የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ነገሥት የመጽሐፉ ይዘት

      • ሆሺአ በእስራኤል ላይ ነገሠ (1-4)

      • የእስራኤል ውድቀት (5, 6)

      • እስራኤላውያን ለግዞት ተዳረጉ (7-23)

      • በሰማርያ ከተሞች የባዕድ አገር ሰዎች እንዲሰፍሩ ተደረገ (24-26)

      • የሳምራውያን ቅይጥ አምልኮ (27-41)

2 ነገሥት 17:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:30

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 15

2 ነገሥት 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:9፤ ኢሳ 10:5, 6፤ ሆሴዕ 10:14, 15
  • +2ነገ 18:14

2 ነገሥት 17:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 31:1

2 ነገሥት 17:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 13:16
  • +ዘሌ 26:32, 33፤ ዘዳ 4:27፤ 28:64፤ 1ነገ 14:15
  • +1ዜና 5:26
  • +2ነገ 18:9-11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 12, 19-20

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 47-48

2 ነገሥት 17:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፈሩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:2
  • +ዘፀ 20:5

2 ነገሥት 17:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባቸውን ቦታዎችም ሆነ ሰው የሚበዛባቸውን ቦታዎች ሁሉ ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 12:11

2 ነገሥት 17:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 12:2፤ ኢሳ 57:5
  • +ዘፀ 34:13፤ ዘዳ 16:21, 22

2 ነገሥት 17:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:23

2 ነገሥት 17:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ፋንድያ” ከሚለው ቃል ጋር ዝምድና ሊኖረው የሚችል ሲሆን ንቀትን ለማመልከት ተሠርቶበታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:3-5፤ ዘሌ 26:1፤ ዘዳ 4:23
  • +1ነገ 12:28-30፤ 21:25, 26

2 ነገሥት 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 24:18, 19፤ 36:15, 16፤ ኤር 25:4
  • +ኢሳ 55:7

2 ነገሥት 17:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እንደ አባቶቻቸው አንገት እነሱም አንገታቸውን አደነደኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:32፤ 31:27

2 ነገሥት 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:2፤ 29:12
  • +ሆሴዕ 4:6
  • +ዘዳ 12:30
  • +ዘዳ 32:21፤ 1ሳሙ 12:21
  • +መዝ 115:4-8፤ ኢሳ 44:9

2 ነገሥት 17:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጠው የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን።”

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30
  • +1ነገ 14:15፤ 16:33
  • +ዘዳ 4:19፤ ኤር 8:2
  • +1ነገ 16:30, 31፤ 22:51, 53፤ 2ነገ 10:21፤ 23:4, 5

2 ነገሥት 17:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሸጡ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:1, 3
  • +ዘዳ 18:10፤ ሚክ 5:12

2 ነገሥት 17:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 23:12, 13፤ ኢሳ 42:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 12

2 ነገሥት 17:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 14:22፤ ኤር 3:8
  • +ሕዝ 23:4, 11

2 ነገሥት 17:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:20

2 ነገሥት 17:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:28-30

2 ነገሥት 17:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:45, 63፤ 1ነገ 14:16፤ ሆሴዕ 1:4፤ አሞጽ 5:27፤ ሚክ 1:6
  • +2ነገ 18:11

2 ነገሥት 17:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 19:11, 13

2 ነገሥት 17:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሖዋን አያመልኩም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:29

2 ነገሥት 17:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዚያን ምድር አምላክ ሃይማኖታዊ ልማዶች።”

2 ነገሥት 17:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማምለክ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 28:18, 19፤ ኢያሱ 16:1፤ 1ነገ 12:28, 29
  • +ዮሐ 4:20-22

2 ነገሥት 17:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አማልክት።”

2 ነገሥት 17:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:24

2 ነገሥት 17:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 18:34

2 ነገሥት 17:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 12:31, 32፤ 13:33

2 ነገሥት 17:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በነበሯቸው ሃይማኖታዊ ልማዶች መሠረት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:24, 41

2 ነገሥት 17:34

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በፊት የነበሯቸውን ሃይማኖታዊ ልማዶች በመከተል።”

  • *

    ቃል በቃል “የሚፈራ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 32:28

2 ነገሥት 17:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:5፤ 24:7፤ ዘዳ 29:1
  • +ዘፀ 20:3-5፤ 23:24፤ 34:14፤ ዘዳ 5:9

2 ነገሥት 17:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:12, 13
  • +ዘፀ 6:6

2 ነገሥት 17:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:9

2 ነገሥት 17:38

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:23

2 ነገሥት 17:40

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በፊት የነበሯቸውን ሃይማኖታዊ ልማዶች በመከተል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:34

2 ነገሥት 17:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 4:1, 2

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ነገ. 17:12ነገ 15:30
2 ነገ. 17:32ነገ 18:9፤ ኢሳ 10:5, 6፤ ሆሴዕ 10:14, 15
2 ነገ. 17:32ነገ 18:14
2 ነገ. 17:4ኢሳ 31:1
2 ነገ. 17:6ሆሴዕ 13:16
2 ነገ. 17:6ዘሌ 26:32, 33፤ ዘዳ 4:27፤ 28:64፤ 1ነገ 14:15
2 ነገ. 17:61ዜና 5:26
2 ነገ. 17:62ነገ 18:9-11
2 ነገ. 17:7ዘፀ 20:2
2 ነገ. 17:7ዘፀ 20:5
2 ነገ. 17:9ሆሴዕ 12:11
2 ነገ. 17:10ዘዳ 12:2፤ ኢሳ 57:5
2 ነገ. 17:10ዘፀ 34:13፤ ዘዳ 16:21, 22
2 ነገ. 17:11ዘሌ 20:23
2 ነገ. 17:12ዘፀ 20:3-5፤ ዘሌ 26:1፤ ዘዳ 4:23
2 ነገ. 17:121ነገ 12:28-30፤ 21:25, 26
2 ነገ. 17:132ዜና 24:18, 19፤ 36:15, 16፤ ኤር 25:4
2 ነገ. 17:13ኢሳ 55:7
2 ነገ. 17:14ዘዳ 1:32፤ 31:27
2 ነገ. 17:15ዘዳ 5:2፤ 29:12
2 ነገ. 17:15ሆሴዕ 4:6
2 ነገ. 17:15ዘዳ 12:30
2 ነገ. 17:15ዘዳ 32:21፤ 1ሳሙ 12:21
2 ነገ. 17:15መዝ 115:4-8፤ ኢሳ 44:9
2 ነገ. 17:161ነገ 12:28-30
2 ነገ. 17:161ነገ 14:15፤ 16:33
2 ነገ. 17:16ዘዳ 4:19፤ ኤር 8:2
2 ነገ. 17:161ነገ 16:30, 31፤ 22:51, 53፤ 2ነገ 10:21፤ 23:4, 5
2 ነገ. 17:172ነገ 16:1, 3
2 ነገ. 17:17ዘዳ 18:10፤ ሚክ 5:12
2 ነገ. 17:18ኢያሱ 23:12, 13፤ ኢሳ 42:24
2 ነገ. 17:191ነገ 14:22፤ ኤር 3:8
2 ነገ. 17:19ሕዝ 23:4, 11
2 ነገ. 17:211ነገ 12:20
2 ነገ. 17:221ነገ 12:28-30
2 ነገ. 17:23ዘዳ 28:45, 63፤ 1ነገ 14:16፤ ሆሴዕ 1:4፤ አሞጽ 5:27፤ ሚክ 1:6
2 ነገ. 17:232ነገ 18:11
2 ነገ. 17:242ነገ 19:11, 13
2 ነገ. 17:25ዘፀ 23:29
2 ነገ. 17:28ዘፍ 28:18, 19፤ ኢያሱ 16:1፤ 1ነገ 12:28, 29
2 ነገ. 17:28ዮሐ 4:20-22
2 ነገ. 17:302ነገ 17:24
2 ነገ. 17:312ነገ 18:34
2 ነገ. 17:321ነገ 12:31, 32፤ 13:33
2 ነገ. 17:332ነገ 17:24, 41
2 ነገ. 17:34ዘፍ 32:28
2 ነገ. 17:35ዘፀ 19:5፤ 24:7፤ ዘዳ 29:1
2 ነገ. 17:35ዘፀ 20:3-5፤ 23:24፤ 34:14፤ ዘዳ 5:9
2 ነገ. 17:36ዘዳ 6:12, 13
2 ነገ. 17:36ዘፀ 6:6
2 ነገ. 17:37ዘዳ 31:9
2 ነገ. 17:38ዘዳ 4:23
2 ነገ. 17:402ነገ 17:34
2 ነገ. 17:41ዕዝራ 4:1, 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ነገሥት 17:1-41

ሁለተኛ ነገሥት

17 የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በነገሠ በ12ኛው ዓመት የኤላህ ልጅ ሆሺአ+ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እሱም ለዘጠኝ ዓመት ገዛ። 2 ከእሱ በፊት የነበሩትን የእስራኤል ነገሥታት ያህል አይሁን እንጂ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። 3 የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር በእሱ ላይ መጣ፤+ ሆሺአም አገልጋዩ ሆነ፤ ገበረለትም።+ 4 ሆኖም የአሦር ንጉሥ ሰልምናሶር ሆሺአ እንዳሴረበት አወቀ፤ ምክንያቱም ሆሺአ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሶህ መልእክተኞች ልኮ ነበር፤+ ደግሞም ቀደም ባሉት ዓመታት ያደርግ እንደነበረው ለአሦር ንጉሥ መገበሩን አቁሞ ነበር። ስለሆነም የአሦር ንጉሥ እስር ቤት ውስጥ አስሮ አስቀመጠው።

5 የአሦር ንጉሥ መላ አገሪቱን ወረረ፤ ወደ ሰማርያም መጥቶ ከተማዋን ለሦስት ዓመት ከበባት። 6 ሆሺአ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ።+ ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ወደ አሦር በግዞት+ በመውሰድ በሃላህ፣ በጎዛን+ ወንዝ አጠገብ በምትገኘው በሃቦርና በሜዶናውያን ከተሞች አሰፈራቸው።+

7 ይህ የሆነው የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ቀንበርና ከግብፅ ምድር ነፃ ባወጣቸው በአምላካቸው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ ነው።+ እነሱም ሌሎች አማልክትን አመለኩ፤*+ 8 ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸውን ብሔራት ልማዶች ተከተሉ፤ ደግሞም የእስራኤል ነገሥታት ያቋቋሟቸውን ልማዶች ተከተሉ።

9 እስራኤላውያን በአምላካቸው በይሖዋ ፊት ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን ያደርጉ ነበር። ከመጠበቂያው ግንብ አንስቶ እስከተመሸገው ከተማ ድረስ በሁሉም ከተሞቻቸው* ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠሩ።+ 10 በእያንዳንዱ ኮረብታ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር+ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን*+ ለራሳቸው አቆሙ፤ 11 ይሖዋ ከፊታቸው አሳዶ በግዞት እንዲወሰዱ ያደረጋቸው ብሔራት ያደርጉ እንደነበረው ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ሁሉ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።+ ይሖዋን ለማስቆጣት ክፉ ነገሮችን ማድረጋቸውን ቀጠሉ።

12 ይሖዋ “አታድርጉ!”+ ያላቸውን ነገር በማድረግ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን* አገለገሉ፤+ 13 ይሖዋ በነቢያቱ ሁሉና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ+ አማካኝነት እስራኤልንና ይሁዳን “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ!+ አባቶቻችሁን ባዘዝኳቸውና በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ለእናንተ በሰጠሁት ሕግ መሠረት ትእዛዛቴንና ደንቦቼን ጠብቁ” በማለት በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 14 እነሱ ግን አልሰሙም፤ በአምላካቸው በይሖዋ እንዳላመኑት አባቶቻቸው እነሱም ግትሮች ሆኑ።*+ 15 ሥርዓቶቹን፣ ከአባቶቻቸው ጋር የገባውን ቃል ኪዳንና+ እነሱን ለማስጠንቀቅ የሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ችላ አሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ የእነሱን ምሳሌ እንዳይከተሉ ያዘዛቸውን+ በዙሪያቸው ያሉትን ብሔራት በመምሰል ከንቱ ጣዖቶችን ተከተሉ፤+ እነሱ ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ።+

16 የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ ተዉ፤ ለራሳቸውም ከብረት የተሠሩ ሁለት የጥጃ ሐውልቶችን* አበጁ፤+ የማምለኪያም ግንድ*+ ሠሩ፤ ለሰማያት ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤+ እንዲሁም ባአልን አገለገሉ።+ 17 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለእሳት አሳልፈው ሰጡ፤+ ሟርተኞችና ጠንቋዮች ሆኑ፤+ ይሖዋንም ያስቆጡት ዘንድ በእሱ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሰጡ።*

18 በመሆኑም ይሖዋ በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፤ ስለሆነም ከፊቱ አስወገዳቸው።+ ከይሁዳ ነገድ ሌላ ማንንም አላስቀረም።

19 የይሁዳም ሰዎች ቢሆኑ የአምላካቸውን የይሖዋን ትእዛዛት አልጠበቁም፤+ እነሱም እስራኤላውያን በተከተሏቸው ልማዶች ተመላለሱ።+ 20 ይሖዋም የእስራኤልን ዘሮች ሁሉ ተወ፤ ከፊቱም እስኪያስወግዳቸው ድረስ አዋረዳቸው፤ ለሚበዘብዟቸውም ሰዎች አሳልፎ ሰጣቸው። 21 እስራኤልን ከዳዊት ቤት ለየ፤ እነሱም የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡት።+ ሆኖም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን ይሖዋን ከመከተል ዞር እንዲሉና ከባድ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ። 22 የእስራኤልም ሰዎች ኢዮርብዓም የፈጸማቸውን ኃጢአቶች ሁሉ ሠሩ።+ ከዚያ ዞር አላሉም፤ 23 ይህም የሆነው ይሖዋ በአገልጋዮቹ በነቢያት ሁሉ አማካኝነት በተናገረው መሠረት እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ ነው።+ በመሆኑም እስራኤላውያን ከገዛ ምድራቸው ወደ አሦር በግዞት ተወሰዱ፤+ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ።

24 የአሦርም ንጉሥ ሰዎችን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋ፣ ከሃማትና ከሰፋርዊም+ አምጥቶ በእስራኤላውያን ምትክ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ መኖር ጀመሩ። 25 በዚያ መኖር እንደጀመሩ አካባቢ ይሖዋን አይፈሩም* ነበር። በመሆኑም ይሖዋ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤+ እነሱም የተወሰኑ ሰዎችን ገደሉ። 26 የአሦርም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “በግዞት ወስደህ በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ ያደረግካቸው ብሔራት የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ* አላወቁም። ስለዚህ በመካከላቸው አንበሶችን ላከባቸው፤ አንዳቸውም የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ ስለማያውቁ አንበሶቹ እየገደሏቸው ነው።”

27 በዚህ ጊዜ የአሦር ንጉሥ “ከዚያ በግዞት ከወሰዳችኋቸው ካህናት መካከል አንዱ ተመልሶ አብሯቸው በመኖር የዚያች ምድር አምላክ እንዴት እንደሚመለክ ያስተምራቸው” ሲል አዘዘ። 28 ስለሆነም ከሰማርያ በግዞት ከወሰዷቸው ካህናት መካከል አንዱ ተመልሶ በመምጣት በቤቴል+ መኖር ጀመረ፤ እሱም ይሖዋን እንዴት መፍራት* እንዳለባቸው ያስተምራቸው ጀመር።+

29 ይሁንና እያንዳንዱ ብሔር የየራሱን አምላክ* በመሥራት ሳምራውያን ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ በሠሯቸው ቤቶች ውስጥ አስቀምጦ ነበር፤ እያንዳንዱ ብሔር በሚኖርባቸው ከተሞች ውስጥ እንዲህ አደረገ። 30 በመሆኑም የባቢሎን ሰዎች ሱኮትቤኖትን፣ የኩት ሰዎች ኔርጋልን፣ የሃማት+ ሰዎች ደግሞ አሺማን ሠሩ፤ 31 አዋውያንም ኒብሃዝን እና ታርታቅን ሠሩ። ሰፋርዊማውያን+ ደግሞ አድራሜሌክና አናሜሌክ ለተባሉት የሰፋርዊም አማልክት ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ነበር። 32 ይሖዋን ይፈሩ የነበረ ቢሆንም ከሕዝቡ መካከል፣ ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች የሚያገለግሉ ካህናትን ሾሙ፤ እነዚህ ካህናትም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች በሚገኙት የአምልኮ ቤቶች የእነሱ አገልጋዮች ሆኑ።+ 33 በአንድ በኩል ይሖዋን ይፈሩ ነበር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመፈናቀላቸው በፊት የነበሩባቸው ብሔራት ያመልኩ እንደነበረው* የራሳቸውን አማልክት ያመልኩ ነበር።+

34 እስከ ዛሬ ድረስ አምልኳቸውን የሚያከናውኑት በፊት ያደርጉት እንደነበረው* ነው። ይሖዋን የሚያመልክ* ብሎም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹን እንዲሁም ይሖዋ እስራኤል የሚል ስም ላወጣለት ለያዕቆብ+ ልጆች የሰጣቸውን ሕግና ትእዛዝ የሚከተል አንድም ሰው አልነበረም። 35 ይሖዋ ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን በተጋባበት ወቅት+ እንዲህ ሲል አዟቸው ነበር፦ “ሌሎች አማልክትን አትፍሩ፤ አትስገዱላቸው፤ አታገልግሏቸው፤ አትሠዉላቸው።+ 36 ከዚህ ይልቅ መፍራት+ ያለባችሁ በታላቅ ኃይልና በተዘረጋ ክንድ ከግብፅ ምድር ያወጣችሁን ይሖዋን ነው፤+ መስገድ ያለባችሁ ለእሱ ነው፤ መሠዋት ያለባችሁም ለእሱ ነው። 37 የጻፈላችሁን ሥርዓቶች፣ ድንጋጌዎች፣ ሕግና ትእዛዛት ምንጊዜም በጥንቃቄ ጠብቁ፤+ ሌሎች አማልክትን አትፍሩ። 38 ደግሞም ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አትርሱ፤+ ሌሎች አማልክትንም አትፍሩ። 39 ይልቁንም ከጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ የሚታደጋችሁ እሱ ስለሆነ መፍራት ያለባችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ነው።”

40 እነሱ ግን አልታዘዙም፤ አምልኳቸውንም የሚያከናውኑት በፊት ያደርጉት እንደነበረው* ነው።+ 41 እነዚህ ብሔራት ይሖዋን ይፈሩ+ የነበረ ቢሆንም የራሳቸውን የተቀረጹ ምስሎችም ያገለግሉ ነበር። ልጆቻቸውም ሆኑ የልጅ ልጆቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ የሚያደርጉት አባቶቻቸው እንዳደረጉት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ