የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ፊልጵስዩስ 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ፊልጵስዩስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ሰላምታ (1, 2)

      • ለአምላክ የቀረበ ምስጋና፤ የጳውሎስ ጸሎት (3-11)

      • አስቸጋሪ ሁኔታ ቢኖርም ምሥራቹ ተስፋፋ (12-20)

      • ‘የምኖረው ለክርስቶስ ነው፤ ብሞት ደግሞ እጠቀማለሁ’ (21-26)

      • ‘አኗኗራችሁ ከምሥራቹ ጋር የሚስማማ ይሁን’ (27-30)

ፊልጵስዩስ 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 3:1, 8
  • +ሥራ 16:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የተደራጀ ሕዝብ፣ ገጽ 53

ፊልጵስዩስ 1:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 1:2

ፊልጵስዩስ 1:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምሥራቹን በማስፋፋቱ ሥራ ተሳትፎ።”

ፊልጵስዩስ 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 1:8
  • +ፊልጵ 2:13

ፊልጵስዩስ 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 3:1፤ ፊልጵ 1:13፤ ቆላ 4:18፤ 2ጢሞ 1:8፤ ፊል 13
  • +ሥራ 24:10, 14፤ 25:10-12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    7/2023፣ ገጽ 3

    መመሥከር፣ ገጽ 131-132

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 21

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2015፣ ገጽ 22-23

    8/15/1999፣ ገጽ 21-22

    12/1/1998፣ ገጽ 18

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 14፣ ገጽ 11

ፊልጵስዩስ 1:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 17:3
  • +ዕብ 5:14
  • +1ተሰ 3:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2022፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2019፣ ገጽ 9-10

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1997፣ ገጽ 16-17

    6/15/1995፣ ገጽ 20

ፊልጵስዩስ 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:2
  • +ሮም 14:13, 21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 12

    ንቁ!፣

    ቁጥር 1 2020፣ ገጽ 12

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2019፣ ገጽ 10-11

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2008፣ ገጽ 24

    3/15/1997፣ ገጽ 16-17

ፊልጵስዩስ 1:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 15:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2019፣ ገጽ 11-12

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2007፣ ገጽ 24

ፊልጵስዩስ 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 3:1
  • +ሥራ 28:30, 31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2013፣ ገጽ 14-16

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1648

ፊልጵስዩስ 1:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/1991፣ ገጽ 21

ፊልጵስዩስ 1:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 1:7

ፊልጵስዩስ 1:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 1:11
  • +ዮሐ 15:26

ፊልጵስዩስ 1:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 14:8፤ 1ጴጥ 4:16

ፊልጵስዩስ 1:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 2:20
  • +1ተሰ 4:14፤ 2ጢሞ 4:8፤ ራእይ 14:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1995፣ ገጽ 30-31

ፊልጵስዩስ 1:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጢሞ 4:6
  • +2ቆሮ 5:6, 8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2008፣ ገጽ 28

    3/1/1995፣ ገጽ 30-31

ፊልጵስዩስ 1:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዜጎች እንደመሆናችሁ መጠን ስለ ክርስቶስ ከሚገልጸው ምሥራች ጋር በሚስማማ መንገድ ኑሩ።”

  • *

    ወይም “በአንድነት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 4:1, 3፤ ቆላ 1:10
  • +ሮም 15:5, 6፤ 1ቆሮ 1:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2012፣ ገጽ 11-12

    9/15/2010፣ ገጽ 13-14

ፊልጵስዩስ 1:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ተሰ 1:6
  • +ሉቃስ 21:19፤ 2ተሰ 1:4, 5

ፊልጵስዩስ 1:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 5:41

ፊልጵስዩስ 1:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:22, 23፤ 1ተሰ 2:2

ተዛማጅ ሐሳብ

ፊልጵ. 1:11ጢሞ 3:1, 8
ፊልጵ. 1:1ሥራ 16:12
ፊልጵ. 1:41ተሰ 1:2
ፊልጵ. 1:61ቆሮ 1:8
ፊልጵ. 1:6ፊልጵ 2:13
ፊልጵ. 1:7ኤፌ 3:1፤ ፊልጵ 1:13፤ ቆላ 4:18፤ 2ጢሞ 1:8፤ ፊል 13
ፊልጵ. 1:7ሥራ 24:10, 14፤ 25:10-12
ፊልጵ. 1:9ዮሐ 17:3
ፊልጵ. 1:9ዕብ 5:14
ፊልጵ. 1:91ተሰ 3:12
ፊልጵ. 1:10ሮም 12:2
ፊልጵ. 1:10ሮም 14:13, 21
ፊልጵ. 1:11ዮሐ 15:5
ፊልጵ. 1:13ኤፌ 3:1
ፊልጵ. 1:13ሥራ 28:30, 31
ፊልጵ. 1:16ፊልጵ 1:7
ፊልጵ. 1:192ቆሮ 1:11
ፊልጵ. 1:19ዮሐ 15:26
ፊልጵ. 1:20ሮም 14:8፤ 1ጴጥ 4:16
ፊልጵ. 1:21ገላ 2:20
ፊልጵ. 1:211ተሰ 4:14፤ 2ጢሞ 4:8፤ ራእይ 14:13
ፊልጵ. 1:232ጢሞ 4:6
ፊልጵ. 1:232ቆሮ 5:6, 8
ፊልጵ. 1:27ኤፌ 4:1, 3፤ ቆላ 1:10
ፊልጵ. 1:27ሮም 15:5, 6፤ 1ቆሮ 1:10
ፊልጵ. 1:282ተሰ 1:6
ፊልጵ. 1:28ሉቃስ 21:19፤ 2ተሰ 1:4, 5
ፊልጵ. 1:29ሥራ 5:41
ፊልጵ. 1:30ሥራ 16:22, 23፤ 1ተሰ 2:2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ፊልጵስዩስ 1:1-30

ለፊልጵስዩስ ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ

1 የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያዎች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፣ ሽማግሌዎችንና የጉባኤ አገልጋዮችን+ ጨምሮ በፊልጵስዩስ+ ለሚገኙ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ቅዱሳን ሁሉ፦

2 አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

3 እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ 4 ይህን የማደርገው ስለ እያንዳንዳችሁ ምልጃ ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉ ነው። ደግሞም ምንጊዜም ምልጃ የማቀርበው በደስታ ነው፤+ 5 ምክንያቱም ምሥራቹን ከሰማችሁበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ለምሥራቹ አስተዋጽኦ* ስታደርጉ ቆይታችኋል። 6 በእናንተ መካከል መልካም ሥራ የጀመረው አምላክ፣ ሥራውን እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን+ ድረስ ወደ ፍጻሜ እንደሚያመጣው እርግጠኛ ነኝ።+ 7 ስለ እናንተ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ብዬ ማሰቤ ትክክል ነው፤ ምክንያቱም በእስራቴም+ ሆነ ለምሥራቹ ስሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ለማድረግ ስጥር+ ከእኔ ጋር የጸጋው ተካፋዮች የሆናችሁት እናንተ በልቤ ውስጥ ናችሁ።

8 ክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ዓይነት ጥልቅ ፍቅር እናንተ ሁላችሁም በጣም እንደምትናፍቁኝ አምላክ ምሥክሬ ነው። 9 ፍቅራችሁ ከአምላክ ፈቃድ ትክክለኛ እውቀትና+ ጥልቅ ግንዛቤ+ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲሄድ መጸለዬን እቀጥላለሁ፤+ 10 ደግሞም ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ በማወቅ+ እስከ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንከን የማይገኝባችሁ እንድትሆኑና ሌሎችን እንዳታሰናክሉ+ 11 እንዲሁም ለአምላክ ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተትረፈረፈ የጽድቅ ፍሬ እንድታፈሩ እጸልያለሁ።+

12 እንግዲህ ወንድሞች፣ እኔ ያጋጠመኝ ሁኔታ ምሥራቹ ይበልጥ እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ፤ 13 የታሰርኩት+ የክርስቶስ አገልጋይ በመሆኔ የተነሳ እንደሆነ በንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘብ ሁሉና በሌሎች ሰዎች ሁሉ ዘንድ በይፋ ታውቋል።+ 14 ጌታን የሚያገለግሉ አብዛኞቹ ወንድሞች በእኔ መታሰር ምክንያት የልበ ሙሉነት ስሜት አድሮባቸው የአምላክን ቃል ያለፍርሃት ለመናገር ከቀድሞው የበለጠ ድፍረት እያሳዩ ነው።

15 እርግጥ፣ አንዳንዶች ክርስቶስን እየሰበኩ ያሉት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ ይሁንና ሌሎች ይህን እያደረጉ ያሉት በጥሩ ዓላማ ነው። 16 እነዚህ፣ እኔ ለምሥራቹ ለመሟገት+ እንደተሾምኩ ስለሚያውቁ ስለ ክርስቶስ የሚያውጁት ከፍቅር ተነሳስተው ነው፤ 17 እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ ችግር ሊፈጥሩብኝ ስላሰቡ ይህን የሚያደርጉት በቅን ልቦና ሳይሆን በጥላቻ ተነሳስተው ነው። 18 ታዲያ ይህ ምን አስከተለ? በማስመሰልም ሆነ በእውነት፣ በሁሉም መንገድ ክርስቶስ እንዲሰበክ አስችሏል፤ በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ። ወደፊትም ቢሆን መደሰቴን እቀጥላለሁ፤ 19 ይህ በእናንተ ምልጃ+ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በሚሰጠኝ ድጋፍ+ መዳን እንደሚያስገኝልኝ አውቃለሁና። 20 ይህም በጉጉት ከምጠባበቀው ነገርና ከተስፋዬ ጋር በሚስማማ ሁኔታ በማንኛውም መንገድ እንዳላፍር ነው፤ ከዚህ ይልቅ በነፃነት በመናገር በሕይወትም ሆነ በሞት እንደ ወትሮው ሁሉ አሁንም ክርስቶስን በሰውነቴ አማካኝነት ከፍ ከፍ አደርገው ዘንድ ነው።+

21 እኔ ብኖር የምኖረው ለክርስቶስ ነውና፤+ ብሞት ደግሞ እጠቀማለሁ።+ 22 በሥጋ መኖሬን የምቀጥል ከሆነ በማከናውነው ሥራ አማካኝነት ብዙ ፍሬ ማፍራት እችላለሁ፤ ይሁንና የትኛውን እንደምመርጥ አላሳውቅም። 23 በእነዚህ ሁለት ነገሮች አጣብቂኝ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ምኞቴ ነፃ መለቀቅና ከክርስቶስ ጋር መሆን ነውና፤+ እርግጡን ለመናገር ይህ እጅግ የተሻለ ነው።+ 24 ይሁን እንጂ ለእናንተ ሲባል በሥጋ መኖሬ ይበልጥ አስፈላጊ ነው። 25 በመሆኑም በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ ስለሆንኩ እድገት እንድታደርጉና በእምነት ደስታ እንድታገኙ ስል በሥጋ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር መኖሬን እንደምቀጥል አውቃለሁ፤ 26 ይህም ዳግመኛ በእናንተ መካከል ስገኝ በእኔ ምክንያት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ ደስታችሁ ይትረፈረፍ ዘንድ ነው።

27 ብቻ አኗኗራችሁ ስለ ክርስቶስ ከሚገልጸው ምሥራች ጋር የሚስማማ ይሁን፤*+ ይህም መጥቼ ባያችሁም ሆነ ከእናንተ ብርቅ አንድ ላይ ሆናችሁ በምሥራቹ ላይ ያላችሁን እምነት ጠብቃችሁ ለመኖር በአንድ ነፍስ* በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን+ 28 እንዲሁም በምንም መንገድ በጠላቶቻችሁ አለመሸበራችሁን እሰማና አውቅ ዘንድ ነው። ይህ ነገር እነሱ እንደሚጠፉ+ እናንተ ግን እንደምትድኑ የሚያሳይ+ ማስረጃ ነው፤ ይህም ከአምላክ የተሰጠ ነው። 29 እናንተ በክርስቶስ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን ለእሱ ስትሉ መከራ እንድትቀበሉም መብት ተሰጥቷችኋል።+ 30 እኔ ስጋፈጥ ያያችሁትንና+ አሁንም እየተጋፈጥኩት እንዳለሁ የሰማችሁትን ያንኑ ትግል እናንተም እየተጋፈጣችሁ ነውና።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ