የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 9:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ልጅ ተወልዶልናልና፤+

      ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤

      ገዢነትም* በጫንቃው ላይ ይሆናል።+

      ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል።

       7 በዳዊት ዙፋንና+ በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤

      እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም* ሆነ

      ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም።+

      ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም

      በማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤+

      በፍትሕና+ በጽድቅም+ ጸንቶ ይኖራል።

      የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

  • ኢሳይያስ 16:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  5 ከዚያም ዙፋን በታማኝ ፍቅር ጸንቶ ይመሠረታል።

      በዳዊት ድንኳን ላይ በዙፋኑ የሚቀመጠው ታማኝ ይሆናል፤+

      በትክክል ይፈርዳል፤ ጽድቅንም በቶሎ ያስፈጽማል።”+

  • ኤርምያስ 23:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+

  • ሕዝቅኤል 37:24, 25
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 “‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤+ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል።+ ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።+ 25 አባቶቻችሁ በኖሩባት፣ ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይቀመጣሉ፤+ እነሱና ልጆቻቸው* እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው በእሷ ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤+ አገልጋዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃቸው* ይሆናል።+

  • ዘካርያስ 12:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 በዚያ ቀን ይሖዋ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዙሪያ መከታ ይሆናል፤+ በዚያም ቀን ከእነሱ መካከል የሚሰናከለው* እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት እንደ አምላክ፣ በፊታቸውም እንደሚሄደው የይሖዋ መልአክ ይሆናል።+

  • ሉቃስ 1:31-33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 እነሆም፣ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤+ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።+ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ