የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 2:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  8 ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤+

      ሕጉ በአደራ የተሰጣቸውም እኔን አላወቁም፤

      እረኞቹ በእኔ ላይ ዓመፁ፤+

      ነቢያቱ በባአል ስም ትንቢት ተናገሩ፤+

      ምንም ጥቅም የማያስገኙላቸውንም አማልክት ተከተሉ።

  • ኤርምያስ 8:10-12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣

      እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+

      ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+

      ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+

      11 ሰላም ሳይኖር፣

      “ሰላም ነው! ሰላም ነው!” እያሉ

      የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+

      12 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?

      እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!

      ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+

      “‘ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።

      እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ’+ ይላል ይሖዋ።

  • ኤርምያስ 23:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “ነቢዩም ሆነ ካህኑ ተበክለዋል።*+

      በገዛ ቤቴ እንኳ ሳይቀር የሠሩትን ክፋት አግኝቻለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

  • ሚክያስ 3:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣+

      በጥርሳቸው ሲነክሱ*+ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣+

      አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ* ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

  • ሚክያስ 3:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 መሪዎቿ* በጉቦ ይፈርዳሉ፤+

      ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤+

      ነቢያቷም በገንዘብ* ያሟርታሉ።+

      ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም?+

      ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም”+

      እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።*

  • ሶፎንያስ 3:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 ነቢያቷ እብሪተኞችና አታላዮች ናቸው።+

      ካህናቷ ቅዱስ የሆነውን ነገር ያረክሳሉ፤+

      በሕጉ ላይ ያምፃሉ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ