የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ናታን ዳዊትን ገሠጸው (1-15ሀ)

      • የቤርሳቤህ ልጅ ሞተ (15ለ-23)

      • ቤርሳቤህ ሰለሞንን ወለደች (24, 25)

      • የአሞናውያን ከተማ የሆነችው ራባ ተያዘች (26-31)

2 ሳሙኤል 12:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 1:8፤ 1ዜና 17:1፤ 29:29
  • +መዝ 51:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2010፣ ገጽ 30

2 ሳሙኤል 12:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:13፤ 15:16

2 ሳሙኤል 12:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:3

2 ሳሙኤል 12:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:4

2 ሳሙኤል 12:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2010፣ ገጽ 30

2 ሳሙኤል 12:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:1

2 ሳሙኤል 12:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 7:8
  • +1ሳሙ 18:10, 11፤ 19:10፤ 23:14

2 ሳሙኤል 12:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 13:13, 14፤ 15:26, 28
  • +2ሳሙ 3:7፤ 1ነገ 2:22
  • +2ሳሙ 2:4፤ 5:5
  • +2ሳሙ 7:19

2 ሳሙኤል 12:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:13
  • +2ሳሙ 11:15, 27
  • +ዘፀ 20:14, 17

2 ሳሙኤል 12:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 14:18፤ 2ሳሙ 13:32፤ 18:33፤ ገላ 6:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2010፣ ገጽ 30

2 ሳሙኤል 12:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለባልንጀራህ።”

  • *

    ቃል በቃል “በዚህች ፀሐይ ዓይኖች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:15, 19፤ 13:10-15፤ 15:14
  • +ዘፀ 21:24፤ ኢዮብ 31:9-11፤ 34:11
  • +2ሳሙ 16:21, 22

2 ሳሙኤል 12:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በፀሐይ ፊት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:4, 15

2 ሳሙኤል 12:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኃጢአትህ አልፎ እንዲሄድ ያደርጋል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 39:9፤ መዝ 32:5፤ 38:3፤ 51:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ፤ 51:4፤ ምሳሌ 28:13
  • +ዘፀ 34:6፤ መዝ 32:1
  • +ዘሌ 20:10፤ መዝ 103:10

2 ሳሙኤል 12:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 12:22፤ ዮናስ 3:8, 9

2 ሳሙኤል 12:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥቱም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሩት 3:3፤ 2ሳሙ 14:2
  • +2ሳሙ 6:17

2 ሳሙኤል 12:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 38:3, 5፤ ኢዩ 2:13, 14፤ አሞጽ 5:15፤ ዮናስ 3:8, 9
  • +2ሳሙ 12:16፤ ኢዩ 1:14

2 ሳሙኤል 12:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 9:6
  • +ኢዮብ 30:23፤ መክ 3:20፤ ሥራ 2:29, 34፤ 13:36
  • +መክ 9:5, 10

2 ሳሙኤል 12:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ሰላም” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:3
  • +1ዜና 3:5, 9፤ 22:9፤ 28:5፤ ማቴ 1:6
  • +2ሳሙ 7:12፤ 1ዜና 29:1

2 ሳሙኤል 12:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በያህ የተወደደ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:4, 5፤ 12:1፤ 1ነገ 1:8

2 ሳሙኤል 12:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመንግሥቱንም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 23:3, 6
  • +ዘዳ 3:11፤ ኢያሱ 13:24, 25
  • +2ሳሙ 11:25፤ 1ዜና 20:1

2 ሳሙኤል 12:27

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተማዋ ውኃ የምታገኝባቸውን የውኃ ምንጮች የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 11:1

2 ሳሙኤል 12:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ስሜ ይጠራባታል።”

2 ሳሙኤል 12:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ የአሞናውያን ጣዖት ሳይሆን አይቀርም፤ በሌላ ቦታ ላይ ሞሎክ ወይም ሚልኮም ተብሎም ተጠርቷል።

  • *

    አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 20:2, 3
  • +2ሳሙ 8:11, 12

2 ሳሙኤል 12:31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2005፣ ገጽ 27

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 12:11ነገ 1:8፤ 1ዜና 17:1፤ 29:29
2 ሳሙ. 12:1መዝ 51:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ
2 ሳሙ. 12:22ሳሙ 5:13፤ 15:16
2 ሳሙ. 12:32ሳሙ 11:3
2 ሳሙ. 12:42ሳሙ 11:4
2 ሳሙ. 12:5ዘዳ 6:13
2 ሳሙ. 12:6ዘፀ 22:1
2 ሳሙ. 12:71ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 7:8
2 ሳሙ. 12:71ሳሙ 18:10, 11፤ 19:10፤ 23:14
2 ሳሙ. 12:81ሳሙ 13:13, 14፤ 15:26, 28
2 ሳሙ. 12:82ሳሙ 3:7፤ 1ነገ 2:22
2 ሳሙ. 12:82ሳሙ 2:4፤ 5:5
2 ሳሙ. 12:82ሳሙ 7:19
2 ሳሙ. 12:9ዘፀ 20:13
2 ሳሙ. 12:92ሳሙ 11:15, 27
2 ሳሙ. 12:9ዘፀ 20:14, 17
2 ሳሙ. 12:10ዘኁ 14:18፤ 2ሳሙ 13:32፤ 18:33፤ ገላ 6:7
2 ሳሙ. 12:112ሳሙ 12:15, 19፤ 13:10-15፤ 15:14
2 ሳሙ. 12:11ዘፀ 21:24፤ ኢዮብ 31:9-11፤ 34:11
2 ሳሙ. 12:112ሳሙ 16:21, 22
2 ሳሙ. 12:122ሳሙ 11:4, 15
2 ሳሙ. 12:13ዘፍ 39:9፤ መዝ 32:5፤ 38:3፤ 51:በመዝሙሩ አናት ላይ የሚገኘው መግለጫ፤ 51:4፤ ምሳሌ 28:13
2 ሳሙ. 12:13ዘፀ 34:6፤ መዝ 32:1
2 ሳሙ. 12:13ዘሌ 20:10፤ መዝ 103:10
2 ሳሙ. 12:162ሳሙ 12:22፤ ዮናስ 3:8, 9
2 ሳሙ. 12:20ሩት 3:3፤ 2ሳሙ 14:2
2 ሳሙ. 12:202ሳሙ 6:17
2 ሳሙ. 12:22ኢሳ 38:3, 5፤ ኢዩ 2:13, 14፤ አሞጽ 5:15፤ ዮናስ 3:8, 9
2 ሳሙ. 12:222ሳሙ 12:16፤ ኢዩ 1:14
2 ሳሙ. 12:23መክ 9:6
2 ሳሙ. 12:23ኢዮብ 30:23፤ መክ 3:20፤ ሥራ 2:29, 34፤ 13:36
2 ሳሙ. 12:23መክ 9:5, 10
2 ሳሙ. 12:242ሳሙ 11:3
2 ሳሙ. 12:241ዜና 3:5, 9፤ 22:9፤ 28:5፤ ማቴ 1:6
2 ሳሙ. 12:242ሳሙ 7:12፤ 1ዜና 29:1
2 ሳሙ. 12:252ሳሙ 7:4, 5፤ 12:1፤ 1ነገ 1:8
2 ሳሙ. 12:26ዘዳ 23:3, 6
2 ሳሙ. 12:26ዘዳ 3:11፤ ኢያሱ 13:24, 25
2 ሳሙ. 12:262ሳሙ 11:25፤ 1ዜና 20:1
2 ሳሙ. 12:272ሳሙ 11:1
2 ሳሙ. 12:301ዜና 20:2, 3
2 ሳሙ. 12:302ሳሙ 8:11, 12
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 12:1-31

ሁለተኛ ሳሙኤል

12 በመሆኑም ይሖዋ ናታንን+ ወደ ዳዊት ላከው። እሱም ወደ ዳዊት መጥቶ+ እንዲህ አለው፦ “በአንዲት ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንደኛው ሀብታም ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድሃ ነበር። 2 ሀብታሙ ሰው እጅግ ብዙ በጎችና ከብቶች ነበሩት፤+ 3 ድሃው ሰው ግን ከገዛት አንዲት ትንሽ የበግ ጠቦት ሌላ ምንም አልነበረውም።+ እሱም ይንከባከባት ነበር፤ እሷም ከእሱና ከወንዶች ልጆቹ ጋር አብራ እየኖረች አደገች። ያለችውን ጥቂት ምግብ አብራ ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በእቅፉ ትተኛ ነበር። ለእሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች። 4 አንድ ቀን ሀብታሙ ሰው እንግዳ መጣበት፤ ሆኖም ይህ ሰው ወደ እሱ ለመጣው መንገደኛ የሚበላ ነገር ለማዘጋጀት ከራሱ በጎችና ከብቶች ላይ አልወሰደም። ከዚህ ይልቅ የድሃውን ሰው የበግ ጠቦት ወስዶ ወደ እሱ ለመጣው እንግዳ አዘጋጅቶ አቀረበለት።”+

5 በዚህ ጊዜ ዳዊት በሰውየው ላይ እጅግ ተቆጥቶ ናታንን እንዲህ አለው፦ “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣+ ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል! 6 ይህ ሰው እንዲህ ያለውን ነገር ስላደረገና ርኅራኄ ስላላሳየ በበግ ጠቦቷ ምትክ አራት እጥፍ መክፈል አለበት።”+

7 ከዚያም ናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ያ ሰው አንተ ነህ! የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እኔ ራሴ ቀባሁህ፤+ ከሳኦልም እጅ ታደግኩህ።+ 8 የጌታህን ቤት ልሰጥህ፣+ የጌታህንም ሚስቶች+ በእቅፍህ ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ፤ የእስራኤልንና የይሁዳንም ቤት ሰጠሁህ።+ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ ነገር ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ።+ 9 ታዲያ በፊቱ መጥፎ ነገር በመሥራት የይሖዋን ቃል ያቃለልከው ለምንድን ነው? ሂታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታኸው!+ በአሞናውያን ሰይፍ ከገደልከውም+ በኋላ ሚስቱን ወስደህ ሚስትህ አደረግካት።+ 10 ስለዚህ የሂታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደህ ሚስትህ በማድረግ እኔን ስለናቅክ ሰይፍ ከቤትህ ፈጽሞ አይለይም።’+ 11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከገዛ ቤትህ መከራ አመጣብሃለሁ፤+ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው* እሰጣቸዋለሁ፤+ እሱም በቀን ብርሃን* ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።+ 12 አንተ ይህን በድብቅ ብታደርገውም+ እኔ ግን በመላው እስራኤል ፊት በቀን ብርሃን* አደርገዋለሁ።’”

13 ከዚያም ዳዊት ናታንን “በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ” አለው።+ ናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋም ኃጢአትህን ይቅር ይላል።*+ አትሞትም።+ 14 ይሁንና ይህን ድርጊት በመፈጸም ይሖዋን እጅግ ስለናቅክ አሁን የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።”

15 ከዚያም ናታን ወደ ቤቱ ሄደ።

ይሖዋም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ በመቅሰፍት መታው፤ ልጁም ታመመ። 16 ዳዊትም ስለ ልጁ እውነተኛውን አምላክ ተማጸነ። ምንም ነገር ሳይቀምስም ጾመ፤ ወደ ክፍሉ ገብቶም ሌሊቱን ሙሉ መሬት ላይ ተኝቶ አደረ።+ 17 በቤቱ ያሉ ሽማግሌዎችም መጥተው አጠገቡ ቆሙ፤ ከመሬት ሊያነሱትም ሞከሩ። እሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ አብሯቸውም ምግብ አልበላም። 18 በሰባተኛው ቀን ልጁ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮች ግን የልጁን መሞት ለእሱ መንገር ፈሩ። እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ልጁ በሕይወት ሳለ ዳዊትን አነጋግረነው ነበር፤ እሱ ግን ሊሰማን ፈቃደኛ አልሆነም። ታዲያ አሁን ልጁ መሞቱን እንዴት እንነግረዋለን? መቼም ይህን ብንነግረው መጥፎ ነገር ሊያደርግ ይችላል።”

19 ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ሲያይ ልጁ እንደሞተ ገባው። በመሆኑም አገልጋዮቹን “ልጁ ሞተ?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ሞቷል” ብለው መለሱለት። 20 በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሳ። ከታጠበ፣ ዘይት ከተቀባና+ ልብሱን ከቀየረ በኋላም ወደ ይሖዋ ቤት+ ሄዶ ሰገደ። ወደ ቤቱም* ሄዶ ምግብ እንዲያቀርቡለት ጠየቀ፤ ከዚያም በላ። 21 አገልጋዮቹም “እንዲህ ያደረግከው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት ሳለ ስትጾምና ስታለቅስ ነበር፤ ልጁ ሲሞት ግን ወዲያውኑ ተነሳህ፤ ምግብም በላህ” አሉት። 22 እሱም እንዲህ አለ፦ “ልጁ በሕይወት ሳለ ‘ማን ያውቃል፣ ይሖዋ ይራራልኝና ልጁን በሕይወት ያኖርልኝ ይሆናል’+ ብዬ ስላሰብኩ ጾምኩ፤+ እንዲሁም አለቀስኩ። 23 አሁን ግን ልጁ ሞቷል፤ ታዲያ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁ?+ እኔ ወደ እሱ እሄዳለሁ+ እንጂ እሱ ወደ እኔ አይመለስም።”+

24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን+ አጽናናት። ወደ እሷም ገብቶ አብሯት ተኛ። ከጊዜ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙም ሰለሞን*+ ተባለ። ይሖዋም ወደደው፤+ 25 በነቢዩ ናታን+ በኩል መልእክት ልኮም ለይሖዋ ሲል ስሙን ይዲድያህ* አለው።

26 ኢዮአብ የአሞናውያን+ ከተማ የሆነችውን ራባን+ መውጋቱን ቀጠለ፤ የነገሥታቱንም* ከተማ ተቆጣጠረ።+ 27 በመሆኑም ኢዮአብ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፦ “ከራባ+ ጋር ተዋግቼ የውኃዎችን ከተማ* ይዣለሁ። 28 በል አሁን የቀረውን ሠራዊት ሰብስብና ከተማዋን ከበህ በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት። አለዚያ ከተማዋን እይዛትና ክብሩ ለእኔ ይሆናል።”*

29 በመሆኑም ዳዊት ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ራባ ሄደ፤ ከተማዋንም ወግቶ በቁጥጥር ሥር አደረጋት። 30 ከዚያም የማልካምን* ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት* ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ+ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ 31 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በብረት መጥረቢያዎች እንዲሠሩ እንዲሁም ጡብ እንዲያመርቱ አደረጋቸው። በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ