የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • በጳውሎስ ላይ የቀረቡ ክሶች (1-9)

      • ጳውሎስ በፊሊክስ ፊት የመከላከያ መልስ ሰጠ (10-21)

      • የጳውሎስ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ለሁለት ዓመት ቆየ (22-27)

የሐዋርያት ሥራ 24:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 23:2
  • +ሥራ 23:26

የሐዋርያት ሥራ 24:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 192

የሐዋርያት ሥራ 24:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 192

የሐዋርያት ሥራ 24:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ችግር ፈጣሪ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:11፤ ሥራ 16:20, 21፤ 17:6, 7
  • +ሉቃስ 23:1, 2
  • +ማቴ 2:23፤ ሥራ 28:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 192

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 22-23

የሐዋርያት ሥራ 24:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:27, 28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 192

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 22-23

የሐዋርያት ሥራ 24:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።

የሐዋርያት ሥራ 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 1:7

የሐዋርያት ሥራ 24:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:17, 26

የሐዋርያት ሥራ 24:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 28:23፤ ሮም 3:21
  • +ዘፀ 3:15፤ ሥራ 3:13፤ 2ጢሞ 1:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 13-14

የሐዋርያት ሥራ 24:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 23:43
  • +ኢሳ 26:19፤ ማቴ 22:31, 32፤ ሉቃስ 14:13, 14፤ ዮሐ 5:28, 29፤ 11:25፤ ዕብ 11:35፤ ራእይ 20:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 77

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2022፣ ገጽ 16-18, 20, 22, 26

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 30

    ንቁ!፣

    ቁጥር 1 2021፣ ገጽ 13

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2020፣ ገጽ 7

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2015፣ ገጽ 6

    6/1/2014፣ ገጽ 10-11

    3/15/2012፣ ገጽ 11

    6/15/2006፣ ገጽ 6

    7/15/2001፣ ገጽ 6

    7/15/2000፣ ገጽ 13-14

    4/1/1999፣ ገጽ 18

    7/1/1998፣ ገጽ 22

    2/15/1995፣ ገጽ 8-12

    8/1/1991፣ ገጽ 6

    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?፣ ገጽ 77-79

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ገጽ 72-73

    ራእይ፣ ገጽ 297-298

    ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ ገጽ 27

    እውቀት፣ ገጽ 185-187

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 170-172, 179-180

    ማመራመር፣ ገጽ 246, 339

የሐዋርያት ሥራ 24:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እንከን የለሽ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 23:1፤ 1ቆሮ 4:4፤ ዕብ 13:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2005፣ ገጽ 14-15

የሐዋርያት ሥራ 24:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 8:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 169

የሐዋርያት ሥራ 24:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:24, 26

የሐዋርያት ሥራ 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 25:16

የሐዋርያት ሥራ 24:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 23:6

የሐዋርያት ሥራ 24:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 9:1, 2፤ 19:9

የሐዋርያት ሥራ 24:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 194-195

የሐዋርያት ሥራ 24:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:30, 31፤ 2ቆሮ 5:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 194-195

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/1993፣ ገጽ 17-19

የሐዋርያት ሥራ 24:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 23

የሐዋርያት ሥራ 24:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 25:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 195

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 24:1ሥራ 23:2
ሥራ 24:1ሥራ 23:26
ሥራ 24:5ማቴ 5:11፤ ሥራ 16:20, 21፤ 17:6, 7
ሥራ 24:5ሉቃስ 23:1, 2
ሥራ 24:5ማቴ 2:23፤ ሥራ 28:22
ሥራ 24:6ሥራ 21:27, 28
ሥራ 24:10ፊልጵ 1:7
ሥራ 24:11ሥራ 21:17, 26
ሥራ 24:14ሥራ 28:23፤ ሮም 3:21
ሥራ 24:14ዘፀ 3:15፤ ሥራ 3:13፤ 2ጢሞ 1:3
ሥራ 24:15ሉቃስ 23:43
ሥራ 24:15ኢሳ 26:19፤ ማቴ 22:31, 32፤ ሉቃስ 14:13, 14፤ ዮሐ 5:28, 29፤ 11:25፤ ዕብ 11:35፤ ራእይ 20:12
ሥራ 24:16ሥራ 23:1፤ 1ቆሮ 4:4፤ ዕብ 13:18
ሥራ 24:172ቆሮ 8:4
ሥራ 24:18ሥራ 21:24, 26
ሥራ 24:19ሥራ 25:16
ሥራ 24:21ሥራ 23:6
ሥራ 24:22ሥራ 9:1, 2፤ 19:9
ሥራ 24:24ማቴ 10:18
ሥራ 24:25ሥራ 17:30, 31፤ 2ቆሮ 5:10
ሥራ 24:27ሥራ 25:9
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 24:1-27

የሐዋርያት ሥራ

24 ከአምስት ቀን በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ+ ከተወሰኑ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ እነሱም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዢው አቀረቡ።+ 2 በተጠራም ጊዜ ጠርጡለስ እንዲህ ሲል ይከሰው ጀመር፦

“ክቡር ፊሊክስ ሆይ፣ በአንተ አማካኝነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ አስተዋይነትህም ለዚህ ሕዝብ መሻሻል አስገኝቷል፤ 3 በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። 4 ይሁንና አሁን ጊዜህን እንዳልወስድብህ በአጭሩ የምንነግርህን ጉዳይ መልካም ፈቃድህ ሆኖ እንድትሰማን እለምንሃለሁ። 5 ይህ ሰው መቅሰፍት* ሆኖብናል፤+ በዓለም ባሉት አይሁዳውያን ሁሉ መካከል ዓመፅ ያነሳሳል፤+ ከዚህም ሌላ የናዝሬታውያን ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ ነው።+ 6 በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር ስላገኘነው ያዝነው።+ 7 *—— 8 አንተ ራስህ ስትመረምረው በእሱ ላይ ያቀረብነው ክስ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ ትችላለህ።”

9 አይሁዳውያኑም የተባለው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በመግለጽ በክሱ ተባበሩ። 10 አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦

“ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው።+ 11 ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከ12 ቀን እንደማይበልጥ አንተው ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤+ 12 እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ከማንም ጋር ስከራከርም ሆነ በምኩራቦች ወይም በከተማው ውስጥ ሕዝቡን ለዓመፅ ሳነሳሳ አላገኙኝም። 13 በተጨማሪም አሁን ላቀረቡብኝ ክስ ሁሉ ምንም ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም። 14 ይሁን እንጂ በሕጉና በነቢያት የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ+ ስለማምን እነሱ ኑፋቄ ብለው የሚጠሩትን የሕይወት መንገድ እንደምከተልና በዚህም መንገድ ለአባቶቼ አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንደማቀርብ አልክድም።+ 15 ደግሞም እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ተስፋ እንደሚያደርጉት ጻድቃንም ሆኑ ጻድቃን ያልሆኑ ሰዎች+ ከሞት እንደሚነሱ+ በአምላክ ተስፋ አለኝ። 16 በዚህ የተነሳ በአምላክም ሆነ በሰው ፊት ንጹሕ* ሕሊና ይዤ ለመኖር ሁልጊዜ ጥረት አደርጋለሁ።+ 17 ከብዙ ዓመታት በኋላም ለወገኖቼ ምጽዋት ለመስጠትና+ ለአምላክ መባ ለማቅረብ መጣሁ። 18 በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያገኙኝ የመንጻት ሥርዓት ፈጽሜ+ ይህንኑ ሳደርግ እንጂ ከብዙ ሕዝብ ጋር ሆኜ ሁከት ሳነሳሳ አልነበረም። ሆኖም ከእስያ አውራጃ የመጡ አንዳንድ አይሁዳውያን ነበሩ፤ 19 እነሱ እኔን የሚከሱበት ነገር ካላቸው እዚህ ፊትህ ተገኝተው ሊከሱኝ ይገባ ነበር።+ 20 ወይም እዚህ ያሉት ሰዎች በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት በቀረብኩበት ጊዜ ያገኙብኝ ጥፋት ካለ እነሱ ራሳቸው ይናገሩ፤ 21 በመካከላቸው ቆሜ በነበረበት ጊዜ ድምፄን ከፍ አድርጌ ‘ዛሬ በፊታችሁ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ በማመኔ ነው!’ ብዬ ከመናገር በቀር ያደረግኩት ነገር የለም።”+

22 ይሁን እንጂ ፊሊክስ ስለ ጌታ መንገድ+ በሚገባ ያውቅ ስለነበረ “የሠራዊቱ ሻለቃ ሉስዮስ ሲመጣ ለጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” በማለት ያቀረቡትን ክስ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈው። 23 ከዚያም ጳውሎስ በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ፣ ይሁንና መጠነኛ ነፃነት እንዲሰጠው መኮንኑን አዘዘው፤ ደግሞም ወዳጆቹ የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ ሲመጡ እንዲፈቅድላቸው መመሪያ ሰጠው።

24 ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ፊሊክስ አይሁዳዊት ከሆነችው ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ማመን ሲናገር አዳመጠው።+ 25 ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛትና ስለሚመጣው ፍርድ+ ሲናገር ግን ፊሊክስ ፈርቶ “ለአሁኑ ይበቃል፤ አጋጣሚ ሳገኝ ግን እንደገና አስጠራሃለሁ” አለው። 26 በዚሁ አጋጣሚ ጳውሎስ ጉቦ ይሰጠኛል ብሎ ተስፋ ያደርግ ስለነበር ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር። 27 ይሁንና ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፊሊክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ በዚህ ጊዜ ፊሊክስ በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ+ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ