የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኤርምያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የይሁዳ ኃጢአት በጽላት ላይ ተቀርጿል (1-4)

      • በይሖዋ መታመን የሚያስገኘው በረከት (5-8)

      • ልብ ከዳተኛ ነው (9-11)

      • የእስራኤል ተስፋ የሆነው ይሖዋ (12, 13)

      • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (14-18)

      • “የሰንበትን ቀን ቀድሱ” (19-27)

ኤርምያስ 17:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 1:29፤ ሕዝ 6:13
  • +መሳ 3:7፤ 2ዜና 24:18፤ 33:1, 3

ኤርምያስ 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 24:11, 13፤ ኤር 15:13
  • +ዘሌ 26:30፤ ሕዝ 6:3

ኤርምያስ 17:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በቁጣዬ እንደ እሳት ነደሃልና” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 5:2
  • +ዘዳ 28:48፤ ኤር 16:13
  • +ኢሳ 5:25፤ ኤር 15:14

ኤርምያስ 17:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሥጋን ክንዱ የሚያደርግና።”

  • *

    ወይም “ብርቱ ሰው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:1, 2
  • +2ነገ 16:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 44

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 10

    8/15/1998፣ ገጽ 6

ኤርምያስ 17:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ብርቱ ሰው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 34:8፤ 146:5፤ ኢሳ 26:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2007፣ ገጽ 10

ኤርምያስ 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 1:3፤ 92:12, 13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    9/2019፣ ገጽ 8

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2011፣ ገጽ 28

    3/15/2011፣ ገጽ 14

    3/1/2009፣ ገጽ 16-17

ኤርምያስ 17:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አታላይ።”

  • *

    “ፈውስ የለውም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 6:5፤ 8:21፤ ምሳሌ 28:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2004፣ ገጽ 10-11

    10/15/2001፣ ገጽ 25

    8/1/2001፣ ገጽ 9-10

    3/1/2000፣ ገጽ 30

ኤርምያስ 17:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ጥልቅ ስሜትንም።” ቃል በቃል “ኩላሊትንም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:7፤ 1ዜና 28:9፤ ምሳሌ 17:3፤ 21:2
  • +ሮም 2:6፤ ገላ 6:7፤ ራእይ 2:23፤ 22:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2013፣ ገጽ 9

ኤርምያስ 17:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 28:20፤ ኢሳ 1:23፤ ያዕ 5:4

ኤርምያስ 17:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 2:5፤ ኢሳ 6:1

ኤርምያስ 17:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እኔን።” ይሖዋን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 73:27፤ ኢሳ 1:28
  • +ኤር 2:13፤ ራእይ 22:1

ኤርምያስ 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:20

ኤርምያስ 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 5:19፤ 2ጴጥ 3:4

ኤርምያስ 17:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጥፍ ድርብ ጥፋት አምጣባቸው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 15:15፤ 20:11
  • +ኤር 18:23

ኤርምያስ 17:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 7:2

ኤርምያስ 17:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለነፍሳችሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 13:19

ኤርምያስ 17:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:9, 10፤ ዘሌ 23:3
  • +ዘፀ 31:13

ኤርምያስ 17:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገታቸውን አደነደኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 48:4፤ ሕዝ 20:13

ኤርምያስ 17:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:12-14

ኤርምያስ 17:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 132:11
  • +ኤር 22:4

ኤርምያስ 17:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከደቡብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 32:44
  • +ኤር 33:13
  • +ዘሌ 1:3
  • +ዕዝራ 3:3
  • +ዘሌ 2:1, 2
  • +መዝ 107:22፤ 116:17፤ ኤር 33:10, 11

ኤርምያስ 17:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 25:9, 10፤ ኤር 39:8
  • +2ነገ 22:16, 17፤ ሰቆ 4:11

ተዛማጅ ሐሳብ

ኤር. 17:2ኢሳ 1:29፤ ሕዝ 6:13
ኤር. 17:2መሳ 3:7፤ 2ዜና 24:18፤ 33:1, 3
ኤር. 17:32ነገ 24:11, 13፤ ኤር 15:13
ኤር. 17:3ዘሌ 26:30፤ ሕዝ 6:3
ኤር. 17:4ሰቆ 5:2
ኤር. 17:4ዘዳ 28:48፤ ኤር 16:13
ኤር. 17:4ኢሳ 5:25፤ ኤር 15:14
ኤር. 17:5ኢሳ 30:1, 2
ኤር. 17:52ነገ 16:7
ኤር. 17:7መዝ 34:8፤ 146:5፤ ኢሳ 26:3
ኤር. 17:8መዝ 1:3፤ 92:12, 13
ኤር. 17:9ዘፍ 6:5፤ 8:21፤ ምሳሌ 28:26
ኤር. 17:101ሳሙ 16:7፤ 1ዜና 28:9፤ ምሳሌ 17:3፤ 21:2
ኤር. 17:10ሮም 2:6፤ ገላ 6:7፤ ራእይ 2:23፤ 22:12
ኤር. 17:11ምሳሌ 28:20፤ ኢሳ 1:23፤ ያዕ 5:4
ኤር. 17:122ዜና 2:5፤ ኢሳ 6:1
ኤር. 17:13መዝ 73:27፤ ኢሳ 1:28
ኤር. 17:13ኤር 2:13፤ ራእይ 22:1
ኤር. 17:14ኤር 15:20
ኤር. 17:15ኢሳ 5:19፤ 2ጴጥ 3:4
ኤር. 17:18ኤር 15:15፤ 20:11
ኤር. 17:18ኤር 18:23
ኤር. 17:19ኤር 7:2
ኤር. 17:21ነህ 13:19
ኤር. 17:22ዘፀ 20:9, 10፤ ዘሌ 23:3
ኤር. 17:22ዘፀ 31:13
ኤር. 17:23ኢሳ 48:4፤ ሕዝ 20:13
ኤር. 17:24ዘዳ 5:12-14
ኤር. 17:25መዝ 132:11
ኤር. 17:25ኤር 22:4
ኤር. 17:26ኤር 32:44
ኤር. 17:26ኤር 33:13
ኤር. 17:26ዘሌ 1:3
ኤር. 17:26ዕዝራ 3:3
ኤር. 17:26ዘሌ 2:1, 2
ኤር. 17:26መዝ 107:22፤ 116:17፤ ኤር 33:10, 11
ኤር. 17:272ነገ 25:9, 10፤ ኤር 39:8
ኤር. 17:272ነገ 22:16, 17፤ ሰቆ 4:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኤርምያስ 17:1-27

ኤርምያስ

17 “የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፏል።

በሾለ የአልማዝ ጫፍ በልባቸው ጽላትና

በመሠዊያዎቻቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጿል፤

 2 ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻቸው ከፍ ባሉ ኮረብቶች ላይ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ አጠገብ ያሉትን+

መሠዊያዎቻቸውንና የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ያስታውሳሉ፤+

 3 በአውላላ ሜዳ ላይ ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትንም ያስባሉ።

ንብረትህን ይኸውም ውድ ሀብትህን ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ፤+

አዎ፣ በመላው ክልልህ ካለው ኃጢአት የተነሳ ከፍ ያሉ ቦታዎችህ እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።+

 4 የሰጠሁህን ርስት በገዛ ፈቃድህ አሳልፈህ ትሰጣለህ።+

በማታውቀውም ምድር ጠላቶችህን እንድታገለግል አደርግሃለሁ፤+

ቁጣዬን እንደ እሳት አቀጣጥለሃልና።*+

እሳቱም ለዘላለም ይነዳል።”

 5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

“በሰዎች የሚታመን፣+

በሰብዓዊ ኃይል የሚመካና*+

ልቡ ከይሖዋ የራቀ ሰው* የተረገመ ነው።

 6 በበረሃ ብቻውን እንዳለ ዛፍ ይሆናል።

መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤

ይልቁንም በምድረ በዳ ደረቅ በሆኑ ስፍራዎች፣

ማንም መኖር በማይችልበት የጨው ምድር ይኖራል።

 7 በይሖዋ የሚታመን፣

መመኪያውም ይሖዋ የሆነ ሰው* የተባረከ ነው።+

 8 በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣

ሥሮቹን ወደ ጅረት እንደሚሰድ ዛፍ ይሆናል።

ሙቀት ሲመጣ አያስተውልም፤

ከዚህ ይልቅ ቅጠሉ ሁልጊዜ ይለመልማል።+

ድርቅ በሚከሰትበት ዓመትም ምንም አይጨነቅም፤

ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።

 9 ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ* ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም።*+

ማንስ ሊያውቀው ይችላል?

10 እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣

እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠት

ልብን እመረምራለሁ፤+

የውስጥ ሐሳብንም* እፈትናለሁ።+

11 በማጭበርበር* ሀብት የሚያከማች ሰው፣

ያልጣለችውን እንቁላል እንደምትሰበስብ ቆቅ ነው።+

በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤

በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።”

12 ከመጀመሪያ አንስቶ ክብራማ የሆነ ዙፋን ከፍ ከፍ ብሏል፤

እሱም መቅደሳችን ነው።+

13 የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣

አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ።

አንተን* የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤+

ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል።+

14 ይሖዋ ሆይ፣ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ።

አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤+

የማወድሰው አንተን ነውና።

15 እነሆ፣ “የይሖዋ ቃል የት አለ?+

እስቲ ይፈጸም!”

የሚሉኝ ሰዎች አሉ።

16 እኔ ግን እረኛ ሆኜ አንተን ከመከተል ወደኋላ አላልኩም፤

የጥፋትንም ቀን ፈጽሞ አልተመኘሁም።

አንተ ከንፈሮቼ የተናገሩትን ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤

ሁሉም የተፈጸመው በፊትህ ነው!

17 ሽብር ላይ አትጣለኝ።

አንተ በጥፋት ቀን መጠጊያዬ ነህ።

18 አሳዳጆቼ ኀፍረት ይከናነቡ፤+

እኔ ግን ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።

እነሱ በሽብር ይዋጡ፤

እኔ ግን አልሸበር።

የጥፋት ቀን አምጣባቸው፤+

አድቅቃቸው፤ ሙሉ በሙሉም አጥፋቸው።*

19 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም።+ 20 እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፣ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። 21 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለራሳችሁ* ተጠንቀቁ፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም አትሸከሙ ወይም በኢየሩሳሌም በሮች አታስገቡ።+ 22 በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም ከቤታችሁ ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ።+ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሁሉ እናንተም የሰንበትን ቀን ቀድሱ።+ 23 ሆኖም እነሱ አልሰሙም፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም፤ ላለመታዘዝና ተግሣጽ ላለመቀበል በእንቢተኝነታቸው ጸኑ።”’*+

24 “‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣+ 25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት+ ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤+ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች። 26 ሰዎችም ከይሁዳ ከተሞች፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ቦታዎች፣ ከቢንያም አገር፣+ ከቆላው፣+ ከተራራማው አካባቢና ከኔጌብ* ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎች፣+ መሥዋዕቶች፣+ የእህል መባዎች፣+ ነጭ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕቶች ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት ይመጣሉ።+

27 “‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤+ ፈጽሞም አይጠፋም።”’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ