የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕዝቅኤል 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሕዝቅኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ሕዝቅኤል በባቢሎን ሆኖ የአምላክን ራእዮች ተመለከተ (1-3)

      • የይሖዋ ሰማያዊ ሠረገላ ራእይ (4-28)

        • አውሎ ነፋስ፣ ደመናና እሳት (4)

        • አራት ሕያዋን ፍጥረታት (5-14)

        • አራት መንኮራኩሮች (15-21)

        • እንደ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር (22-24)

        • የይሖዋ ዙፋን (25-28)

ሕዝቅኤል 1:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 3:15
  • +2ነገ 24:12, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 23, 31

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1998፣ ገጽ 15

ሕዝቅኤል 1:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:9, 10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 31

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1998፣ ገጽ 15

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 6

ሕዝቅኤል 1:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “አምላክ ያበረታል” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    ቃል በቃል “እጅ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 22:25
  • +ሕዝ 3:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 30, 48-49

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 6

ሕዝቅኤል 1:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መብረቅ።”

  • *

    የሚያብረቀርቅ የወርቅና የብር ቅይጥ።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 19:11
  • +ዘፀ 19:18፤ መዝ 97:2, 3
  • +ሕዝ 8:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 30

ሕዝቅኤል 1:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 10:9, 15፤ ራእይ 4:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 43

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/1/2007፣ ገጽ 12

    3/1/1991፣ ገጽ 31

ሕዝቅኤል 1:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:2፤ ሕዝ 10:20, 21፤ ራእይ 4:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 43, 238

ሕዝቅኤል 1:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 10:5, 6

ሕዝቅኤል 1:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 10:11, 15

ሕዝቅኤል 1:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 17:10፤ ምሳሌ 28:1
  • +ምሳሌ 14:4
  • +ኢዮብ 39:27, 29
  • +ሕዝ 10:14, 15፤ ራእይ 4:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 43, 238

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 9

ሕዝቅኤል 1:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:2

ሕዝቅኤል 1:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 103:20፤ ዕብ 1:7, 14

ሕዝቅኤል 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 7:9, 10

ሕዝቅኤል 1:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የሠረገላ ተሽከርካሪ እግር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 10:9-13፤ ራእይ 4:7

ሕዝቅኤል 1:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 36-37

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 9

ሕዝቅኤል 1:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 37

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 9-10

ሕዝቅኤል 1:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 15:3፤ ዘካ 4:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 37

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 9

ሕዝቅኤል 1:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 10:15-17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 40

ሕዝቅኤል 1:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የሕያው ፍጡሩ መንፈስ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 38-39

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 10

ሕዝቅኤል 1:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 38-39

ሕዝቅኤል 1:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 10:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 38

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/1991፣ ገጽ 10

ሕዝቅኤል 1:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ቀጥ ብለው ተዘርግተው ነበር” ማለትም ሊሆን ይችላል።

ሕዝቅኤል 1:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 29:3፤ ሕዝ 43:2፤ ራእይ 14:2

ሕዝቅኤል 1:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 24:10፤ መዝ 96:6፤ ሕዝ 10:1
  • +1ነገ 22:19፤ መዝ 99:1፤ ኢሳ 6:1፤ ራእይ 4:2
  • +ዳን 7:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 32-33, 39

ሕዝቅኤል 1:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 8:2
  • +ዘዳ 4:24፤ መዝ 104:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 39-40

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 6 2016፣ ገጽ 4

ሕዝቅኤል 1:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 4:3
  • +ዘፀ 24:16, 17፤ ሕዝ 8:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2022፣ ገጽ 4

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 39-40

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 6 2016፣ ገጽ 4

ተዛማጅ ሐሳብ

ሕዝ. 1:1ሕዝ 3:15
ሕዝ. 1:12ነገ 24:12, 14
ሕዝ. 1:22ዜና 36:9, 10
ሕዝ. 1:3ኤር 22:25
ሕዝ. 1:3ሕዝ 3:14
ሕዝ. 1:41ነገ 19:11
ሕዝ. 1:4ዘፀ 19:18፤ መዝ 97:2, 3
ሕዝ. 1:4ሕዝ 8:2
ሕዝ. 1:5ሕዝ 10:9, 15፤ ራእይ 4:6
ሕዝ. 1:6ኢሳ 6:2፤ ሕዝ 10:20, 21፤ ራእይ 4:8
ሕዝ. 1:7ዳን 10:5, 6
ሕዝ. 1:9ሕዝ 10:11, 15
ሕዝ. 1:102ሳሙ 17:10፤ ምሳሌ 28:1
ሕዝ. 1:10ምሳሌ 14:4
ሕዝ. 1:10ኢዮብ 39:27, 29
ሕዝ. 1:10ሕዝ 10:14, 15፤ ራእይ 4:7
ሕዝ. 1:11ኢሳ 6:2
ሕዝ. 1:12መዝ 103:20፤ ዕብ 1:7, 14
ሕዝ. 1:13ዳን 7:9, 10
ሕዝ. 1:15ሕዝ 10:9-13፤ ራእይ 4:7
ሕዝ. 1:18ምሳሌ 15:3፤ ዘካ 4:10
ሕዝ. 1:19ሕዝ 10:15-17
ሕዝ. 1:22ሕዝ 10:1
ሕዝ. 1:24መዝ 29:3፤ ሕዝ 43:2፤ ራእይ 14:2
ሕዝ. 1:26ዘፀ 24:10፤ መዝ 96:6፤ ሕዝ 10:1
ሕዝ. 1:261ነገ 22:19፤ መዝ 99:1፤ ኢሳ 6:1፤ ራእይ 4:2
ሕዝ. 1:26ዳን 7:9
ሕዝ. 1:27ሕዝ 8:2
ሕዝ. 1:27ዘዳ 4:24፤ መዝ 104:1, 2
ሕዝ. 1:28ራእይ 4:3
ሕዝ. 1:28ዘፀ 24:16, 17፤ ሕዝ 8:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሕዝቅኤል 1:1-28

ሕዝቅኤል

1 በ30ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፣ በኬባር ወንዝ+ አጠገብ በግዞት በተወሰደው ሕዝብ+ መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ። 2 ከወሩ በአምስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዮአኪን+ በግዞት በተወሰደ በአምስተኛው ዓመት፣ 3 በከለዳውያን+ ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የይሖዋ ቃል የካህኑ የቡዚ ልጅ ወደሆነው ወደ ሕዝቅኤል* መጣ። በዚያም የይሖዋ ኃይል* በእሱ ላይ ወረደ።+

4 እኔም በማየት ላይ ሳለሁ ከሰሜን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ+ ሲመጣ ተመለከትኩ፤ በዚያም ታላቅ ደመናና በደማቅ ብርሃን የተከበበ የእሳት+ ብልጭታ* ነበር፤ ከእሳቱም መካከል የሚያብረቀርቅ ብረት*+ የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር። 5 በመካከሉም የአራት ሕያዋን ፍጥረታት+ አምሳያ ነበር፤ የእያንዳንዳቸውም መልክ እንደ ሰው መልክ ነበር። 6 እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው።+ 7 እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፤ እግሮቻቸውም እንደተወለወለ መዳብ ያብረቀርቃሉ።+ 8 በአራቱም ጎኖቻቸው ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው። 9 ክንፎቻቸውም እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም፤ እያንዳንዳቸውም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+

10 የፊታቸው መልክ ይህን ይመስል ነበር፦ አራቱም የሰው ፊት ነበራቸው፤ በስተ ቀኝ የአንበሳ+ ፊት፣ በስተ ግራ የበሬ+ ፊት ነበራቸው፤ ደግሞም አራቱም የንስር+ ፊት ነበራቸው።+ 11 ፊታቸው ይህን ይመስላል። ክንፎቻቸው ከእነሱ በላይ ተዘርግተዋል። እያንዳንዳቸው እርስ በርሳቸው የሚነካኩ ሁለት ክንፎች ነበሯቸው፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር።+

12 እያንዳንዳቸው መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ ሁሉ ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+ በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም። 13 የሕያዋን ፍጥረታቱ መልክ የሚነድ የከሰል ፍም ይመስላል፤ በሕያዋን ፍጥረታቱም መካከል እየነደደ ያለ ችቦ የሚመስል ነገር ወዲያና ወዲህ ይል ነበር፤ ከእሳቱም+ መካከል መብረቅ ይወጣ ነበር። 14 ሕያዋን ፍጥረታቱም ወዲያና ወዲህ ሲሄዱ እንቅስቃሴያቸው የመብረቅ ብልጭታ ይመስል ነበር።

15 እኔም ሕያዋን ፍጥረታቱን ስመለከት አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኮራኩር* አየሁ።+ 16 መንኮራኩሮቹ በአጠቃላይ ሲታዩ እንደ ክርስቲሎቤ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው፤ አራቱም ይመሳሰላሉ። መልካቸውና አሠራራቸው ሲታይ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስላል። 17 በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም ጎን በፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይችላሉ። 18 የመንኮራኩሮቹም ጠርዝ እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚያስፈራ ነበር፤ የአራቱም መንኮራኩሮች ጠርዝ ዙሪያውን በዓይኖች የተሞላ ነበር።+ 19 ሕያዋን ፍጥረታቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር፣ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ከፍ ይላሉ።+ 20 መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ፣ መንፈሱ ወደሚሄድበት ቦታ ሁሉ ይሄዳሉ። መንኮራኩሮቹ ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ* በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። 21 ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲንቀሳቀሱ እነሱም ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲቆሙ እነሱም ይቆማሉ፤ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና።

22 ከሕያዋን ፍጥረታቱ ራስ በላይ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር የሚመስል ነገር ነበር፤ ይህም ከራሳቸው በላይ ተዘርግቶ ነበር።+ 23 ከጠፈሩ በታች ክንፎቻቸው አንዳቸው ወደ ሌላው ቀጥ ብለው ነበር።* እያንዳንዳቸውም በዚህ ጎንና በዚያኛው ጎን ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሯቸው። 24 የክንፎቻቸውን ድምፅ ስሰማ እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ፣ ደግሞም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ድምፅ ነበር።+ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ድምፁ እንደ ሠራዊት ድምፅ ነበር። በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጋሉ።

25 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ አንድ ድምፅ ይሰማ ነበር። (በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጉ ነበር።) 26 ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ+ የመሰለ እንደ ዙፋን ያለ ነገር ነበር።+ ከላይ በኩል ባለው በዙፋኑ ላይ መልኩ የሰው መልክ የሚመስል ተቀምጦ ነበር።+ 27 ወገቡ ከሚመስለው ነገር ጀምሮ ወደ ላይ፣ እሳት የሚመስል እንደ ብረት የሚያብረቀርቅ ነገር+ ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከወገቡ ጀምሮ ወደ ታች፣ እሳት የሚመስል ነገር አየሁ።+ በዙሪያውም ደማቅ ብርሃን ነበር፤ 28 ይህም ዝናባማ በሆነ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ነበር።+ በዙሪያው ያለው ደማቅ ብርሃን ይህን ይመስላል። ደግሞም የይሖዋን ክብር ይመስል ነበር።+ እኔም ባየሁት ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከዚያም አንዱ ሲናገር ድምፅ ሰማሁ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ