የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ነሐሴ 9 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 27 (57)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ ካሉት አቀራረቦች ውስጥ ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑትን ተጠቅመህ የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2004 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች አቀራረቦችንም መጠቀም ይቻላል። በሠርቶ ማሳያዎቹ ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚቻልበት ዝግጅት እንዲጠቀስ አድርግ። አድማጮች ለቀጣዩ ሳምንት አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ፦ “ጽናት ይክሳል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከታኅሣሥ 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-23 አንቀጽ 15-18 ላይ ጥቂት ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር በትራክቶች መጠቀም። በኅዳር 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3-4 ላይ በወጣው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአንቀጽ 5 ላይ እንደተገለጸው አቀራረባችንን እንደ ተማሪው ሁኔታ ለመለዋወጥ ዝግጁ መሆን እንዳለብን ጎላ አድርገህ ተናገር። ከአንቀጽ 8-10 ባለው ሐሳብ ላይ የተመሠረቱ አንድ ወይም ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ለጉባኤው ክልል ውጤታማ የሆነ ሌላ አቀራረብ ካለ ከላይ በተጠቀሱት ፋንታ እንዲቀርብ አድርግ። አድማጮች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት በመጠቀም ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 28 (58) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 73 (166)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ በልጆቻችሁ ውስጥ እውነትን ትከሉ። የቤተሰብ ደስታ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 55-59 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ወላጆች ልጆቻቸው ከይሖዋ ጋር የቀረበ ዝምድና እንዲመሠርቱ መርዳት የሚችሉባቸውን አራት መንገዶች ተናገር።
20 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት—ክፍል 2።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። የሚከተለው ሠርቶ ማሳያ በአምስት ደቂቃ ውስጥ እንዲቀርብ አድርግ። አንድ አስፋፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን እድገት እንዲያደርግ መርዳት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አንድን ሽማግሌ ይጠይቀዋል። ሽማግሌው አላስፈላጊ ነጥቦችንና ከሚጠናው ትምህርት ጋር ብዙም ግንኙነት የሌላቸውን ጉዳዮች እያነሱ በመወያየት ብዙ ጊዜ ማጥፋት የተለመደ ችግር እንደሆነ ይጠቅሳል። ከዚያም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ከተባለው ብሮሹር ላይ ትምህርት 9ን በመጠቀም (1) በርዕሱ ውስጥ በቀረቡት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማተኮር፣ (2) ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች በሚገባ መጠቀምና (3) ትምህርቱን ለተማሪው እንደሚስማማ አድርጎ ማቅረብ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለአስፋፊው ያሳየዋል። አስፋፊውን ምንጊዜም ከጥናቱ በፊት ጥሩ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ያሳስበዋል።
መዝሙር 38 (85) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 (33)
13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጉባኤ ሒሳብ ሪፖርት። የሰኔ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ለአንድ መምህር ምሥክርነት ሲሰጥ የሚያሳይ ይሁን።
20 ደቂቃ፦ “ስሙን በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።” የጉባኤው ጸሐፊ ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመጠቀም ያቀርበዋል። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጉባኤው የተመደበበትን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ተናገር።
12 ደቂቃ፦ በመስከረም የሚበረከቱትን ጽሑፎች ከተናገርክ በኋላ ጽሑፎቹን ለማበርከት የሚረዱ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 57 (136)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ፦ “በተገቢው ጊዜ የቀረበ መንፈሳዊ ምግብ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አንቀጽ 2ን ስትወያዩ ከአድማጮች መካከል አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች የማይረሳ ትዝታ ጥሎባቸው ስላለፈ የአውራጃ ስብሰባ እንዲናገሩ ጋብዝ።
8 ደቂቃ፦ “በምግባራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።” ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱት ጥቅሶች እንዲነበቡና ሐሳብ እንዲሰጥባቸው አድርግ። አድማጮች በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ጥሩ ምግባር ማሳየት ለይሖዋ ውዳሴ እንደሚያመጣ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።
17 ደቂቃ፦ ጥቅም አግኝተህባቸዋል? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት ትምህርቶች ውስጥ የሚከተሉትን ከልሱ:- የመግቢያ ሐሳቦችን በትንሽ ወረቀት ላይ ጽፎ መያዝ። (km 10/03 ገጽ 8) በግለሰብ ደረጃ ሌሎች ያደረጉትን በቀጥታ ጠቅሰን ከልብ ማመስገን። (km 11/03 ገጽ 1) ሰዎች በቤታቸው በሚገኙበት ሰዓት ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ማገልገል። (km 12/03 ገጽ 1) መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ፣ ለስብሰባዎች ለመዘጋጀትና ለመስክ አገልግሎት የተወሰነ ጊዜ መመደብ። (km 1/04 ገጽ 4) በመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና በግል ጥናታችን ላይ “መልካሚቱን ምድር” የተባለውን ብሮሹር መጠቀም። (km 3/04 ገጽ 2) ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ ለመጨረስ ግብ ማውጣት። (km 4/04 ገጽ 1) በንግድ አካባቢዎች ማገልገል። (km 7/04 ገጽ 4) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር በትራክቶች መጠቀም። (km 8/04 ገጽ 2) አድማጮች እነዚህን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 39 (86) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት . . .” የሚለው ርዕስ በሚቀጥለው ወር እንደሚጠና ተናገር።
15 ደቂቃ፦ “ልከኛና የሚያስከብር አለባበስ።” ለአንቀጹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱት ጥቅሶች እንዲነበቡና ሐሳብ እንዲሰጥባቸው አድርግ።
25 ደቂቃ፦ “የአቅኚነት መንፈስ አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንድ ወይም ለሁለት አቅኚዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግላቸው። የወላጆቻቸው፣ የሽማግሌዎች ወይም የሌሎች ምሳሌነት ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዲገቡ የገፋፋቸው እንዴት እንደሆነ ጠይቃቸው።
መዝሙር 83 (187) እና የመደምደሚያ ጸሎት።