የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 22
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • ለባልንጀራህ እንስሳ አሳቢነት አሳይ (1-4)

      • ሴት የወንድ ልብስ፣ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበሱ (5)

      • ለእንስሳት አሳቢነት ማሳየት (6, 7)

      • በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ (8)

      • አትቀላቅል (9-11)

      • በልብስህ ላይ ዘርፍ አድርግ (12)

      • የፆታ ጥቃትን አስመልክቶ የተሰጠ ሕግ (13-30)

ዘዳግም 22:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:4

ዘዳግም 22:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 7:12

ዘዳግም 22:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:5፤ ዘሌ 19:18፤ ሉቃስ 10:27፤ ገላ 6:10

ዘዳግም 22:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 52

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2016፣ ገጽ 18

ዘዳግም 22:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:28፤ መዝ 145:9፤ ምሳሌ 12:10፤ ማቴ 10:29

ዘዳግም 22:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:2፤ ሥራ 10:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2013፣ ገጽ 10

    2/1/2001፣ ገጽ 4-5

ዘዳግም 22:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:19

ዘዳግም 22:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 12:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2003፣ ገጽ 32

    11/15/1995፣ ገጽ 31

ዘዳግም 22:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:19

ዘዳግም 22:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 15:38፤ ማቴ 23:2, 5

ዘዳግም 22:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 6

ዘዳግም 22:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:21፤ ዘዳ 1:13፤ 16:18
  • +ዘዳ 25:2፤ ምሳሌ 10:13፤ 19:29

ዘዳግም 22:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 2:16

ዘዳግም 22:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 13:4
  • +ዘሌ 21:9
  • +ዘሌ 11:45፤ 1ቆሮ 5:13

ዘዳግም 22:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 20:3፤ ዘፀ 20:14፤ ዘሌ 20:10፤ 1ቆሮ 6:9, 10, 18

ዘዳግም 22:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:10፤ ዘዳ 5:18፤ 1ተሰ 4:3, 6፤ ዕብ 13:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2019፣ ገጽ 14

ዘዳግም 22:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2019፣ ገጽ 14

ዘዳግም 22:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ ከሚገድል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 4:8፤ ዘኁ 35:20, 21፤ ያዕ 2:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2019፣ ገጽ 14

ዘዳግም 22:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2019፣ ገጽ 14

ዘዳግም 22:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 34:2, 5

ዘዳግም 22:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 34:11, 12፤ ዘፀ 22:16

ዘዳግም 22:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአባቱን ቀሚስ እንዳይገልጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:8፤ 20:11፤ ዘዳ 27:20፤ 1ቆሮ 5:1

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 22:1ዘፀ 23:4
ዘዳ. 22:2ማቴ 7:12
ዘዳ. 22:4ዘፀ 23:5፤ ዘሌ 19:18፤ ሉቃስ 10:27፤ ገላ 6:10
ዘዳ. 22:6ዘሌ 22:28፤ መዝ 145:9፤ ምሳሌ 12:10፤ ማቴ 10:29
ዘዳ. 22:82ሳሙ 11:2፤ ሥራ 10:9
ዘዳ. 22:9ዘሌ 19:19
ዘዳ. 22:10ምሳሌ 12:10
ዘዳ. 22:11ዘሌ 19:19
ዘዳ. 22:12ዘኁ 15:38፤ ማቴ 23:2, 5
ዘዳ. 22:18ዘፀ 18:21፤ ዘዳ 1:13፤ 16:18
ዘዳ. 22:18ዘዳ 25:2፤ ምሳሌ 10:13፤ 19:29
ዘዳ. 22:19ሚል 2:16
ዘዳ. 22:21ዕብ 13:4
ዘዳ. 22:21ዘሌ 21:9
ዘዳ. 22:21ዘሌ 11:45፤ 1ቆሮ 5:13
ዘዳ. 22:22ዘፍ 20:3፤ ዘፀ 20:14፤ ዘሌ 20:10፤ 1ቆሮ 6:9, 10, 18
ዘዳ. 22:24ዘሌ 20:10፤ ዘዳ 5:18፤ 1ተሰ 4:3, 6፤ ዕብ 13:4
ዘዳ. 22:26ዘፍ 4:8፤ ዘኁ 35:20, 21፤ ያዕ 2:11
ዘዳ. 22:28ዘፍ 34:2, 5
ዘዳ. 22:29ዘፍ 34:11, 12፤ ዘፀ 22:16
ዘዳ. 22:30ዘሌ 18:8፤ 20:11፤ ዘዳ 27:20፤ 1ቆሮ 5:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 22:1-30

ዘዳግም

22 “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ካየህ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ።+ ከዚህ ይልቅ ወደ ወንድምህ መልሰህ ልትወስደው ይገባል። 2 ሆኖም ወንድምህ በአቅራቢያህ የማይኖር ወይም እሱን የማታውቀው ከሆነ እንስሳውን ወደ ቤትህ አምጣው፤ ወንድምህ እሱን ፈልጎ እስኪመጣም ድረስ አንተ ጋ ይቆይ። ከዚያም መልስለት።+ 3 አህያውንም ሆነ ልብሱን ወይም ወንድምህ ጠፍቶበት ያገኘኸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እንዲሁ ማድረግ ይኖርብሃል። አይተህ ዝም ብለህ ማለፍ የለብህም።

4 “የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ። ከዚህ ይልቅ እንስሳው ተነስቶ እንዲቆም በማድረግ ሰውየውን ልትረዳው ይገባል።+

5 “ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበስ። ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው።

6 “መንገድ ላይ ስትሄድ ጫጩቶች ወይም እንቁላሎች ያሉበት የወፍ ጎጆ፣ ዛፍ ላይ ወይም መሬት ላይ ብታገኝና እናትየው ጫጩቶቹን ወይም እንቁላሎቹን ታቅፋ ቢሆን እናትየውን ከጫጩቶቿ ጋር አብረህ አትውሰድ።+ 7 እናትየውን ልቀቃት፤ ጫጩቶቹን ግን መውሰድ ትችላለህ። ይህን የምታደርገው መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህ እንዲረዝም ነው።

8 “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ አንድ ሰው ከጣሪያህ ላይ ወድቆ በቤትህ ላይ የደም ዕዳ እንዳታመጣ በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ።+

9 “በወይን እርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ።+ እንዲህ ካደረግክ ከዘራኸው ዘር የሚገኘው ምርትም ሆነ የወይን እርሻህ ምርት በሙሉ ተወርሶ ለቤተ መቅደሱ ገቢ ይደረጋል።

10 “በሬና አህያ አንድ ላይ ጠምደህ አትረስ።+

11 “ከሱፍና ከበፍታ ተቀላቅሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።+

12 “በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱም ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።+

13 “አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ከእሷ ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ቢጠላት፣ 14 መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ ቢከሳትና ‘ይህችን ሴት አግብቼ ነበር፤ ሆኖም ከእሷ ጋር ግንኙነት ስፈጽም የድንግልናዋን ማስረጃ አላገኘሁም’ በማለት መጥፎ ስም ቢሰጣት 15 የልጅቷ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ይምጡ። 16 የልጅቷም አባት ሽማግሌዎቹን እንዲህ ይበላቸው፦ ‘ልጄን ለዚህ ሰው ድሬለት ነበር፤ እሱ ግን ጠላት፤ 17 እንዲሁም “ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም” በማለት መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ እየከሰሳት ነው። እንግዲህ የልጄ የድንግልና ማስረጃ ይኸውላችሁ።’ እነሱም ልብሱን በከተማዋ ሽማግሌዎች ፊት ይዘርጉት። 18 የዚያች ከተማ ሽማግሌዎችም+ ሰውየውን ወስደው ይቅጡት።+ 19 እነሱም 100 የብር ሰቅል* ያስከፍሉታል፤ ከዚያም ገንዘቡን ለልጅቷ አባት ይስጡት፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የአንዲትን እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷል፤+ እሷም ሚስቱ ሆና ትኖራለች። በሕይወት ዘመኑም ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም።

20 “ሆኖም ክሱ እውነት ከሆነና ልጅቷ ድንግል እንደነበረች የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካልተገኘ 21 ልጅቷን ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያውጧት፤ በአባቷ ቤት የፆታ ብልግና በመፈጸም በእስራኤል ውስጥ አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸመች+ የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+

22 “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።

23 “አንድ ሰው ለሌላ ሰው የታጨችን አንዲት ድንግል ከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእሷ ጋር ቢተኛ 24 ልጅቷ በከተማው ውስጥ ስላልጮኸች፣ ሰውየው ደግሞ የባልንጀራውን ሚስት ስላዋረደ ሁለቱንም ወደ ከተማዋ በር አውጥታችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።

25 “ይሁንና ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ያገኛት ሜዳ ላይ ቢሆንና በጉልበት አስገድዶ አብሯት ቢተኛ እሱ ብቻ ይገደል፤ 26 በልጅቷ ላይ ምንም አታድርግ። ልጅቷ ሞት የሚገባው ኃጢአት አልሠራችም። ይህ ጉዳይ በባልንጀራው ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከሚገድል* ሰው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነው።+ 27 ምክንያቱም ሰውየው ልጅቷን ያገኛት ሜዳ ላይ ሲሆን የታጨችው ልጅ ብትጮኽም እንኳ ማንም አልደረሰላትም።

28 “አንድ ሰው ያልታጨችን አንዲት ድንግል አግኝቶ ቢይዛትና አብሯት ቢተኛ፣ በኋላም ቢጋለጡ+ 29 ሰውየው ለልጅቷ አባት 50 የብር ሰቅል ይስጥ፤ እሷም ሚስቱ ትሆናለች።+ ስላዋረዳትም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም።

30 “ማንም ሰው አባቱን እንዳያዋርድ* የአባቱን ሚስት አያግባ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ