የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ላገቡና ላላገቡ ሰዎች የተሰጠ ምክር (1-16)

      • ‘እያንዳንዱ ሰው አምላክ ሲጠራው በነበረበት ሁኔታ ይመላለስ’ (17-24)

      • ያላገቡና መበለቶች (25-40)

        • ነጠላነት ያለው ጥቅም (32-35)

        • “በጌታ ብቻ” አግቡ (39)

1 ቆሮንቶስ 7:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በፆታ ስሜት መንካትን ያመለክታል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 10-11

1 ቆሮንቶስ 7:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ፖርኒያ የተባለው ግሪክኛ ቃል ብዙ ቁጥር። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 5:18, 19
  • +ዘፍ 2:24፤ ዕብ 13:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 156-157

1 ቆሮንቶስ 7:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:10፤ 1ቆሮ 7:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2011፣ ገጽ 17

    10/15/1996፣ ገጽ 16

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 157

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 244

1 ቆሮንቶስ 7:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 16

1 ቆሮንቶስ 7:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 139

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2015፣ ገጽ 27

    10/15/2011፣ ገጽ 17

    10/15/1996፣ ገጽ 16

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 157-158

1 ቆሮንቶስ 7:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 19:10, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 11-12

1 ቆሮንቶስ 7:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:39, 40፤ 9:5

1 ቆሮንቶስ 7:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 4:4, 5፤ 1ጢሞ 5:11, 14

1 ቆሮንቶስ 7:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:32፤ 19:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2018፣ ገጽ 13

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2000፣ ገጽ 28

1 ቆሮንቶስ 7:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 10:11፤ ሉቃስ 16:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2018፣ ገጽ 13

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2012፣ ገጽ 11

    12/15/2000፣ ገጽ 28

1 ቆሮንቶስ 7:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:25, 40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 21-22

    ማመራመር፣ ገጽ 251

1 ቆሮንቶስ 7:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2018፣ ገጽ 13-14

1 ቆሮንቶስ 7:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 16

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2006፣ ገጽ 26-28

1 ቆሮንቶስ 7:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 12:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 16-17

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2012፣ ገጽ 11-12

    12/15/2000፣ ገጽ 28

1 ቆሮንቶስ 7:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 3:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/1995፣ ገጽ 10-11

1 ቆሮንቶስ 7:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:7

1 ቆሮንቶስ 7:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:20
  • +ሥራ 10:45፤ 15:1, 24፤ ገላ 5:2

1 ቆሮንቶስ 7:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 6:15፤ ቆላ 3:11
  • +መክ 12:13፤ ኤር 7:23፤ ሮም 2:25፤ ገላ 5:6፤ 1ዮሐ 5:3

1 ቆሮንቶስ 7:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:17

1 ቆሮንቶስ 7:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 3:28

1 ቆሮንቶስ 7:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 8:36፤ ፊል 15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1636

1 ቆሮንቶስ 7:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 6:19, 20፤ ዕብ 9:12፤ 1ጴጥ 1:18, 19

1 ቆሮንቶስ 7:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አግብተው የማያውቁትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:12, 40

1 ቆሮንቶስ 7:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 11

1 ቆሮንቶስ 7:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 2:16፤ ማቴ 19:6፤ ኤፌ 5:33

1 ቆሮንቶስ 7:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 184

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    7/2020፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2017፣ ገጽ 4-6

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2015፣ ገጽ 18-19

    10/15/2011፣ ገጽ 15-16

    4/15/2008፣ ገጽ 20

    5/1/2007፣ ገጽ 19

    9/15/2006፣ ገጽ 28-29

    2/15/1999፣ ገጽ 4

    10/15/1996፣ ገጽ 19

    6/15/1995፣ ገጽ 29-30

1 ቆሮንቶስ 7:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 13:11፤ 1ጴጥ 4:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 17

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2008፣ ገጽ 27

    7/15/2000፣ ገጽ 30-31

    10/1/1999፣ ገጽ 9

    10/15/1996፣ ገጽ 19

1 ቆሮንቶስ 7:31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 17

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2015፣ ገጽ 20

    11/15/2011፣ ገጽ 19

    11/15/2010፣ ገጽ 24

    1/15/2008፣ ገጽ 17-19

    10/1/2007፣ ገጽ 19

    2/1/2004፣ ገጽ 18-19

    2/1/2003፣ ገጽ 6

    10/15/1996፣ ገጽ 19

1 ቆሮንቶስ 7:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 12-14

1 ቆሮንቶስ 7:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 5:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2008፣ ገጽ 27

    10/15/1996፣ ገጽ 16

1 ቆሮንቶስ 7:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 5:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2008፣ ገጽ 27

    10/15/1996፣ ገጽ 16-17

1 ቆሮንቶስ 7:35

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ማነቆ ውስጥ ላስገባችሁ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1996፣ ገጽ 12-14

    6/15/1995፣ ገጽ 29

1 ቆሮንቶስ 7:36

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከድንግልናው ጋር በሚስማማ ሁኔታ በአግባቡ መኖር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 19:12፤ 1ቆሮ 7:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 31

    2/15/1999፣ ገጽ 5-6

    10/15/1996፣ ገጽ 14

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 15-16

1 ቆሮንቶስ 7:37

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ድንግልናውን ጠብቆ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 19:10, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2011፣ ገጽ 17

1 ቆሮንቶስ 7:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ድንግልናውን በጋብቻ የሚሰጥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:32

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2012፣ ገጽ 20

    10/15/2011፣ ገጽ 17

    6/15/1995፣ ገጽ 29-30

1 ቆሮንቶስ 7:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 7:2
  • +ዘፍ 24:2, 3፤ ዘዳ 7:3, 4፤ ነህ 13:25, 26፤ 2ቆሮ 6:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    9/2022፣ ገጽ 4

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    በአምላክ ፍቅር ኑሩ፣ ገጽ 134-135

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2015፣ ገጽ 30-32

    1/15/2015፣ ገጽ 31-32

    10/15/2011፣ ገጽ 15

    3/15/2008፣ ገጽ 8

    7/1/2004፣ ገጽ 30-31

    8/15/2001፣ ገጽ 30

    5/15/2001፣ ገጽ 20-21

    ንቁ!፣

    10/8/1999፣ ገጽ 25

    8/8/1999፣ ገጽ 27-29

    3/8/1998፣ ገጽ 20

    4/8/1995፣ ገጽ 7

1 ቆሮንቶስ 7:40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1997፣ ገጽ 6

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 7:2ምሳሌ 5:18, 19
1 ቆሮ. 7:2ዘፍ 2:24፤ ዕብ 13:4
1 ቆሮ. 7:3ዘፀ 21:10፤ 1ቆሮ 7:5
1 ቆሮ. 7:7ማቴ 19:10, 11
1 ቆሮ. 7:81ቆሮ 7:39, 40፤ 9:5
1 ቆሮ. 7:91ተሰ 4:4, 5፤ 1ጢሞ 5:11, 14
1 ቆሮ. 7:10ማቴ 5:32፤ 19:6
1 ቆሮ. 7:11ማር 10:11፤ ሉቃስ 16:18
1 ቆሮ. 7:121ቆሮ 7:25, 40
1 ቆሮ. 7:15ዕብ 12:14
1 ቆሮ. 7:161ጴጥ 3:1, 2
1 ቆሮ. 7:171ቆሮ 7:7
1 ቆሮ. 7:18ሥራ 21:20
1 ቆሮ. 7:18ሥራ 10:45፤ 15:1, 24፤ ገላ 5:2
1 ቆሮ. 7:19ገላ 6:15፤ ቆላ 3:11
1 ቆሮ. 7:19መክ 12:13፤ ኤር 7:23፤ ሮም 2:25፤ ገላ 5:6፤ 1ዮሐ 5:3
1 ቆሮ. 7:201ቆሮ 7:17
1 ቆሮ. 7:21ገላ 3:28
1 ቆሮ. 7:22ዮሐ 8:36፤ ፊል 15, 16
1 ቆሮ. 7:231ቆሮ 6:19, 20፤ ዕብ 9:12፤ 1ጴጥ 1:18, 19
1 ቆሮ. 7:251ቆሮ 7:12, 40
1 ቆሮ. 7:27ሚል 2:16፤ ማቴ 19:6፤ ኤፌ 5:33
1 ቆሮ. 7:29ሮም 13:11፤ 1ጴጥ 4:7
1 ቆሮ. 7:331ጢሞ 5:8
1 ቆሮ. 7:341ጢሞ 5:5
1 ቆሮ. 7:36ማቴ 19:12፤ 1ቆሮ 7:28
1 ቆሮ. 7:37ማቴ 19:10, 11
1 ቆሮ. 7:381ቆሮ 7:32
1 ቆሮ. 7:39ሮም 7:2
1 ቆሮ. 7:39ዘፍ 24:2, 3፤ ዘዳ 7:3, 4፤ ነህ 13:25, 26፤ 2ቆሮ 6:14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 7:1-40

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

7 በደብዳቤያችሁ ላይ ያነሳችኋቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ፣ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ባይነካ* ይሻላል፤ 2 ይሁንና የፆታ ብልግና* ስለተስፋፋ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤+ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት።+ 3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ ሚስትም ብትሆን ለባሏ እንደዚሁ ታድርግለት።+ 4 ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ያለው ባሏ ነው፤ በተመሳሳይም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ናት። 5 አንዳችሁ ለሌላው የሚገባውን አትከልክሉ፤ እንዲህ ማድረግ የምትችሉት በጋራ ስምምነት የተወሰነ ጊዜ ለጸሎት ለማዋል ካሰባችሁ ብቻ ነው፤ ደግሞም ራሳችሁን መግዛት አቅቷችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ። 6 ይሁን እንጂ ይህን ያልኩት እንዲህ ማድረግ እንደሚቻል ለመግለጽ ነው እንጂ ለማዘዝ አይደለም። 7 ይሁንና ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ያገኘው የራሱ ስጦታ አለው፤+ አንዱ አንድ ዓይነት ስጦታ ሲኖረው ሌላው ደግሞ ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።

8 ሆኖም ላላገቡና መበለት ለሆኑ እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ የተሻለ ነው እላለሁ።+ 9 ራሳቸውን መግዛት ካቃታቸው ግን ያግቡ፤ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና።+

10 ላገቡት ሰዎች ይህን መመሪያ እሰጣለሁ፤ ይህ መመሪያ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም፤ ሚስት ከባሏ አትለያይ።+ 11 ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን መተው የለበትም።+

12 ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህን የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም፦+ አንድ ወንድም አማኝ ያልሆነች ሚስት ካለችውና አብራው ለመኖር ከተስማማች አይተዋት፤ 13 እንዲሁም አንዲት ሴት አማኝ ያልሆነ ባል ካላትና ባሏ አብሯት ለመኖር ከተስማማ አትተወው። 14 አማኝ ያልሆነ ባል ከሚስቱ ጋር ባለው ዝምድና የተነሳ ተቀድሷልና፤ አማኝ ያልሆነች ሚስትም ከወንድም ጋር ባላት ዝምድና የተነሳ ተቀድሳለች፤ እንዲህ ባይሆን ኖሮ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው። 15 ይሁንና አማኝ ያልሆነው ወገን ለመለየት ከመረጠ ይለይ፤ እንዲህ ያለ ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት ምንም ዓይነት ግዴታ የለባቸውም፤ አምላክ የጠራችሁ ለሰላም ነውና።+ 16 አንቺ ሚስት፣ ባልሽን ታድኚው እንደሆነ ምን ታውቂያለሽ?+ ወይስ አንተ ባል፣ ሚስትህን ታድን እንደሆነ ምን ታውቃለህ?

17 ያም ሆነ ይህ እያንዳንዱ ሰው ይሖዋ* በሰጠው ድርሻና አምላክ ሲጠራው በነበረበት ሁኔታ ይመላለስ።+ ለጉባኤዎችም ሁሉ ይህን መመሪያ እሰጣለሁ። 18 አንድ ሰው የተጠራው ተገርዞ እያለ ነው?+ እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን። አንድ ሰው የተጠራው ሳይገረዝ ነው? ከሆነ አይገረዝ።+ 19 መገረዝ ምንም ማለት አይደለም፤ አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤+ ዋናው ነገር የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ነው።+ 20 እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዚያው ይቀጥል።+ 21 የተጠራኸው ባሪያ እያለህ ነው? ይሄ አያስጨንቅህ፤+ ሆኖም ነፃ መውጣት የምትችል ከሆነ አጋጣሚውን ተጠቀምበት። 22 ባሪያ እያለ የተጠራ ማንኛውም የጌታ ደቀ መዝሙር ነፃ የወጣ የጌታ ሰው ነውና፤+ በተመሳሳይም ነፃ እያለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው። 23 በዋጋ ተገዝታችኋል፤+ የሰው ባሪያ መሆናችሁ ይብቃ። 24 ወንድሞች፣ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአምላክ ፊት በዚያው ሁኔታ ይቀጥል።

25 ድንግል የሆኑትን* በተመለከተ ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ይሁን እንጂ ጌታ ካሳየኝ ምሕረት የተነሳ እንደ ታማኝ ሰው የራሴን ሐሳብ እሰጣለሁ።+ 26 ስለዚህ አሁን ካለው ችግር አንጻር አንድ ሰው ባለበት ሁኔታ ቢቀጥል የተሻለ ይመስለኛል። 27 በሚስት ታስረሃል? ከሆነ መፈታትን አትሻ።+ ሚስት የሌለህ ነህ? ከሆነ ሚስት ለማግባት አትፈልግ። 28 ይሁንና ብታገባም ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም። እንዲሁም ድንግል የሆነ ሰው ቢያገባ ኃጢአት ይሆንበታል ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በሥጋቸው ላይ መከራ ይደርስባቸዋል። ነገር ግን የእኔ ምኞት ከዚህ እንድትድኑ ነው።

29 ከዚህም በላይ ወንድሞች፣ የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ።+ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያላቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፤ 30 የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፣ የሚደሰቱም እንደማይደሰቱ፣ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው 31 እንዲሁም በዓለም የሚጠቀሙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ፤ የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነውና። 32 በመሆኑም ከጭንቀት ነፃ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። ያላገባ ሰው ጌታን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ጌታ ነገር ይጨነቃል። 33 ያገባ ሰው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ይጨነቃል፤+ 34 በመሆኑም ሐሳቡ ተከፋፍሏል። በተጨማሪም ያላገባች ሴትም ሆነች ድንግል በአካሏም ሆነ በመንፈሷ ቅዱስ መሆን ትችል ዘንድ ስለ ጌታ ነገር ትጨነቃለች።+ ይሁን እንጂ ያገባች ሴት ባሏን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደምትችል በማሰብ ስለ ዓለም ነገር ትጨነቃለች። 35 ይህን የምለው ግን ለእናንተው ጥቅም ብዬ ነው እንጂ ነፃነት ላሳጣችሁ* ብዬ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ተስማሚ የሆነውን ነገር እንድታደርጉና ሐሳባችሁ ሳይከፋፈል ዘወትር ለጌታ ያደራችሁ እንድትሆኑ ላነሳሳችሁ ብዬ ነው።

36 ይሁንና አንድ ሰው ሳያገባ ቀርቶ ራሱን መቆጣጠር* እንደተሳነው ከተሰማው፣ በተለይ ደግሞ አፍላ የጉርምስና ዕድሜን ያለፈ ከሆነና ማግባቱ የሚመረጥ ከሆነ የፈለገውን ያድርግ፤ ኃጢአት አይሆንበትም። እንዲህ ያሉ ሰዎች ያግቡ።+ 37 ሆኖም አንድ ሰው ልቡ ከቆረጠና ይህን ማድረግ እንደማያስፈልገው ከተሰማው፣ ደግሞም ራሱን መግዛት የሚችል ከሆነና ሳያገባ* ለመኖር በልቡ ከወሰነ መልካም ያደርጋል።+ 38 ስለዚህ የሚያገባ* ሁሉ መልካም ያደርጋል፤ ሳያገባ የሚኖር ሁሉ ደግሞ የተሻለ ያደርጋል።+

39 አንዲት ሚስት ባሏ በሕይወት ባለበት ዘመን ሁሉ የታሰረች ናት።+ ባሏ በሞት ካንቀላፋ ግን በጌታ ብቻ ይሁን እንጂ ከፈለገችው ሰው ጋር ለመጋባት ነፃ ናት።+ 40 እንደ እኔ ከሆነ ግን እንዳለች ብትቀጥል ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች፤ እኔ ደግሞ የአምላክ መንፈስ እንዳለኝ እርግጠኛ ነኝ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ