ምሳሌ
1 የእስራኤል ንጉሥ፣+ የዳዊት ልጅ+ የሰለሞን ምሳሌዎች፦+
5 ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤+
ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤+
6 ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልን
እንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።+
ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+
10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።+
11 እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ።
ደም ለማፍሰስ እናድባ።
ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን።
12 እንደ መቃብር፣* በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤
ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን።
13 ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤
ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን።
15 ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው።
17 ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው።
18 እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤
የሰዎችን ሕይወት* ለማጥፋት ያደፍጣሉ።
በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።+
21 ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን* ላይ ሆና ትጣራለች።
በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦+
22 “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ?
እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ?
እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?+
እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤
ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።+
24 በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤
እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤+
25 ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤
ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤
26 እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤
የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤+
27 የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣
ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣
ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ።
28 በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤
አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤+
29 ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤+
ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።+
30 ምክሬን አልተቀበሉም፤
ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል።
32 ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤
ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል።