የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 22:18, 19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ይሖዋን እንድትጠይቁ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማኸውን ቃል በተመለከተ፣ 19 ይህን ቦታም ሆነ ነዋሪዎቹን መቀጣጫ እንደማደርግና እንደምረግም የተናገርኩትን ነገር ስትሰማ ልብህ ስለተነካ፣* በይሖዋም ፊት ራስህን ስላዋረድክ+ እንዲሁም ልብስህን ስለቀደድክና+ በፊቴ ስላለቀስክ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል ይሖዋ።

  • 2 ዜና መዋዕል 33:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ወደ እሱ አጥብቆ ጸለየ፤ እሱም ተለመነው፤ በእሱ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያቀረበውንም ልመና ሰማው፤ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ንግሥናው መለሰው።+ ከዚያም ምናሴ፣ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አወቀ።+

  • መዝሙር 22:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 እሱ የተጨቆነውን ሰው መከራ አልናቀምና፤+ ደግሞም አልተጸየፈም፤

      ፊቱን ከእሱ አልሰወረም።+

      ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል።+

  • መዝሙር 34:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • ምሳሌ 28:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤+

      የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል።+

  • ኢሳይያስ 57:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ለዘላለም የሚኖረውና+ ስሙ ቅዱስ የሆነው፣+

      ከፍ ከፍ ያለውና እጅግ የከበረው እንዲህ ይላልና፦

      “ከፍ ባለውና ቅዱስ በሆነው ስፍራ እኖራለሁ፤+

      ደግሞም የተሰበረ ልብ ካለውና መንፈሱ ከተደቆሰው ጋር እሆናለሁ፤

      ይህም የችግረኞችን መንፈስ አነሳሳ ዘንድ፣

      የተሰበረ ልብ ያላቸውንም አነቃቃ ዘንድ ነው።+

  • ሉቃስ 15:22-24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 አባትየው ግን ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ቶሎ በሉ! ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጥታችሁ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት። 23 የሰባውንም ጥጃ አምጥታችሁ እረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት። 24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል።+ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።

  • ሉቃስ 18:13, 14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ለማየትም እንኳ አልደፈረም፤ እንዲያውም ‘አምላክ ሆይ፣ ኃጢአተኛ ለሆንኩት ለእኔ ቸርነት አድርግልኝ’* እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር።+ 14 እላችኋለሁ፣ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይሄኛው ሰው ይበልጥ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ።+ ምክንያቱም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ግን ከፍ ይደረጋል።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ