የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንደማይሠራ ተነገረው (1-7)

      • ለዳዊት የመንግሥት ቃል ኪዳን ተገባለት (8-17)

      • ዳዊት ያቀረበው የምስጋና ጸሎት (18-29)

2 ሳሙኤል 7:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቤተ መንግሥቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 17:1

2 ሳሙኤል 7:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:1፤ 1ዜና 29:29
  • +2ሳሙ 6:17
  • +2ሳሙ 5:11

2 ሳሙኤል 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 8:17፤ 1ዜና 17:2፤ 22:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2012፣ ገጽ 24-25

2 ሳሙኤል 7:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 5:3፤ 8:17-19፤ 1ዜና 17:4-6፤ 22:7, 8

2 ሳሙኤል 7:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:18, 34፤ ኢያሱ 18:1

2 ሳሙኤል 7:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከእስራኤል ወንዶች ልጆች።”

2 ሳሙኤል 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:2፤ 1ዜና 17:7-10፤ 28:4፤ መዝ 78:70, 71
  • +1ሳሙ 16:11

2 ሳሙኤል 7:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:14፤ 2ሳሙ 5:10
  • +2ሳሙ 22:1፤ መዝ 18:37
  • +1ዜና 14:2, 17

2 ሳሙኤል 7:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:14፤ መዝ 89:20, 22

2 ሳሙኤል 7:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥርወ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:16
  • +ዘዳ 25:19
  • +1ነገ 2:24፤ መዝ 89:4

2 ሳሙኤል 7:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:1
  • +ዘፍ 49:10፤ 1ነገ 8:20፤ 1ዜና 17:11-14፤ መዝ 132:11፤ ኢሳ 9:7፤ 11:1፤ ማቴ 21:9፤ 22:42፤ ሉቃስ 1:32, 33፤ ዮሐ 7:42፤ ሥራ 2:30

2 ሳሙኤል 7:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 5:5፤ 6:12፤ ዘካ 6:12, 13
  • +1ነገ 1:37፤ 1ዜና 22:10፤ 28:7፤ መዝ 89:4, 36

2 ሳሙኤል 7:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በአዳም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 28:6፤ ማቴ 3:17፤ ዕብ 1:5
  • +መዝ 89:30, 32፤ ኤር 52:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 7፣ ገጽ 12

2 ሳሙኤል 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 15:23, 26

2 ሳሙኤል 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 45:6፤ 89:36፤ ዳን 2:44፤ ዕብ 1:8፤ ራእይ 11:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 20

    12/15/2006፣ ገጽ 4

2 ሳሙኤል 7:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 17:15

2 ሳሙኤል 7:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 17:16-22

2 ሳሙኤል 7:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሕግ።”

2 ሳሙኤል 7:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:7፤ መዝ 17:3

2 ሳሙኤል 7:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከፈቃድህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 25:14

2 ሳሙኤል 7:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:24፤ 1ዜና 16:25
  • +ዘፀ 15:11፤ መዝ 83:18
  • +ዘዳ 4:35

2 ሳሙኤል 7:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:7፤ መዝ 147:19, 20
  • +ዘዳ 10:21
  • +ዘፀ 9:16
  • +ዘፀ 3:8፤ 19:5፤ ኢሳ 63:9

2 ሳሙኤል 7:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 26:18
  • +ዘፀ 15:2

2 ሳሙኤል 7:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 17:23-27፤ መዝ 89:20, 28

2 ሳሙኤል 7:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 29:11፤ መዝ 72:19፤ ማቴ 6:9፤ ዮሐ 12:28
  • +ኢሳ 9:7፤ ኤር 33:22

2 ሳሙኤል 7:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሥርወ መንግሥት።”

  • *

    ቃል በቃል “ልብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:11

2 ሳሙኤል 7:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 23:19፤ መዝ 89:35፤ 132:11፤ ዮሐ 17:17

2 ሳሙኤል 7:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 89:20, 36፤ 132:12
  • +2ሳሙ 22:51፤ መዝ 72:17

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 7:11ዜና 17:1
2 ሳሙ. 7:22ሳሙ 12:1፤ 1ዜና 29:29
2 ሳሙ. 7:22ሳሙ 6:17
2 ሳሙ. 7:22ሳሙ 5:11
2 ሳሙ. 7:31ነገ 8:17፤ 1ዜና 17:2፤ 22:7
2 ሳሙ. 7:51ነገ 5:3፤ 8:17-19፤ 1ዜና 17:4-6፤ 22:7, 8
2 ሳሙ. 7:6ዘፀ 40:18, 34፤ ኢያሱ 18:1
2 ሳሙ. 7:82ሳሙ 5:2፤ 1ዜና 17:7-10፤ 28:4፤ መዝ 78:70, 71
2 ሳሙ. 7:81ሳሙ 16:11
2 ሳሙ. 7:91ሳሙ 18:14፤ 2ሳሙ 5:10
2 ሳሙ. 7:92ሳሙ 22:1፤ መዝ 18:37
2 ሳሙ. 7:91ዜና 14:2, 17
2 ሳሙ. 7:10መሳ 2:14፤ መዝ 89:20, 22
2 ሳሙ. 7:11መሳ 2:16
2 ሳሙ. 7:11ዘዳ 25:19
2 ሳሙ. 7:111ነገ 2:24፤ መዝ 89:4
2 ሳሙ. 7:121ነገ 2:1
2 ሳሙ. 7:12ዘፍ 49:10፤ 1ነገ 8:20፤ 1ዜና 17:11-14፤ መዝ 132:11፤ ኢሳ 9:7፤ 11:1፤ ማቴ 21:9፤ 22:42፤ ሉቃስ 1:32, 33፤ ዮሐ 7:42፤ ሥራ 2:30
2 ሳሙ. 7:131ነገ 5:5፤ 6:12፤ ዘካ 6:12, 13
2 ሳሙ. 7:131ነገ 1:37፤ 1ዜና 22:10፤ 28:7፤ መዝ 89:4, 36
2 ሳሙ. 7:141ዜና 28:6፤ ማቴ 3:17፤ ዕብ 1:5
2 ሳሙ. 7:14መዝ 89:30, 32፤ ኤር 52:3
2 ሳሙ. 7:151ሳሙ 15:23, 26
2 ሳሙ. 7:16መዝ 45:6፤ 89:36፤ ዳን 2:44፤ ዕብ 1:8፤ ራእይ 11:15
2 ሳሙ. 7:171ዜና 17:15
2 ሳሙ. 7:181ዜና 17:16-22
2 ሳሙ. 7:201ሳሙ 16:7፤ መዝ 17:3
2 ሳሙ. 7:21መዝ 25:14
2 ሳሙ. 7:22ዘዳ 3:24፤ 1ዜና 16:25
2 ሳሙ. 7:22ዘፀ 15:11፤ መዝ 83:18
2 ሳሙ. 7:22ዘዳ 4:35
2 ሳሙ. 7:23ዘዳ 4:7፤ መዝ 147:19, 20
2 ሳሙ. 7:23ዘዳ 10:21
2 ሳሙ. 7:23ዘፀ 9:16
2 ሳሙ. 7:23ዘፀ 3:8፤ 19:5፤ ኢሳ 63:9
2 ሳሙ. 7:24ዘዳ 26:18
2 ሳሙ. 7:24ዘፀ 15:2
2 ሳሙ. 7:251ዜና 17:23-27፤ መዝ 89:20, 28
2 ሳሙ. 7:261ዜና 29:11፤ መዝ 72:19፤ ማቴ 6:9፤ ዮሐ 12:28
2 ሳሙ. 7:26ኢሳ 9:7፤ ኤር 33:22
2 ሳሙ. 7:272ሳሙ 7:11
2 ሳሙ. 7:28ዘኁ 23:19፤ መዝ 89:35፤ 132:11፤ ዮሐ 17:17
2 ሳሙ. 7:29መዝ 89:20, 36፤ 132:12
2 ሳሙ. 7:292ሳሙ 22:51፤ መዝ 72:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 7:1-29

ሁለተኛ ሳሙኤል

7 ንጉሡ በራሱ ቤት* መኖር በጀመረና+ ይሖዋም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ እረፍት በሰጠው ጊዜ 2 ነቢዩ ናታንን+ “የእውነተኛው አምላክ ታቦት በድንኳን ውስጥ+ ተቀምጦ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ+ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው። 3 ናታንም ንጉሡን “ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለሆነ ሄደህ በልብህ ያለውን ነገር ሁሉ አድርግ” አለው።+

4 በዚያው ሌሊት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ናታን መጣ፦ 5 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የምኖርበትን ቤት መሥራት ይኖርብሃል?+ 6 እስራኤላውያንን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ ድንኳን እጓዝ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ 7 ከእስራኤላውያን* ሁሉ ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ በሙሉ ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የነገድ መሪዎች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?”’ 8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ። 9 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።+ 10 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎች እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤+ 11 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። እኔም ከጠላቶችህ ሁሉ እረፍት እሰጥሃለሁ።+

“‘“በተጨማሪም ይሖዋ ቤት* እንደሚሠራልህ ይሖዋ ራሱ ነግሮሃል።+ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+ 15 ከፊትህ ካስወገድኩት ከሳኦል ላይ ታማኝ ፍቅሬን እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አይወሰድም። 16 ቤትህና መንግሥትህ ለዘላለም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል።”’”+

17 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።+

18 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ገብቶ በይሖዋ ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ኧረ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝስ ቤቴ ምን ስለሆነ ነው?+ 19 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሳያንስ ስለ አገልጋይህ ቤት ገና ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ተናገርክ፤ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ለሰው ዘር ሁሉ የተሰጠ መመሪያ* ነው። 20 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ አገልጋይህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ በሚገባ ታውቀኝ የለ?+ 21 ለቃልህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ* እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል፤ እንዲሁም ለአገልጋይህ ገልጠህለታል።+ 22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በእርግጥም ታላቅ+ የሆንከው ለዚህ ነው። እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። 23 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ አምላክ ሄዶ ለእነሱ ሲል ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን+ በመፈጸም እንዲሁም ስሙን በማስጠራት+ ሕዝቡ አድርጎ ዋጃቸው።+ ከግብፅ ለዋጀኸው ሕዝብ ስትል ብሔራትንና አማልክታቸውን አባረርክ። 24 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አድርገህ አጸናኸው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+

25 “አሁንም ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ አገልጋይህንና ቤቱን በተመለከተ የገባኸውን ቃል እስከ ወዲያኛው ፈጽም፤ ቃል እንደገባኸውም አድርግ።+ 26 ሰዎች ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ላይ አምላክ ነው’ እንዲሉ ስምህ ለዘላለም ከፍ ከፍ ይበል፤+ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።+ 27 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ‘ለአንተ ቤት* እሠራልሃለሁ’+ በማለት ለአገልጋይህ ራእይ ገልጠህለታል። አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት* ያገኘው በዚህ ምክንያት ነው። 28 አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እውነተኛው አምላክ አንተ ነህ፤ ቃልህ እውነት ነው፤+ ለአገልጋይህም እነዚህን መልካም ነገሮች ለማድረግ ቃል ገብተህለታል። 29 በመሆኑም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በፊትህም ለዘላለም የጸና ይሁን፤+ ምክንያቱም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ ቃል ገብተሃል፤ በአንተም በረከት የአገልጋይህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሁን።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ