መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
א [አሌፍ]
2 እንደ ሣር በፍጥነት ይደርቃሉ፤+
እንደለመለመ ተክልም ይጠወልጋሉ።
ב [ቤት]
4 በይሖዋ ሐሴት አድርግ፤*
እሱም የልብህን መሻት ይሰጥሃል።
ג [ጊሜል]
6 ጽድቅህን እንደ ንጋት ብርሃን፣
የአንተንም ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል።
ד [ዳሌት]
የጠነሰሰውን ሴራ
በተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ።+
ה [ሄ]
ו [ዋው]
ז [ዛየን]
12 ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ያሴራል፤+
በእሱ ላይ ጥርሱን ያፋጫል።
13 ይሖዋ ግን ይስቅበታል፤
የሚጠፋበት ቀን እንደሚደርስ ያውቃልና።+
ח [ኼት]
14 ክፉዎች የተጨቆነውንና ድሃውን ለመጣል፣
እንዲሁም ቀና የሆነውን መንገድ የሚከተሉትን ለማረድ
ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ደጋናቸውንም ይወጥራሉ።
15 ሆኖም ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤+
ደጋኖቻቸው ይሰበራሉ።
ט [ቴት]
16 ብዙ ክፉ ሰዎች ካላቸው የተትረፈረፈ ሀብት ይልቅ
ጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ነገር ይሻላል።+
17 የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤
ይሖዋ ግን ጻድቃንን ይደግፋል።
י [ዮድ]
19 በአደጋ ወቅት ለኀፍረት አይዳረጉም፤
በረሃብ ዘመን የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራቸዋል።
כ [ካፍ]
ל [ላሜድ]
22 አምላክ የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤
እሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ።+
מ [ሜም]
נ [ኑን]
26 ሁልጊዜ ሳይሰስት ያበድራል፤+
ልጆቹም በረከት ያገኛሉ።
ס [ሳሜኽ]
27 ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤+
ለዘላለምም ትኖራለህ።
28 ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤
ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም።+
ע [አይን]
פ [ፔ]
צ [ጻዴ]
32 ክፉ ሰው ጻድቁን ለመግደል
በዓይነ ቁራኛ ይከታተለዋል።
ק [ኮፍ]
34 ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል፤
እሱም ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ምድርንም ትወርሳለህ።
ר [ረሽ]
35 ጨካኝ የሆነውን ክፉ ሰው፣
በበቀለበት መሬት ላይ እንደለመለመ ዛፍ ተንሰራፍቶ አየሁት።+
ש [ሺን]
38 ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ፤
ክፉዎች ምንም ተስፋ አይኖራቸውም።+
ת [ታው]
40 ይሖዋ ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም።+
እሱን መጠጊያ ስላደረጉ፣
ከክፉዎች ይታደጋቸዋል፤ ደግሞም ያድናቸዋል።+