የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 46
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7)

      • ወደ ግብፅ የሄዱት ሰዎች ስም ዝርዝር (8-27)

      • ዮሴፍ በጎሸን ከያዕቆብ ጋር ተገናኘ (28-34)

ዘፍጥረት 46:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የእሱ የሆኑትን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 21:31
  • +ዘፍ 31:42፤ ዘፀ 3:6

ዘፍጥረት 46:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:13
  • +ዘፍ 12:1, 2፤ ዘፀ 1:7፤ ዘዳ 26:5

ዘፍጥረት 46:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ ዓይኖቹን መክደንን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 15:16፤ 28:15፤ 47:29, 30፤ 50:13
  • +ዘፍ 50:1

ዘፍጥረት 46:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 1:1-4
  • +ዘፍ 35:23፤ 1ዜና 5:1

ዘፍጥረት 46:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 26:5, 6

ዘፍጥረት 46:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:33
  • +ዘኁ 26:12, 13፤ 1ዜና 4:24

ዘፍጥረት 46:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:34
  • +1ዜና 6:16

ዘፍጥረት 46:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:35፤ ራእይ 5:5
  • +ዘፍ 38:2-5
  • +ሉቃስ 3:23, 33
  • +ዘፍ 38:30
  • +ዘፍ 38:7, 9, 10
  • +ዘኁ 26:21፤ 1ዜና 2:5

ዘፍጥረት 46:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 26:23, 24፤ 1ዜና 7:1

ዘፍጥረት 46:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:20
  • +ዘኁ 26:26

ዘፍጥረት 46:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ነፍስ ሁሉ 33 ነበር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:21

ዘፍጥረት 46:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:11
  • +ዘኁ 26:15-17

ዘፍጥረት 46:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:13
  • +ዘኁ 26:44, 45

ዘፍጥረት 46:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “16 ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:24

ዘፍጥረት 46:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:24
  • +ዘፍ 35:18

ዘፍጥረት 46:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም አምስት ተጨማሪ ስሞችን ይጠቅሳል። እስጢፋኖስ በሥራ 7:14 ላይ 70 ነፍስ በማለት ፋንታ 75 ነፍስ ያለው ከዚህ ትርጉም ስለጠቀሰ ሊሆን ይችላል።

  • *

    ሂልያፖሊስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 41:51
  • +ዘፍ 41:52
  • +ዘፍ 41:50

ዘፍጥረት 46:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 7:6
  • +1ዜና 8:1, 3
  • +1ዜና 7:12
  • +ዘኁ 26:38-40

ዘፍጥረት 46:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “14 ነፍስ።”

ዘፍጥረት 46:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:6
  • +ዘኁ 26:42

ዘፍጥረት 46:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:8
  • +ዘኁ 26:48, 49

ዘፍጥረት 46:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰባት ነፍስ።”

ዘፍጥረት 46:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሳት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 35:10, 11

ዘፍጥረት 46:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሁለት ነፍስ።”

  • *

    ወይም “70 ነፍስ።” የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም “ሰባ አምስት” ነፍስ ይላል። ዘፍ 46:20 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 1:5፤ ዘዳ 10:22፤ ሥራ 7:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2002፣ ገጽ 27

ዘፍጥረት 46:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 43:8፤ 44:18
  • +ዘፍ 45:10፤ 47:1

ዘፍጥረት 46:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 41:39, 40
  • +ዘፍ 45:19፤ ሥራ 7:13

ዘፍጥረት 46:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 31:17, 18፤ 47:3
  • +ዘፍ 31:38
  • +ዘፍ 46:6

ዘፍጥረት 46:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:35, 36
  • +ዘፍ 43:32
  • +ዘፍ 45:17, 18፤ 47:27

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 46:1ዘፍ 21:31
ዘፍ. 46:1ዘፍ 31:42፤ ዘፀ 3:6
ዘፍ. 46:3ዘፍ 28:13
ዘፍ. 46:3ዘፍ 12:1, 2፤ ዘፀ 1:7፤ ዘዳ 26:5
ዘፍ. 46:4ዘፍ 15:16፤ 28:15፤ 47:29, 30፤ 50:13
ዘፍ. 46:4ዘፍ 50:1
ዘፍ. 46:8ዘፀ 1:1-4
ዘፍ. 46:8ዘፍ 35:23፤ 1ዜና 5:1
ዘፍ. 46:9ዘኁ 26:5, 6
ዘፍ. 46:10ዘፍ 29:33
ዘፍ. 46:10ዘኁ 26:12, 13፤ 1ዜና 4:24
ዘፍ. 46:11ዘፍ 29:34
ዘፍ. 46:111ዜና 6:16
ዘፍ. 46:12ዘፍ 29:35፤ ራእይ 5:5
ዘፍ. 46:12ዘፍ 38:2-5
ዘፍ. 46:12ሉቃስ 3:23, 33
ዘፍ. 46:12ዘፍ 38:30
ዘፍ. 46:12ዘፍ 38:7, 9, 10
ዘፍ. 46:12ዘኁ 26:21፤ 1ዜና 2:5
ዘፍ. 46:13ዘኁ 26:23, 24፤ 1ዜና 7:1
ዘፍ. 46:14ዘፍ 30:20
ዘፍ. 46:14ዘኁ 26:26
ዘፍ. 46:15ዘፍ 30:21
ዘፍ. 46:16ዘፍ 30:11
ዘፍ. 46:16ዘኁ 26:15-17
ዘፍ. 46:17ዘፍ 30:13
ዘፍ. 46:17ዘኁ 26:44, 45
ዘፍ. 46:18ዘፍ 29:24
ዘፍ. 46:19ዘፍ 30:24
ዘፍ. 46:19ዘፍ 35:18
ዘፍ. 46:20ዘፍ 41:51
ዘፍ. 46:20ዘፍ 41:52
ዘፍ. 46:20ዘፍ 41:50
ዘፍ. 46:211ዜና 7:6
ዘፍ. 46:211ዜና 8:1, 3
ዘፍ. 46:211ዜና 7:12
ዘፍ. 46:21ዘኁ 26:38-40
ዘፍ. 46:23ዘፍ 30:6
ዘፍ. 46:23ዘኁ 26:42
ዘፍ. 46:24ዘፍ 30:8
ዘፍ. 46:24ዘኁ 26:48, 49
ዘፍ. 46:26ዘፍ 35:10, 11
ዘፍ. 46:27ዘፀ 1:5፤ ዘዳ 10:22፤ ሥራ 7:14
ዘፍ. 46:28ዘፍ 43:8፤ 44:18
ዘፍ. 46:28ዘፍ 45:10፤ 47:1
ዘፍ. 46:31ዘፍ 41:39, 40
ዘፍ. 46:31ዘፍ 45:19፤ ሥራ 7:13
ዘፍ. 46:32ዘፍ 31:17, 18፤ 47:3
ዘፍ. 46:32ዘፍ 31:38
ዘፍ. 46:32ዘፍ 46:6
ዘፍ. 46:34ዘፍ 30:35, 36
ዘፍ. 46:34ዘፍ 43:32
ዘፍ. 46:34ዘፍ 45:17, 18፤ 47:27
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 46:1-34

ዘፍጥረት

46 በመሆኑም እስራኤል ያለውን* ሁሉ ይዞ ተነሳ። ቤርሳቤህ+ በደረሰ ጊዜም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ+ መሥዋዕቶችን አቀረበ። 2 ከዚያም አምላክ ለእስራኤል ሌሊት በራእይ ተገልጦለት “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት!” አለ። 3 አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ።+ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።+ 4 እኔ ራሴ ከአንተ ጋር ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፤ ደግሞም እኔ ራሴ ከዚያ አወጣሃለሁ፤+ ዮሴፍም ዓይኖችህን በእጁ ይከድናል።”*+

5 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሳ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን በላከለት ሠረገሎች ላይ አሳፍረው ጉዞ ጀመሩ። 6 እነሱም በከነአን ምድር ያፈሩትን ንብረትና መንጎቻቸውን ይዘው ሄዱ። ከዚያም ያዕቆብና ከእሱ ጋር የነበሩት ልጆቹ በሙሉ ወደ ግብፅ መጡ። 7 እሱም ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ይኸውም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ወደ ግብፅ መጣ።

8 ወደ ግብፅ የመጡት የእስራኤል ማለትም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦+ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል።+

9 የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ።+

10 የስምዖን+ ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እንዲሁም ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ።+

11 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ።+

12 የይሁዳ+ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን፣ ሴሎም፣+ ፋሬስ+ እና ዛራ+ ነበሩ፤ ይሁንና ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ።+

የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል ነበሩ።+

13 የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑዋ፣ ዮብ እና ሺምሮን ነበሩ።+

14 የዛብሎን+ ወንዶች ልጆች ሰሬድ፣ ኤሎን እና ያህልኤል ነበሩ።+

15 ሴት ልጁን ዲናን+ ጨምሮ እነዚህ ሊያ በጳዳንአራም ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆች ናቸው። በአጠቃላይ ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ 33 ነበሩ።*

16 የጋድ+ ወንዶች ልጆች ጺፍዮን፣ ሃጊ፣ ሹኒ፣ ኤጽቦን፣ ኤሪ፣ አሮድ እና አርዔላይ ነበሩ።+

17 የአሴር+ ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች።

የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና ማልኪኤል ነበሩ።+

18 ላባ ለልጁ ለሊያ የሰጣት ዚልጳ+ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ 16* ነበሩ።

19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ወንዶች ልጆች ዮሴፍና+ ቢንያም+ ነበሩ።

20 ዮሴፍ በግብፅ ምድር ሳለ ምናሴንና+ ኤፍሬምን*+ ወለደ፤ እነዚህም የኦን* ካህን የሆነው የጶጥፌራ ልጅ አስናት+ የወለደችለት ናቸው።

21 የቢንያም+ ወንዶች ልጆች ቤላ፣ ቤኬር፣ አሽቤል፣ ጌራ፣+ ንዕማን፣ ኤሂ፣ ሮሽ፣ ሙጲም፣ ሁፒም+ እና አርድ+ ነበሩ።

22 እነዚህ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ወንዶች ልጆች ናቸው፤ እነሱም በአጠቃላይ 14* ነበሩ።

23 የዳን+ ልጅ* ሁሺም+ ነበር።

24 የንፍታሌም+ ወንዶች ልጆች ያህጽኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሺሌም ነበሩ።+

25 ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት ባላ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ ሰባት* ነበሩ።

26 የያዕቆብ ዝርያዎች የሆኑትና ከእሱ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች፣* የልጆቹን ሚስቶች ሳይጨምር በአጠቃላይ 66 ነበሩ።+ 27 ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሁለት* ነበሩ። ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተሰቦች በአጠቃላይ 70* ነበሩ።+

28 ያዕቆብ ወደ ጎሸን እየሄደ መሆኑን ለዮሴፍ እንዲነግረው ይሁዳን+ ከእሱ አስቀድሞ ላከው። ወደ ጎሸን ምድር+ በደረሱም ጊዜ 29 ዮሴፍ ሠረገላው እንዲዘጋጅለት ካደረገ በኋላ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጎሸን ሄደ። ባገኘውም ጊዜ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ረዘም ላለ ጊዜ አለቀሰ። 30 ከዚያም እስራኤል ዮሴፍን “ከእንግዲህ ብሞት አይቆጨኝም፤ ዓይንህን ለማየት በቅቻለሁ፤ በሕይወት መኖርህንም አረጋግጫለሁ” አለው።

31 ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተሰቦች እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ ሁኔታውን ልንገረው፤+ እንዲህም ልበለው፦ ‘በከነአን ምድር ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተሰቦች ወደ እኔ መጥተዋል።+ 32 እነሱ እረኞችና+ ከብት አርቢዎች+ ናቸው፤ መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’+ 33 እንግዲህ ፈርዖን ጠርቶ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቃችሁ 34 ‘እኛ አገልጋዮችህም ሆን የቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ ከብት አርቢዎች ነን’ በሉት።+ ግብፃውያን በግ ጠባቂዎችን ስለሚጸየፉ+ በጎሸን ምድር እንድትኖሩ+ ይፈቅድላችኋል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ