የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሰላምታ (1-3)

      • ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የተነሳ አምላክን አመሰገነ (4-9)

      • አንድነታቸውን እንዲጠብቁ የተሰጠ ማሳሰቢያ (10-17)

      • ክርስቶስ፣ የአምላክ ኃይልና ጥበብ (18-25)

      • “የሚኩራራ በይሖዋ ይኩራራ” (26-31)

1 ቆሮንቶስ 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 9:15

1 ቆሮንቶስ 1:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:1
  • +1ቆሮ 6:11፤ ዕብ 9:13, 14
  • +ማቴ 12:18, 21፤ ሥራ 4:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/1994፣ ገጽ 24-25

1 ቆሮንቶስ 1:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 1:9

1 ቆሮንቶስ 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:5

1 ቆሮንቶስ 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 17:29, 30፤ 2ተሰ 1:7፤ 1ጴጥ 1:7

1 ቆሮንቶስ 1:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 4:5፤ 5:5፤ ራእይ 1:10

1 ቆሮንቶስ 1:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተካፋይ እንድትሆኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:9

1 ቆሮንቶስ 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 16:17
  • +ሮም 15:5, 6፤ 2ቆሮ 13:11፤ ኤፌ 4:1, 3፤ ፊልጵ 2:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    6/8/2003፣ ገጽ 24-25

    ማመራመር፣ ገጽ 325

1 ቆሮንቶስ 1:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/1997፣ ገጽ 29

1 ቆሮንቶስ 1:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጴጥሮስ ተብሎም ይጠራል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:24፤ 1ቆሮ 3:4, 5, 21-23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/1996፣ ገጽ 21-22

1 ቆሮንቶስ 1:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:8
  • +ሮም 16:23

1 ቆሮንቶስ 1:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 16:15

1 ቆሮንቶስ 1:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    ወይም “በአፈ ጮሌነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 9:15

1 ቆሮንቶስ 1:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:18፤ 1ቆሮ 2:14
  • +ሮም 1:16

1 ቆሮንቶስ 1:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 29:14

1 ቆሮንቶስ 1:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዚህ ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

  • *

    ሕጉን ጠንቅቀው የተማሩ ሰዎችን ያመለክታል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ማመራመር፣ ገጽ 291

1 ቆሮንቶስ 1:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 2:8
  • +ሉቃስ 10:21
  • +1ቆሮ 2:14፤ 3:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2008፣ ገጽ 26

1 ቆሮንቶስ 1:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 12:38፤ ሉቃስ 11:29

1 ቆሮንቶስ 1:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2012፣ ገጽ 23

    8/15/2010፣ ገጽ 4

    6/15/2003፣ ገጽ 6

    6/15/1999፣ ገጽ 30

1 ቆሮንቶስ 1:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 2:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 87-96

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2015፣ ገጽ 3-7

1 ቆሮንቶስ 1:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 13:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ማመራመር፣ ገጽ 291

1 ቆሮንቶስ 1:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሥጋዊ መንገድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 4:13
  • +ዮሐ 7:48፤ ያዕ 2:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/1994፣ ገጽ 12-13

1 ቆሮንቶስ 1:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 11:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2014፣ ገጽ 24

    8/15/1994፣ ገጽ 12-13

1 ቆሮንቶስ 1:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 2:6

1 ቆሮንቶስ 1:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”

1 ቆሮንቶስ 1:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 10:4፤ 2ቆሮ 5:21
  • +ዮሐ 17:19፤ ዕብ 10:10
  • +ሮም 3:24፤ ቆላ 1:13, 14

1 ቆሮንቶስ 1:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 9:24፤ 2ቆሮ 10:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2005፣ ገጽ 13

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 1:1ሥራ 9:15
1 ቆሮ. 1:2ሥራ 18:1
1 ቆሮ. 1:21ቆሮ 6:11፤ ዕብ 9:13, 14
1 ቆሮ. 1:2ማቴ 12:18, 21፤ ሥራ 4:12
1 ቆሮ. 1:5ቆላ 1:9
1 ቆሮ. 1:6ሥራ 18:5
1 ቆሮ. 1:7ሉቃስ 17:29, 30፤ 2ተሰ 1:7፤ 1ጴጥ 1:7
1 ቆሮ. 1:81ቆሮ 4:5፤ 5:5፤ ራእይ 1:10
1 ቆሮ. 1:9ዘዳ 7:9
1 ቆሮ. 1:10ሮም 15:5, 6፤ 2ቆሮ 13:11፤ ኤፌ 4:1, 3፤ ፊልጵ 2:2
1 ቆሮ. 1:10ሮም 16:17
1 ቆሮ. 1:12ሥራ 18:24፤ 1ቆሮ 3:4, 5, 21-23
1 ቆሮ. 1:14ሥራ 18:8
1 ቆሮ. 1:14ሮም 16:23
1 ቆሮ. 1:161ቆሮ 16:15
1 ቆሮ. 1:17ሥራ 9:15
1 ቆሮ. 1:18ሥራ 17:18፤ 1ቆሮ 2:14
1 ቆሮ. 1:18ሮም 1:16
1 ቆሮ. 1:19ኢሳ 29:14
1 ቆሮ. 1:21ቆላ 2:8
1 ቆሮ. 1:21ሉቃስ 10:21
1 ቆሮ. 1:211ቆሮ 2:14፤ 3:18
1 ቆሮ. 1:22ማቴ 12:38፤ ሉቃስ 11:29
1 ቆሮ. 1:23ሥራ 17:32
1 ቆሮ. 1:24ቆላ 2:3
1 ቆሮ. 1:252ቆሮ 13:4
1 ቆሮ. 1:26ሥራ 4:13
1 ቆሮ. 1:26ዮሐ 7:48፤ ያዕ 2:5
1 ቆሮ. 1:27ማቴ 11:25
1 ቆሮ. 1:281ቆሮ 2:6
1 ቆሮ. 1:30ሮም 10:4፤ 2ቆሮ 5:21
1 ቆሮ. 1:30ዮሐ 17:19፤ ዕብ 10:10
1 ቆሮ. 1:30ሮም 3:24፤ ቆላ 1:13, 14
1 ቆሮ. 1:31ኤር 9:24፤ 2ቆሮ 10:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 1:1-31

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

1 በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ+ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ፣ 2 በቆሮንቶስ ለሚገኘው የአምላክ ጉባኤ+ ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባላችሁ አንድነት ለተቀደሳችሁ፣+ እንዲሁም የእነሱም ሆነ የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም+ በየስፍራው ሆነው ከሚጠሩ ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ፦

3 ከአባታችን ከአምላክና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4 በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ በሰጠው ጸጋ የተነሳ አምላኬን ሁልጊዜ ስለ እናንተ አመሰግናለሁ፤ 5 ምክንያቱም በሁሉም ነገር ይኸውም በመናገር ችሎታ ሁሉና በእውቀት ሁሉ በክርስቶስ በልጽጋችኋል፤+ 6 ደግሞም ስለ ክርስቶስ የተሰጠው ምሥክርነት+ በእናንተ መካከል በሚገባ ሥር ሰዷል፤ 7 ስለዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ ማንኛውም ስጦታ ፈጽሞ አይጎድልባችሁም።+ 8 በተጨማሪም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን+ ከማንኛውም ክስ ነፃ መሆን እንድትችሉ እስከ መጨረሻው ያጸናችኋል። 9 ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ* የጠራችሁ አምላክ ታማኝ ነው።+

10 እንግዲህ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣+ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ+ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አጥብቄ አሳስባችኋለሁ። 11 ወንድሞቼ ሆይ፣ የቀሎኤ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አንዳንዶች በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ ነግረውኛል። 12 ይኸውም እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፣” “እኔ ግን የአጵሎስ+ ነኝ፣” “እኔ ደግሞ የኬፋ* ነኝ፣” “እኔ የክርስቶስ ነኝ” ትላላችሁ። 13 ታዲያ የክርስቶስ ጉባኤ ተከፋፍሏል ማለት ነው? ጳውሎስ ለእናንተ ሲል በእንጨት ላይ ተሰቅሏል እንዴ? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነው? 14 ከቀርስጶስና+ ከጋይዮስ+ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁንም ባለማጥመቄ አምላክን አመሰግናለሁ፤ 15 በመሆኑም ከእናንተ መካከል በእኔ ስም እንደተጠመቀ ሊናገር የሚችል ማንም የለም። 16 እርግጥ የእስጢፋናስን+ ቤተሰብም አጥምቄአለሁ። ከእነዚህ ሌላ ግን ያጠመቅኩት ሰው መኖሩን አላስታውስም። 17 ክርስቶስ የላከኝ እንዳጠምቅ ሳይሆን ምሥራቹን እንዳውጅ ነው፤+ ደግሞም የክርስቶስ የመከራ እንጨት* ከንቱ እንዳይሆን ምሥራቹን የማውጀው በንግግር ጥበብ* አይደለም።

18 ስለ መከራው እንጨት* የሚነገረው መልእክት ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ሞኝነት፣+ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላለነው ለእኛ ግን የአምላክ ኃይል መገለጫ ነው።+ 19 “የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የሊቃውንትንም ማስተዋል ወዲያ እጥላለሁ” ተብሎ ተጽፏልና።+ 20 የዚህ ሥርዓት* ጥበበኞች የት አሉ? ጸሐፍትስ* የት አሉ? ተሟጋቾችስ የት አሉ? አምላክ የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገም? 21 ዓለም በራሱ ጥበብ+ አምላክን ሊያውቀው ስላልቻለ+ አምላክ በጥበቡ፣ እንደ ሞኝነት በሚቆጠረውና+ እየተሰበከ ባለው መልእክት አማካኝነት የሚያምኑትን ሰዎች ለማዳን መርጧል።

22 አይሁዳውያን ተአምራዊ ምልክቶች ማየት ይፈልጋሉ፤+ ግሪካውያን ደግሞ ጥበብን ይሻሉ፤ 23 እኛ ግን በእንጨት ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁዳውያን መሰናክል ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው።+ 24 ይሁን እንጂ ክርስቶስ ለተጠሩት፣ ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን የአምላክ ኃይልና የአምላክ ጥበብ ነው።+ 25 ምክንያቱም የአምላክ ሞኝነት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ የአምላክ ድክመት እንደሆነ ተደርጎ የሚታሰበው ነገር ደግሞ ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።+

26 ወንድሞች፣ ከራሳችሁ ሁኔታ መረዳት እንደምትችሉት በሰብዓዊ አመለካከት* ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፣+ ኃያላን የሆኑ ብዙዎች እንዲሁም ከትልቅ ቤተሰብ የተወለዱ ብዙዎች አልተጠሩም፤+ 27 ከዚህ ይልቅ አምላክ ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱውንም ነገር ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤+ 28 አምላክ በሰዎች ዘንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን ነገር ከንቱ ያደርግ ዘንድ በዚህ ዓለም ዝቅ ተደርጎ የሚታየውንና የተናቀውን ነገር ይኸውም ከንቱ መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ፤+ 29 ይህን ያደረገው ማንም ሰው* በአምላክ ፊት እንዳይኩራራ ነው። 30 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ሊኖራችሁ የቻለው በእሱ ምክንያት ነው፤ ክርስቶስ ደግሞ ለእኛ ከአምላክ የመጣ ጥበብ፣ ጽድቅና+ ቅድስና+ ሆኖልናል፤ እንዲሁም በቤዛው ነፃ አውጥቶናል፤+ 31 ይህም “የሚኩራራ በይሖዋ* ይኩራራ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ