የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 30
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ባላ ዳንንና ንፍታሌምን ወለደች (1-8)

      • ዚልጳ ጋድንና አሴርን ወለደች (9-13)

      • ሊያ ይሳኮርንና ዛብሎንን ወለደች (14-21)

      • ራሔል ዮሴፍን ወለደች (22-24)

      • የያዕቆብ መንጋ እየበዛ ሄደ (25-43)

ዘፍጥረት 30:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የማህፀን ፍሬ የነፈገሽን።”

ዘፍጥረት 30:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በጉልበቶቼ ላይ እንድትወልድልኝና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2007፣ ገጽ 10-11

ዘፍጥረት 30:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:22

ዘፍጥረት 30:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ዳኛ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:25፤ 46:23፤ 49:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 3/2020፣ ገጽ 8

ዘፍጥረት 30:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የገጠምኩት ትግል” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:25፤ 46:24፤ 49:21፤ ዘዳ 33:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 3/2020፣ ገጽ 8

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2002፣ ገጽ 29-30

ዘፍጥረት 30:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:26

ዘፍጥረት 30:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “መልካም ዕድል” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:19፤ ዘኁ 32:33

ዘፍጥረት 30:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ደስተኛ፤ ደስታ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:46, 48
  • +ዘፍ 35:26፤ 46:17፤ 49:20፤ ዘዳ 33:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 3/2020፣ ገጽ 8

ዘፍጥረት 30:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እንግሊዝኛ፣ ማንድሬክ። ከድንች ዝርያ የሚመደብ ተክል ሲሆን ብርቱካንማ ቀለም ያለው ፍሬ ያፈራል፤ ከፕሪም ጋር የሚመሳሰል ቅርጽ አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2007፣ ገጽ 11

    1/15/2004፣ ገጽ 28

ዘፍጥረት 30:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:30

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2007፣ ገጽ 11

    1/15/2004፣ ገጽ 28

ዘፍጥረት 30:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቅጥር ደሞዝ።”

  • *

    “እሱ ደሞዝ ነው” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:23፤ 46:13፤ 49:14፤ ዘዳ 33:18

ዘፍጥረት 30:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሩት 4:11

ዘፍጥረት 30:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “መቻል” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:23፤ 46:15፤ መዝ 127:3
  • +ዘፍ 29:32
  • +ዘፍ 46:14፤ 49:13፤ ዘዳ 33:18

ዘፍጥረት 30:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 34:1

ዘፍጥረት 30:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አምላክ ልመናዋን ሰምቶ ማህፀኗን በመክፈት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:31

ዘፍጥረት 30:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:24, 25

ዘፍጥረት 30:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዮሴፍያህ የተባለው ስም አጭር አጠራር ሲሆን “ያህ ይጨምር” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:24፤ 45:4፤ ዘዳ 33:13፤ ሥራ 7:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 3/2020፣ ገጽ 8

ዘፍጥረት 30:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:15፤ 31:13

ዘፍጥረት 30:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:41፤ ሆሴዕ 12:12

ዘፍጥረት 30:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከማስረጃው።”

ዘፍጥረት 30:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:7

ዘፍጥረት 30:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:38

ዘፍጥረት 30:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 32:9, 10

ዘፍጥረት 30:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 12:12

ዘፍጥረት 30:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2003፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 30:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሐቀኝነቴ።”

ዘፍጥረት 30:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2003፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 30:35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2003፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 30:36

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2003፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 30:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጥሩ መዓዛ ያላቸው ነጫጭ አበቦች የሚያወጣ ዛፍ።

  • *

    የተንዠረገጉ ቅርንጫፎችና እየተቀረፈ የሚወድቅ ቅርፊት ያለው ዛፍ።

ዘፍጥረት 30:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:9

ዘፍጥረት 30:43

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 32:5፤ 36:6, 7

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 30:3ዘፍ 29:29
ዘፍ. 30:4ዘፍ 35:22
ዘፍ. 30:6ዘፍ 35:25፤ 46:23፤ 49:16
ዘፍ. 30:8ዘፍ 35:25፤ 46:24፤ 49:21፤ ዘዳ 33:23
ዘፍ. 30:9ዘፍ 35:26
ዘፍ. 30:11ዘፍ 49:19፤ ዘኁ 32:33
ዘፍ. 30:13ሉቃስ 1:46, 48
ዘፍ. 30:13ዘፍ 35:26፤ 46:17፤ 49:20፤ ዘዳ 33:24
ዘፍ. 30:14ዘፍ 29:32
ዘፍ. 30:15ዘፍ 29:30
ዘፍ. 30:18ዘፍ 35:23፤ 46:13፤ 49:14፤ ዘዳ 33:18
ዘፍ. 30:19ሩት 4:11
ዘፍ. 30:20ዘፍ 35:23፤ 46:15፤ መዝ 127:3
ዘፍ. 30:20ዘፍ 29:32
ዘፍ. 30:20ዘፍ 46:14፤ 49:13፤ ዘዳ 33:18
ዘፍ. 30:21ዘፍ 34:1
ዘፍ. 30:22ዘፍ 29:31
ዘፍ. 30:23ሉቃስ 1:24, 25
ዘፍ. 30:24ዘፍ 35:24፤ 45:4፤ ዘዳ 33:13፤ ሥራ 7:9
ዘፍ. 30:25ዘፍ 28:15፤ 31:13
ዘፍ. 30:26ዘፍ 31:41፤ ሆሴዕ 12:12
ዘፍ. 30:28ዘፍ 31:7
ዘፍ. 30:29ዘፍ 31:38
ዘፍ. 30:30ዘፍ 32:9, 10
ዘፍ. 30:31ሆሴዕ 12:12
ዘፍ. 30:32ዘፍ 31:7
ዘፍ. 30:34ዘፍ 31:8
ዘፍ. 30:42ዘፍ 31:9
ዘፍ. 30:43ዘፍ 32:5፤ 36:6, 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 30:1-43

ዘፍጥረት

30 ራሔል ለያዕቆብ ምንም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእህቷ ቀናች፤ ያዕቆብንም “ልጆች ስጠኝ፤ አለዚያ እሞታለሁ” ትለው ጀመር። 2 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ራሔልን በጣም ተቆጥቶ “እኔ፣ እንዳትወልጂ ያደረገሽን* አምላክ መሰልኩሽ እንዴ?” አላት። 3 እሷም በዚህ ጊዜ “ባሪያዬ ባላ+ ይችውልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና* እኔም በእሷ አማካኝነት ልጆች እንዳገኝ ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጽም” አለችው። 4 በዚህ መሠረት አገልጋይዋን ባላን ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ።+ 5 ባላም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6 ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን*+ አለችው። 7 የራሔል አገልጋይ ባላ በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 8 ራሔልም “ከእህቴ ጋር ብርቱ ትግል ገጠምኩ፤ አሸናፊም ሆንኩ!” አለች። በመሆኑም ስሙን ንፍታሌም*+ አለችው።

9 ሊያ ልጅ መውለድ እንዳቆመች ስትረዳ አገልጋይዋን ዚልጳን ለያዕቆብ ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው።+ 10 የሊያም አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 11 ከዚያም ሊያ “ምንኛ መታደል ነው!” አለች። በመሆኑም ስሙን ጋድ*+ አለችው። 12 ከዚያ በኋላ የሊያ አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 13 ከዚያም ሊያ “ምንኛ ደስተኛ ነኝ! በእርግጥም ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛ ይሉኛል”+ አለች። በመሆኑም ስሙን አሴር*+ አለችው።

14 የስንዴ መከር በሚሰበሰብበት ወቅት ሮቤል+ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከሜዳውም ላይ ፍሬ* ለቀመ። ለእናቱ ለሊያም አመጣላት። ከዚያም ራሔል ሊያን “እባክሽ፣ ልጅሽ ካመጣው ፍሬ የተወሰነ ስጪኝ” አለቻት። 15 በዚህ ጊዜ ሊያ “ባሌን የወሰድሽብኝ አነሰሽና+ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣውን ፍሬ መውሰድ ትፈልጊያለሽ?” አለቻት። በመሆኑም ራሔል “እሺ፣ ልጅሽ ባመጣው ፍሬ ፋንታ ዛሬ ማታ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት።

16 ያዕቆብ የዚያን ቀን ምሽት ከእርሻ ሲመለስ ሊያ ወጥታ ተቀበለችውና “ልጄ ባመጣው ፍሬ ስለተከራየሁህ ዛሬ የምትተኛው ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ስለሆነም በዚያ ሌሊት ከእሷ ጋር አደረ። 17 አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18 ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን* ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር*+ አለችው። 19 ሊያም በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ስድስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት።+ 20 ሊያም “አምላክ አድሎኛል፤ አዎ፣ መልካም ስጦታ ሰጥቶኛል። ለባሌ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት+ ከእንግዲህ ይታገሠኛል”+ አለች። በመሆኑም ስሙን ዛብሎን*+ አለችው። 21 ከዚያ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና+ አለቻት።

22 በመጨረሻም አምላክ ራሔልን አሰባት፤ ልመናዋንም ሰምቶ መፀነስ እንድትችል በማድረግ* ጸሎቷን መለሰላት።+ 23 እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ከዚያም “አምላክ ነቀፋዬን አስወገደልኝ!”+ አለች። 24 በመሆኑም “ይሖዋ ሌላ ወንድ ልጅ ጨመረልኝ” በማለት ስሙን ዮሴፍ*+ አለችው።

25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬና ወደ ምድሬ እንድመለስ አሰናብተኝ።+ 26 ለእነሱ ስል ያገለገልኩህን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል እንዳገለገልኩህ በሚገባ ታውቃለህ።”+ 27 ከዚያም ላባ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ ይሖዋ እየባረከኝ ያለው በአንተ የተነሳ መሆኑን በንግርት* ተረድቻለሁ” አለው። 28 ከዚያም “ደሞዝህን አሳውቀኝና እሰጥሃለሁ”+ አለው። 29 በመሆኑም ያዕቆብ እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልኩህና መንጋህም ምን ያህል እየበዛልህ እንዳለ ታውቃለህ፤+ 30 እኔ ከመምጣቴ በፊት የነበረህ ነገር ጥቂት እንደሆነና እኔ ከመጣሁ በኋላ ግን ከብቶችህ በጣም እየበዙ እንደሄዱ፣ ይሖዋም እንደባረከህ ታውቃለህ። ታዲያ ለራሴ ቤት አንድ ነገር የማደርገው መቼ ነው?”+

31 ከዚያም ላባ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው። ያዕቆብም እንዲህ አለ፦ “እኔ ምንም ነገር እንድትሰጠኝ አልፈልግም! የምጠይቅህን አንድ ነገር ብቻ የምታደርግልኝ ከሆነ መንጋህን መጠበቄንና መንከባከቤን እቀጥላለሁ።+ 32 ዛሬ በመንጎችህ ሁሉ መካከል እዘዋወራለሁ። አንተም ከመንጋው መካከል ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን በጎች ሁሉ፣ ከጠቦቶቹም መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን በጎች ሁሉ እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑትንና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንስት ፍየሎች ሁሉ ለይ። ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነቶቹ የእኔ ደሞዝ ይሆናሉ።+ 33 ወደፊት ደሞዜን ለመመልከት በምትመጣበት ጊዜ ጽድቄ* ስለ እኔ ይናገራል፤ ከእንስት ፍየሎቹ መካከል ጠቃጠቆ የሌለበትና ዥጉርጉር ያልሆነ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ ያልሆነ በእኔ ዘንድ ከተገኘ ያ የተሰረቀ እንደሆነ ይቆጠራል።”

34 በዚህ ጊዜ ላባ “ይሄማ ጥሩ ነው! እንዳልከው ይሁን” አለው።+ 35 ከዚያም በዚያኑ ቀን ሽንትር ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን ተባዕት ፍየሎች ሁሉ፣ ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን እንስት ፍየሎች ሁሉ፣ ነጭ የሚባል ነገር ያለበትን ሁሉ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን ሁሉ ለየ፤ እነዚህንም ወንዶች ልጆቹ እንዲጠብቋቸው ሰጣቸው። 36 ከዚህ በኋላ በእሱና በያዕቆብ መካከል የሦስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት እንዲኖር አደረገ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጎች ይጠብቅ ጀመር።

37 ከዚያም ያዕቆብ ከሊብነህ፣* ከአልሞንድና ከአርሞን* ዛፎች ላይ የተቆረጡ እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በመቀጠልም በትሮቹን አለፍ አለፍ ብሎ በመላጥና ነጩ እንዲታይ በማድረግ ዥጉርጉር እንዲሆኑ አደረገ። 38 ከዚያም የላጣቸውን በትሮች ወስዶ መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ እንዲያዩአቸው በመንጎቹ ፊት ለፊት በቦዮቹ ማለትም ውኃ በሚጠጡባቸው ገንዳዎች ውስጥ አስቀመጣቸው፤ ይህን ያደረገውም መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነው።

39 ስለዚህ መንጎቹ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ ይነሳሱ ነበር፤ መንጎቹም ሽንትርና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑ ግልገሎችን ይወልዱ ነበር። 40 ከዚያም ያዕቆብ ጠቦቶቹን ለየ፤ ከዚያም መንጎቹ በላባ መንጎች መካከል ወዳሉት ሽንትር ወዳለባቸውና ጥቁር ቡናማ ወደሆኑት ሁሉ እንዲመለከቱ አደረገ። ከዚያም የራሱን መንጎች ለየ፤ ከላባ መንጎች ጋር አልቀላቀላቸውም። 41 ያዕቆብም ብርቱ የሆኑት እንስሳት ለስሪያ በተነሳሱ ቁጥር በትሮቹን በመንጎቹ ፊት ለፊት ገንዳዎቹ ውስጥ ያስቀምጣቸው ነበር፤ እንዲህ የሚያደርገው መንጎቹ በበትሮቹ አማካኝነት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነበር። 42 እንስሶቹ ደካማ ሲሆኑ ግን በትሮቹን ገንዳዎቹ ውስጥ አያስቀምጥም ነበር። ስለሆነም ደካማ ደካማዎቹ ለላባ ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎቹ ግን ለያዕቆብ ሆኑ።+

43 በዚህ መንገድ ይህ ሰው እጅግ ባለጸጋ እየሆነ ሄደ፤ የብዙ መንጎች፣ የወንድና የሴት አገልጋዮች፣ የግመሎች እንዲሁም የአህዮች ባለቤት ሆነ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ