የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የጸሐፍትንና የፈሪሳውያንን አርዓያ አትከተሉ (1-12)

      • ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላቸው! (13-36)

      • ኢየሱስ ስለ ኢየሩሳሌም የተሰማውን ሐዘን ገለጸ (37-39)

ማቴዎስ 23:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 2:7, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2005፣ ገጽ 26-27

ማቴዎስ 23:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሌሎችን ሸክም ለማቅለል ፈቃደኞች አለመሆናቸውን ሊያመለክት ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 11:28
  • +ሉቃስ 11:46

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2005፣ ገጽ 26-27

    10/15/1994፣ ገጽ 18

    4/1/1993፣ ገጽ 29-30

ማቴዎስ 23:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አይሁዳውያን ወንዶች በግንባራቸውና በግራ ክንዳቸው ላይ የሚያስሩት የሕጉን አራት ክፍሎች የያዘ ማኅደር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:1, 2
  • +ዘዳ 6:6, 8
  • +ዘኁ 15:38, 39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 252

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2010፣ ገጽ 13

ማቴዎስ 23:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የተሻለውን መቀመጫ ማግኘት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 12:38, 39፤ ሉቃስ 11:43፤ 14:7, 10፤ 20:46

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 17

ማቴዎስ 23:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መምህር።”

ማቴዎስ 23:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 13:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2018፣ ገጽ 9-10

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 252

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2001፣ ገጽ 14-15

    6/15/2000፣ ገጽ 17-19, 21-22

    7/1/1996፣ ገጽ 30-31

ማቴዎስ 23:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

ማቴዎስ 23:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

    የተደራጀ ሕዝብ፣ ገጽ 13-14

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2007፣ ገጽ 21

ማቴዎስ 23:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 20:26፤ ማር 9:35፤ ሉቃስ 22:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

ማቴዎስ 23:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 16:18
  • +ምሳሌ 29:23፤ ማቴ 18:4፤ ሉቃስ 14:11፤ ሮም 12:3፤ 1ጴጥ 5:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 20

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2012፣ ገጽ 14

ማቴዎስ 23:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 11:52

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2001፣ ገጽ 21

    3/15/1991፣ ገጽ 5

ማቴዎስ 23:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።

ማቴዎስ 23:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:2፤ ሉቃስ 12:56

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2008፣ ገጽ 31

ማቴዎስ 23:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:34, 35
  • +ማቴ 15:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 252-253

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2000፣ ገጽ 19

    3/15/1995፣ ገጽ 25-26

ማቴዎስ 23:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 252-253

ማቴዎስ 23:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:13

ማቴዎስ 23:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 27:30
  • +ሚክ 6:8፤ ዮሐ 7:24
  • +ማቴ 9:13፤ 12:7
  • +ሉቃስ 11:42

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ተከታዬ ሁን፣” ገጽ 103

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2017፣ ገጽ 13-14

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2001፣ ገጽ 22

ማቴዎስ 23:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 15:14
  • +ዘሌ 11:23
  • +ዘሌ 11:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 253

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2002፣ ገጽ 11

ማቴዎስ 23:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዝርፊያና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 7:3, 4
  • +ማር 12:38, 40
  • +ሉቃስ 11:39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2000፣ ገጽ 19

ማቴዎስ 23:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

ማቴዎስ 23:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 12:56
  • +ሉቃስ 11:44፤ ሥራ 23:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/2009፣ ገጽ 15

    10/15/1995፣ ገጽ 29

ማቴዎስ 23:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 16:15

ማቴዎስ 23:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:2
  • +ሉቃስ 11:47

ማቴዎስ 23:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 11:48፤ ሥራ 7:52፤ ዕብ 11:32, 37

ማቴዎስ 23:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 3:7፤ 12:34፤ ሉቃስ 3:7
  • +ማቴ 10:28፤ ሉቃስ 12:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2008፣ ገጽ 7

ማቴዎስ 23:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 11:49-51
  • +ማቴ 13:52
  • +ዮሐ 16:2፤ ሥራ 7:59
  • +ሥራ 5:40፤ 2ቆሮ 11:24
  • +ሉቃስ 21:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2013፣ ገጽ 12-13

ማቴዎስ 23:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:8, 10፤ ዕብ 11:4
  • +2ዜና 24:20-22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

ማቴዎስ 23:36

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/1995፣ ገጽ 12-13

ማቴዎስ 23:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 8:59፤ ዕብ 11:32, 37
  • +ሉቃስ 13:34፤ 19:41, 42

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 6 2016፣ ገጽ 9

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2006፣ ገጽ 19

    6/15/2005፣ ገጽ 19-20

ማቴዎስ 23:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቤተ መቅደሱን ያመለክታል።

  • *

    “ወና ሆኖ ይቀርላችኋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 9:7, 8፤ ኤር 12:7፤ 22:5፤ ማቴ 21:43፤ ሉቃስ 21:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/1996፣ ገጽ 13

ማቴዎስ 23:39

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 118:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 254

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 23:3ሚል 2:7, 8
ማቴ. 23:4ማቴ 11:28
ማቴ. 23:4ሉቃስ 11:46
ማቴ. 23:5ማቴ 6:1, 2
ማቴ. 23:5ዘዳ 6:6, 8
ማቴ. 23:5ዘኁ 15:38, 39
ማቴ. 23:6ማር 12:38, 39፤ ሉቃስ 11:43፤ 14:7, 10፤ 20:46
ማቴ. 23:8ዮሐ 13:13
ማቴ. 23:9ማቴ 6:9
ማቴ. 23:11ማቴ 20:26፤ ማር 9:35፤ ሉቃስ 22:26
ማቴ. 23:12ምሳሌ 16:18
ማቴ. 23:12ምሳሌ 29:23፤ ማቴ 18:4፤ ሉቃስ 14:11፤ ሮም 12:3፤ 1ጴጥ 5:5
ማቴ. 23:13ሉቃስ 11:52
ማቴ. 23:15ማቴ 6:2፤ ሉቃስ 12:56
ማቴ. 23:16ማቴ 5:34, 35
ማቴ. 23:16ማቴ 15:14
ማቴ. 23:211ነገ 8:13
ማቴ. 23:23ዘሌ 27:30
ማቴ. 23:23ሚክ 6:8፤ ዮሐ 7:24
ማቴ. 23:23ማቴ 9:13፤ 12:7
ማቴ. 23:23ሉቃስ 11:42
ማቴ. 23:24ማቴ 15:14
ማቴ. 23:24ዘሌ 11:23
ማቴ. 23:24ዘሌ 11:4
ማቴ. 23:25ማር 7:3, 4
ማቴ. 23:25ማር 12:38, 40
ማቴ. 23:25ሉቃስ 11:39
ማቴ. 23:27ሉቃስ 12:56
ማቴ. 23:27ሉቃስ 11:44፤ ሥራ 23:3
ማቴ. 23:28ሉቃስ 16:15
ማቴ. 23:29ማቴ 6:2
ማቴ. 23:29ሉቃስ 11:47
ማቴ. 23:31ሉቃስ 11:48፤ ሥራ 7:52፤ ዕብ 11:32, 37
ማቴ. 23:33ማቴ 3:7፤ 12:34፤ ሉቃስ 3:7
ማቴ. 23:33ማቴ 10:28፤ ሉቃስ 12:5
ማቴ. 23:34ሉቃስ 11:49-51
ማቴ. 23:34ማቴ 13:52
ማቴ. 23:34ዮሐ 16:2፤ ሥራ 7:59
ማቴ. 23:34ሥራ 5:40፤ 2ቆሮ 11:24
ማቴ. 23:34ሉቃስ 21:12
ማቴ. 23:35ዘፍ 4:8, 10፤ ዕብ 11:4
ማቴ. 23:352ዜና 24:20-22
ማቴ. 23:37ዮሐ 8:59፤ ዕብ 11:32, 37
ማቴ. 23:37ሉቃስ 13:34፤ 19:41, 42
ማቴ. 23:381ነገ 9:7, 8፤ ኤር 12:7፤ 22:5፤ ማቴ 21:43፤ ሉቃስ 21:20
ማቴ. 23:39መዝ 118:26
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 23:1-39

የማቴዎስ ወንጌል

23 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 2 “ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በገዛ ሥልጣናቸው የሙሴን ቦታ ወስደዋል። 3 ስለዚህ የሚነግሯችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ሆኖም የሚናገሩትን በተግባር ስለማያውሉ እነሱ የሚያደርጉትን አታድርጉ።+ 4 ከባድ ሸክም አስረው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤+ እነሱ ግን በጣታቸው እንኳ ለመንካት* ፈቃደኞች አይደሉም።+ 5 ማንኛውንም ነገር የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ብለው ነው፤+ ለምሳሌ ትልቅ ክታብ* ያስራሉ፤+ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ።+ 6 በራት ግብዣ ላይ የክብር ቦታ ማግኘት፣ በምኩራብ ደግሞ ከፊት መቀመጥ* ይወዳሉ፤+ 7 በገበያ ቦታም ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ይፈልጋሉ እንዲሁም ረቢ* ተብለው መጠራት ይሻሉ። 8 እናንተ ግን መምህራችሁ+ አንድ ስለሆነ ረቢ ተብላችሁ አትጠሩ፤ እናንተ ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ። 9 በተጨማሪም አባታችሁ+ አንድ እሱም በሰማይ ያለው ብቻ ስለሆነ በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ። 10 እንዲሁም መሪያችሁ አንድ እሱም ክርስቶስ ስለሆነ መሪ ተብላችሁ አትጠሩ። 11 ይልቁንም ከመካከላችሁ ታላቅ የሆነው የእናንተ አገልጋይ መሆን ይገባዋል።+ 12 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይደረጋል፤+ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ ከፍ ይደረጋል።+

13 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉ ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ ለመግባት የሚመጡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።+ 14 *——

15 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ አንድን ሰው ወደ ይሁዲነት ለመለወጥ በባሕርና በየብስ ስለምትጓዙና ሰውየው በተለወጠ ጊዜ ከእናንተ ይባስ ሁለት እጥፍ ለገሃነም* የተገባ እንዲሆን ስለምታደርጉት ወዮላችሁ!

16 “‘አንድ ሰው በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም አይደለም፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን መሐላውን የመጠበቅ ግዴታ አለበት’+ የምትሉ እናንተ ዕውር መሪዎች+ ወዮላችሁ! 17 እናንተ ሞኞችና ዕውሮች! ለመሆኑ ከወርቁና ወርቁ እንዲቀደስ ካደረገው ቤተ መቅደስ የትኛው ይበልጣል? 18 ደግሞም ‘አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ በመሠዊያው ላይ ባለው መባ ቢምል ግን መሐላውን የመጠበቅ ግዴታ አለበት’ ትላላችሁ። 19 እናንተ ዕውሮች! ለመሆኑ ከመባውና መባው እንዲቀደስ ካደረገው መሠዊያ የትኛው ይበልጣል? 20 ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል ሁሉ በመሠዊያውና በላዩ ላይ ባለው ነገር ሁሉ ይምላል፤ 21 እንዲሁም በቤተ መቅደሱ የሚምል ሁሉ በቤተ መቅደሱና በዚያ በሚኖረው+ ይምላል፤ 22 በሰማይ የሚምል ሁሉ ደግሞ በአምላክ ዙፋንና በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ይምላል።

23 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከኮሰረት፣ ከእንስላልና ከከሙን አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን በሕጉ ውስጥ የሚገኙትን እንደ ፍትሕ፣+ ምሕረትና+ ታማኝነት ያሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ችላ ትላላችሁ። እነዚያን ችላ ማለት ባይኖርባችሁም እነዚህን ነገሮች ማድረጋችሁ አስፈላጊ ነው።+ 24 እናንተ ዕውር መሪዎች!+ ትንኝን+ አጥልላችሁ ታወጣላችሁ፤ ግመልን+ ግን ትውጣላችሁ!

25 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ጽዋውንና ሳህኑን ከውጭ በኩል ታጸዳላችሁ፤+ ውስጡ ግን ስግብግብነትና*+ ራስ ወዳድነት የሞላበት ነው።+ 26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ በመጀመሪያ ጽዋውንና ሳህኑን ከውስጥ በኩል አጽዳ፤ ከዚያ በኋላ ከውጭ በኩልም ንጹሕ ይሆናል።

27 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ ከውጭ አምረው የሚታዩ ከውስጥ ግን በሙታን አፅምና በብዙ ዓይነት ርኩሰት የተሞሉ በኖራ የተቀቡ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!+ 28 እናንተም ከውጭ ስትታዩ ጻድቅ ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በግብዝነትና በዓመፅ የተሞላ ነው።+

29 “እናንተ ግብዞች+ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን፣ የነቢያትን መቃብር ስለምትገነቡና የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ ወዮላችሁ!+ 30 ደግሞም ‘በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር’ ትላላችሁ። 31 በመሆኑም የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሠክራላችሁ።+ 32 እንግዲያው አባቶቻችሁ የጀመሩትን ተግባር ዳር አድርሱ።

33 “እናንተ እባቦች፣ የእፉኝት ልጆች፣+ ከገሃነም* ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?+ 34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ 35 በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም+ ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+ 36 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳሉ።

37 “ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም፣ ነቢያትን የምትገድል! ወደ እሷ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግር!+ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።+ 38 እነሆ፣ ቤታችሁ* ለእናንተ የተተወ ይሆናል።*+ 39 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ‘በይሖዋ* ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!’+ እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ አታዩኝም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ