የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • መጥምቁ ዮሐንስ ተወደሰ (1-15)

      • ዓመፀኛው ትውልድ ተወገዘ (16-24)

      • ‘ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለልጆች ገለጥክላቸው’ (25-27)

      • የኢየሱስ ቀንበር እረፍት ይሰጣል (28-30)

ማቴዎስ 11:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 4:23፤ 19:1፤ ሉቃስ 9:6

ማቴዎስ 11:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 14:3፤ ማር 6:17
  • +ሉቃስ 7:18-23

ማቴዎስ 11:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 3:11፤ ዮሐ 1:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 96

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2010፣ ገጽ 19

    1/15/2008፣ ገጽ 29-30

    7/1/1997፣ ገጽ 5-6

ማቴዎስ 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 7:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 96

ማቴዎስ 11:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:5, 6፤ 61:1
  • +ማቴ 8:3
  • +ማቴ 4:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 96

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/1997፣ ገጽ 5-6

ማቴዎስ 11:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:3፤ ሉቃስ 7:23፤ 1ቆሮ 1:23፤ 1ጴጥ 2:7, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    5/2021፣ ገጽ 2-4, 5-7

ማቴዎስ 11:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 3:1, 5
  • +ሉቃስ 7:24-28

ማቴዎስ 11:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለስላሳ ልብስ።”

ማቴዎስ 11:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:67, 76

ማቴዎስ 11:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 3:1፤ ማቴ 3:3፤ ማር 1:2፤ ሉቃስ 1:17፤ ዮሐ 3:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 96

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 31

ማቴዎስ 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 7:28፤ ዮሐ 3:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 178

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2019፣ ገጽ 29-30

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 96

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2008፣ ገጽ 21

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 32

ማቴዎስ 11:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 13:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2005፣ ገጽ 11

ማቴዎስ 11:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 16:16

ማቴዎስ 11:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 4:5፤ ማቴ 17:10-13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 113

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2011፣ ገጽ 10

    5/1/2001፣ ገጽ 22

    9/15/1997፣ ገጽ 12

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 31

ማቴዎስ 11:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 7:31-35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

ማቴዎስ 11:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

ማቴዎስ 11:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

ማቴዎስ 11:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ትክክል መሆኗ።”

  • *

    ወይም “በውጤቷ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 9:10፤ ማር 2:15፤ ዮሐ 2:2
  • +ሉቃስ 5:30፤ 15:2፤ 19:7
  • +ሉቃስ 7:34, 35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2018፣ ገጽ 6

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2001፣ ገጽ 12-13

ማቴዎስ 11:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እነዚህ የአይሁዳውያን ከተሞች አልነበሩም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮናስ 3:5, 6፤ ሉቃስ 10:13

ማቴዎስ 11:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 10:14

ማቴዎስ 11:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሐዲስ።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 4:31
  • +ሉቃስ 10:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 179

ማቴዎስ 11:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:15፤ ሉቃስ 10:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 179

ማቴዎስ 11:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 29:14፤ ማቴ 13:15፤ ሉቃስ 10:21፤ 1ቆሮ 1:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2013፣ ገጽ 9

ማቴዎስ 11:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 3:35
  • +ዮሐ 1:18
  • +ሉቃስ 10:22፤ ዮሐ 10:15፤ 1ዮሐ 5:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ተከታዬ ሁን፣” ገጽ 17-18

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/1997፣ ገጽ 19

    6/1/1994፣ ገጽ 29

ማቴዎስ 11:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው፣ ርዕስ 28

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2019፣ ገጽ 20-21

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2007፣ ገጽ 11-12

    8/15/2004፣ ገጽ 22-23

    6/1/2004፣ ገጽ 16

    12/15/2001፣ ገጽ 9-11

    8/15/1995፣ ገጽ 12-17

ማቴዎስ 11:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀንበሬን አብራችሁኝ ተሸከሙ።”

  • *

    ወይም “ደቀ መዛሙርቴም ሁኑ።”

  • *

    “ልዝብ፤ ለስላሳ፤ ሻካራ ያልሆነ” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    ወይም “ለነፍሳችሁም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 9:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው፣ ርዕስ 28

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    5/2020፣ ገጽ 18

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2019፣ ገጽ 21-25

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2018፣ ገጽ 8-9

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2012፣ ገጽ 13

    5/15/2007፣ ገጽ 11, 12-13

    8/15/2004፣ ገጽ 22-23

    6/1/2004፣ ገጽ 16

    12/15/2001፣ ገጽ 11-20

    9/1/2000፣ ገጽ 7-8

    6/15/1997፣ ገጽ 32

    8/15/1995፣ ገጽ 17-22

    6/1/1993፣ ገጽ 10

    10/15/1991፣ ገጽ 21-22, 24

    9/1/1991፣ ገጽ 27

    የመንግሥት አገልግሎት፣

    5/2008፣ ገጽ 1

ማቴዎስ 11:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለመሸከም የማያስቸግር።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው፣ ርዕስ 28

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    1/2018፣ ገጽ 7

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 98

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2010፣ ገጽ 25-26

    5/15/2007፣ ገጽ 11, 12-13

    12/15/2001፣ ገጽ 20

    10/15/1991፣ ገጽ 21-22, 24

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 11:1ማቴ 4:23፤ 19:1፤ ሉቃስ 9:6
ማቴ. 11:2ማቴ 14:3፤ ማር 6:17
ማቴ. 11:2ሉቃስ 7:18-23
ማቴ. 11:3ማቴ 3:11፤ ዮሐ 1:15
ማቴ. 11:4ሉቃስ 7:22
ማቴ. 11:5ኢሳ 35:5, 6፤ 61:1
ማቴ. 11:5ማቴ 8:3
ማቴ. 11:5ማቴ 4:23
ማቴ. 11:6ማር 6:3፤ ሉቃስ 7:23፤ 1ቆሮ 1:23፤ 1ጴጥ 2:7, 8
ማቴ. 11:7ማቴ 3:1, 5
ማቴ. 11:7ሉቃስ 7:24-28
ማቴ. 11:9ሉቃስ 1:67, 76
ማቴ. 11:10ሚል 3:1፤ ማቴ 3:3፤ ማር 1:2፤ ሉቃስ 1:17፤ ዮሐ 3:28
ማቴ. 11:11ሉቃስ 7:28፤ ዮሐ 3:3
ማቴ. 11:12ሉቃስ 13:24
ማቴ. 11:13ሉቃስ 16:16
ማቴ. 11:14ሚል 4:5፤ ማቴ 17:10-13
ማቴ. 11:16ሉቃስ 7:31-35
ማቴ. 11:19ማቴ 9:10፤ ማር 2:15፤ ዮሐ 2:2
ማቴ. 11:19ሉቃስ 5:30፤ 15:2፤ 19:7
ማቴ. 11:19ሉቃስ 7:34, 35
ማቴ. 11:21ዮናስ 3:5, 6፤ ሉቃስ 10:13
ማቴ. 11:22ሉቃስ 10:14
ማቴ. 11:23ሉቃስ 4:31
ማቴ. 11:23ሉቃስ 10:15
ማቴ. 11:24ማቴ 10:15፤ ሉቃስ 10:12
ማቴ. 11:25ኢሳ 29:14፤ ማቴ 13:15፤ ሉቃስ 10:21፤ 1ቆሮ 1:27
ማቴ. 11:27ዮሐ 3:35
ማቴ. 11:27ዮሐ 1:18
ማቴ. 11:27ሉቃስ 10:22፤ ዮሐ 10:15፤ 1ዮሐ 5:20
ማቴ. 11:29ዘካ 9:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 11:1-30

የማቴዎስ ወንጌል

11 ኢየሱስ ለ12 ደቀ መዛሙርቱ መመሪያ ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ በሌሎች ከተሞች ለማስተማርና ለመስበክ ሄደ።+

2 ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ+ ክርስቶስ ስላከናወናቸው ሥራዎች ሲሰማ ደቀ መዛሙርቱን በመላክ+ 3 “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀው።+ 4 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የምትሰሙትንና የምታዩትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፤+ 5 ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤+ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤+ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።+ 6 በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው።”+

7 መልእክተኞቹ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር?+ ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ 8 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት? ምርጥ ልብስ የለበሱማ የሚገኙት በነገሥታት ቤት ነው። 9 ታዲያ ለምን ሄዳችሁ? ነቢይ ለማየት? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ 10 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ!’+ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው። 11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።+ 12 መንግሥተ ሰማያት ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሰዎች የሚጋደሉለት ግብ ሆኗል፤ በተጋድሏቸው የሚጸኑም ያገኙታል።+ 13 ነቢያትና ሕጉ በሙሉ እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ተንብየዋልና፤+ 14 እንግዲህ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆናችሁ ‘ይመጣል የተባለው ኤልያስ’ እሱ ነው።+ 15 ጆሮ ያለው ይስማ።

16 “ይህን ትውልድ ከማን ጋር ላመሳስለው?+ በገበያ ስፍራ ተቀምጠው ጓደኞቻቸውን እየተጣሩ እንዲህ ከሚሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላል፦ 17 ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን በሐዘን ደረታችሁን አልደቃችሁም።’ 18 በተመሳሳይም ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ ሰዎች ግን ‘ጋኔን አለበት’ አሉ። 19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤+ ሰዎች ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉ።+ የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ መሆኗ* በሥራዋ* ተረጋግጧል።”+

20 ከዚያም ብዙ ተአምራት የፈጸመባቸውን ከተሞች ንስሐ ባለመግባታቸው የተነሳ እንዲህ ሲል ይነቅፋቸው ጀመር፦ 21 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና* ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር።+ 22 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።+ 23 አንቺም ቅፍርናሆም+ ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር* ትወርጃለሽ፤+ ምክንያቱም በአንቺ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በሰዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር። 24 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም ምድር ይቀልላታል።”+

25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ።+ 26 አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና። 27 አባቴ ሁሉንም ነገር ለእኔ ሰጥቶኛል፤+ ከአብ በስተቀር ወልድን በሚገባ የሚያውቅ የለም፤+ ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብን በሚገባ የሚያውቅ ማንም የለም።+ 28 እናንተ የደከማችሁና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ። 29 ቀንበሬን ተሸከሙ፤* ከእኔም ተማሩ፤* እኔ ገርና* በልቤ ትሑት ነኝ፤+ ለራሳችሁም* እረፍት ታገኛላችሁ። 30 ቀንበሬ ልዝብ፣* ሸክሜም ቀላል ነውና።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ