ፊት ይሖዋን አወደሰ። እንዲህም አለ፦ “የአባታችን የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ውዳሴ ይድረስህ። 11 ይሖዋ ሆይ፣ ታላቅነት፣+ ኃያልነት፣+ ውበት፣ ግርማና ሞገስ*+ የአንተ ነው፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነው።+ ይሖዋ ሆይ፣ መንግሥት የአንተ ነው።+ ከሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ያልክ ራስ ነህ። 12 ሀብትና ክብር ከአንተ ነው፤+ አንተም ሁሉንም ነገር ትገዛለህ፤+ ኃይልና+ ብርታት+ በእጅህ ነው፤ እጅህ ሁሉንም ታላቅ ማድረግና+ ለሁሉም ብርታት መስጠት ይችላል።+ 13 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ እናመሰግንሃለን፤ ውብ የሆነውን ስምህንም እናወድሳለን።

14 “ይሁንና በፈቃደኝነት ተነሳስተን እንዲህ ያለ መባ ማቅረብ እንችል ዘንድ እኔም ሆንኩ ሕዝቤ ማን ነን? ሁሉም ነገር የተገኘው ከአንተ ነውና፤ የሰጠንህም ከገዛ እጅህ የተቀበልነውን ነው። 15 እንደ አባቶቻችን ሁሉ እኛም በፊትህ የባዕድ አገር ሰዎችና ሰፋሪዎች ነንና።+ የሕይወት ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤+ ተስፋም የለውም። 16 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ለቅዱስ ስምህ ቤት ለመሥራት ያዘጋጀነው ይህ ሁሉ ሀብት የተገኘው ከገዛ እጅህ ነው፤ ሁሉም የአንተ ነው። 17 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ልብን እንደምትመረምርና+ በንጹሕ አቋም * ደስ እንደምትሰኝ+ በሚገባ አውቃለሁ። እኔ በልቤ ቅንነት፣ በፈቃደኝነት ተነሳስቼ ይህን ሁሉ ነገር ሰጥቻለሁ፤ ደግሞም እዚህ የተገኘው ሕዝብህ በፈቃደኝነት ተነሳስቶ ለአንተ መባ ሲያቀርብ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። 18 የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ እንዲህ ያለ የፈቃደኝነት መንፈስና ዝንባሌ ይዞ ለዘላለም እንዲኖርና በሙሉ ልቡ እንዲያገለግልህ እርዳው።+ 19 ልጄ ሰለሞንም ትእዛዛትህን፣ ማሳሰቢያዎችህንና ሥርዓቶችህን እንዲጠብቅ+ ሙሉ* ልብ ስጠው፤+ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንዲያደርግና እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ቤተ መቅደስ* እንዲገነባ እርዳው።”+

20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ “አሁን፣ አምላካችሁን ይሖዋን አወድሱ” አለ። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን አወደሱ፤ ለይሖዋና ለንጉሡም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። 21 በማግስቱም ለይሖዋ መሥዋዕት መሠዋታቸውንና ለይሖዋ የሚቃጠል መባ+ ማቅረባቸውን ቀጠሉ፤ 1,000 ወይፈኖች፣ 1,000 አውራ በጎች፣ 1,000 ተባዕት የበግ ጠቦቶችና የመጠጥ መባዎች+ አቀረቡ፤ ስለ እስራኤል ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።+ 22 በዚያ ዕለት በይሖዋ ፊት በታላቅ ደስታ ይበሉና ይጠጡ ነበር፤+ ደግሞም የዳዊትን ልጅ ሰለሞንን ለሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ በይሖዋም ፊት መሪ አድርገው ቀቡት፤+ ሳዶቅንም ካህን አድርገው ቀቡት።+ 23 ሰለሞንም በአባቱ በዳዊት ፋንታ በይሖዋ ዙፋን+ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተቀመጠ፤ እሱም ተሳካለት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ታዘዙለት። 24 መኳንንቱና+ ኃያላን ተዋጊዎቹ+ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች+ ሁሉ ለንጉሥ ሰለሞን ተገዙለት። 25 ይሖዋም በእስራኤል ሁሉ ፊት ሰለሞንን እጅግ ታላቅ አደረገው፤ ደግሞም በእስራኤል ከእሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላገኙትን ንጉሣዊ ግርማ አጎናጸፈው።+

26 በዚህ መንገድ የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ገዛ፤ 27 በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛበት ጊዜ ርዝመት* 40 ዓመት ነበር። በኬብሮን ለ7 ዓመት፣+ በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ።+ 28 እሱም አስደሳች የሆነ ብዙ ዘመን ኖሮ፣+ ዕድሜ* ጠግቦ እንዲሁም ብዙ ሀብትና ክብር አግኝቶ ሞተ፤ ልጁ ሰለሞንም በእሱ ፋንታ ነገሠ።+ 29 የንጉሥ ዳዊት ታሪክ ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ባለ ራእዩ* ሳሙኤል፣ ነቢዩ ናታንና+ ባለ ራእዩ ጋድ+ ባዘጋጇቸው ጽሑፎች ውስጥ ሰፍሯል፤ 30 በተጨማሪም ስለ ንግሥናውና ስለ ኃያልነቱ ሁሉ እንዲሁም ከእሱ፣ ከእስራኤልና በዙሪያው ካሉ መንግሥታት ሁሉ ጋር በተያያዘ ስለተከናወኑት ነገሮች ተጽፏል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ