መዝሙር
የዳዊት መዝሙር።
27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው።
ማንን እፈራለሁ?+
ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+
ማን ያሸብረኛል?
2 ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+
ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው።
3 ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣
ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+
ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳ
በልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ።
6 በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤
በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤
ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።
8 ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር
“ፊቴን ፈልጉ” ብሏል።
ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+
9 ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+
አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው።
አንተ ረዳቴ ነህ፤+
አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።
11 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+
ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ።
አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ።