የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዮሐንስ 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዮሐንስ የመጽሐፉ ይዘት

      • አልዓዛር ሞተ (1-16)

      • ኢየሱስ ማርታንና ማርያምን አጽናናቸው (17-37)

      • ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳው (38-44)

      • ኢየሱስን ለመግደል የተጠነሰሰ ሴራ (45-57)

ዮሐንስ 11:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 10:38

ዮሐንስ 11:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:6, 7፤ ማር 14:3፤ ዮሐ 12:3

ዮሐንስ 11:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2023፣ ገጽ 10

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 210

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 176

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2011፣ ገጽ 14

ዮሐንስ 11:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 9:1-3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2013፣ ገጽ 32

    9/15/2000፣ ገጽ 14-15

ዮሐንስ 11:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2015፣ ገጽ 18-19

ዮሐንስ 11:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2013፣ ገጽ 32

    8/1/2010፣ ገጽ 14-15

    1/1/2008፣ ገጽ 31

    9/15/2000፣ ገጽ 14-15

ዮሐንስ 11:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 1:38
  • +ዮሐ 8:59፤ 10:31

ዮሐንስ 11:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 9:4፤ 12:35

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 210-211

ዮሐንስ 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 13:3፤ ማቴ 9:24፤ ሥራ 7:59, 60፤ 1ቆሮ 15:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 29

    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?፣ ገጽ 63-64

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ገጽ 59

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2002፣ ገጽ 6

ዮሐንስ 11:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 29

ዮሐንስ 11:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 29

ዮሐንስ 11:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መክ 9:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 29

ዮሐንስ 11:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መንትያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 211

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2010፣ ገጽ 14

ዮሐንስ 11:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2008፣ ገጽ 31

ዮሐንስ 11:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “15 ስታዲዮን ገደማ።” ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1629

ዮሐንስ 11:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 10:38, 39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 176

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2011፣ ገጽ 14

ዮሐንስ 11:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2023፣ ገጽ 10-11

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 177

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2011፣ ገጽ 14

ዮሐንስ 11:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

ዮሐንስ 11:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

ዮሐንስ 11:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 26:19፤ ዮሐ 5:28, 29፤ ሥራ 24:15፤ ዕብ 11:35፤ ራእይ 20:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2017፣ ገጽ 3-7

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2014፣ ገጽ 7

    4/1/2011፣ ገጽ 14

    7/1/1998፣ ገጽ 21-22

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 177

    አስተማሪ፣ ገጽ 188

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 166-168

ዮሐንስ 11:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በእኔ እንደሚያምን በተግባር የሚያሳይ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 14:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2023፣ ገጽ 10-11

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/2014፣ ገጽ 6

    1/1/2014፣ ገጽ 15

    4/15/2005፣ ገጽ 5

ዮሐንስ 11:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 8:51

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 212

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2005፣ ገጽ 5

    2/15/1995፣ ገጽ 16-17

    ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ ገጽ 30

    ማመራመር፣ ገጽ 247

ዮሐንስ 11:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 172, 178

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2011፣ ገጽ 11, 14

ዮሐንስ 11:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 23:8፤ ዮሐ 13:13

ዮሐንስ 11:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 11:17

ዮሐንስ 11:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በመንፈሱ ቃተተ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2008፣ ገጽ 5

    5/1/2006፣ ገጽ 28

    የምትወዱት ሰው፣ ገጽ 29-30

ዮሐንስ 11:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 19:41፤ ዕብ 4:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2023፣ ገጽ 11

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2022፣ ገጽ 15-16

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2019፣ ገጽ 19

    3/2019፣ ገጽ 17

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    7/2017፣ ገጽ 13-14

    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?፣ ገጽ 72

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2013፣ ገጽ 32

    4/15/2012፣ ገጽ 5

    11/1/2010፣ ገጽ 10

    1/15/2009፣ ገጽ 6

    12/1/2008፣ ገጽ 5

    5/1/2008፣ ገጽ 24

    5/1/2006፣ ገጽ 28

    6/15/1999፣ ገጽ 23-24

    6/1/1995፣ ገጽ 8

    የምትወዱት ሰው፣ ገጽ 29-30

    ንቁ!፣

    9/8/2001፣ ገጽ 23

ዮሐንስ 11:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 9:6, 7

ዮሐንስ 11:38

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 30

ዮሐንስ 11:39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 30

ዮሐንስ 11:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 9:1-3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2006፣ ገጽ 6

ዮሐንስ 11:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 14:19፤ ማር 7:34, 35

ዮሐንስ 11:42

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:28-30፤ 17:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 214-215

ዮሐንስ 11:43

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 7:12, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 30

    ንቁ!፣

    10/2007፣ ገጽ 29

ዮሐንስ 11:44

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 30

    ንቁ!፣

    10/2007፣ ገጽ 29

    ማመራመር፣ ገጽ 336

ዮሐንስ 11:45

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 2:23፤ 10:42፤ 12:10, 11

ዮሐንስ 11:47

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 12:37፤ ሥራ 4:15, 16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 11-12

ዮሐንስ 11:48

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቤተ መቅደሱን ያመለክታል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 11-12

ዮሐንስ 11:49

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:3፤ ሉቃስ 3:2፤ ሥራ 4:5, 6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

ዮሐንስ 11:50

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 12

ዮሐንስ 11:51

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 12

ዮሐንስ 11:52

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2006፣ ገጽ 12

ዮሐንስ 11:54

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 13:23፤ 2ዜና 13:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 215-216

ዮሐንስ 11:55

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 12:14፤ ዘዳ 16:1፤ ዮሐ 2:13፤ 5:1፤ 6:4፤ 12:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 236

ዮሐንስ 11:56

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 236

ዮሐንስ 11:57

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማሰር።”

ተዛማጅ ሐሳብ

ዮሐ. 11:1ሉቃስ 10:38
ዮሐ. 11:2ማቴ 26:6, 7፤ ማር 14:3፤ ዮሐ 12:3
ዮሐ. 11:4ዮሐ 9:1-3
ዮሐ. 11:8ዮሐ 1:38
ዮሐ. 11:8ዮሐ 8:59፤ 10:31
ዮሐ. 11:9ዮሐ 9:4፤ 12:35
ዮሐ. 11:11መዝ 13:3፤ ማቴ 9:24፤ ሥራ 7:59, 60፤ 1ቆሮ 15:6
ዮሐ. 11:14መክ 9:5
ዮሐ. 11:16ዮሐ 11:8
ዮሐ. 11:20ሉቃስ 10:38, 39
ዮሐ. 11:24ኢሳ 26:19፤ ዮሐ 5:28, 29፤ ሥራ 24:15፤ ዕብ 11:35፤ ራእይ 20:12
ዮሐ. 11:25ዮሐ 14:6
ዮሐ. 11:26ዮሐ 8:51
ዮሐ. 11:28ማቴ 23:8፤ ዮሐ 13:13
ዮሐ. 11:31ዮሐ 11:17
ዮሐ. 11:35ሉቃስ 19:41፤ ዕብ 4:15
ዮሐ. 11:37ዮሐ 9:6, 7
ዮሐ. 11:40ዮሐ 9:1-3
ዮሐ. 11:41ማቴ 14:19፤ ማር 7:34, 35
ዮሐ. 11:42ዮሐ 12:28-30፤ 17:8
ዮሐ. 11:43ሉቃስ 7:12, 14
ዮሐ. 11:45ዮሐ 2:23፤ 10:42፤ 12:10, 11
ዮሐ. 11:47ዮሐ 12:37፤ ሥራ 4:15, 16
ዮሐ. 11:49ማቴ 26:3፤ ሉቃስ 3:2፤ ሥራ 4:5, 6
ዮሐ. 11:542ሳሙ 13:23፤ 2ዜና 13:19
ዮሐ. 11:55ዘፀ 12:14፤ ዘዳ 16:1፤ ዮሐ 2:13፤ 5:1፤ 6:4፤ 12:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
  • 50
  • 51
  • 52
  • 53
  • 54
  • 55
  • 56
  • 57
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዮሐንስ 11:1-57

የዮሐንስ ወንጌል

11 ማርያምና እህቷ ማርታ+ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ አልዓዛር የተባለ ሰው ታሞ ነበር። 2 ማርያም በጌታ ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ያፈሰሰችውና በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው+ ሴት ስትሆን የታመመውም፣ ወንድሟ አልዓዛር ነበር። 3 ስለዚህ እህቶቹ “ጌታ ሆይ፣ የምትወደው ሰው ታሟል” ሲሉ መልእክት ላኩበት። 4 ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ ሕመም ለአምላክ ክብር የሚያመጣ ነው+ እንጂ በሞት የሚያበቃ አይደለም፤ ይህም የአምላክ ልጅ በዚህ አማካኝነት ክብር ይጎናጸፍ ዘንድ ነው” አለ።

5 ኢየሱስ ማርታንና እህቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወዳቸው ነበር። 6 ይሁን እንጂ አልዓዛር መታመሙን ከሰማ በኋላ በዚያው በነበረበት ቦታ ሁለት ቀን ቆየ። 7 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን “ተመልሰን ወደ ይሁዳ እንሂድ” አላቸው። 8 ደቀ መዛሙርቱ ግን “ረቢ፣+ በቅርቡ እኮ የይሁዳ ሰዎች በድንጋይ ሊወግሩህ ፈልገው ነበር፤+ ታዲያ ወደዚያ ተመልሰህ ልትሄድ ነው?” አሉት። 9 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ብርሃን የሚሆንበት 12 ሰዓት አለ አይደል?+ ማንም ሰው በቀን ብርሃን የሚሄድ ከሆነ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ ምንም ነገር አያደናቅፈውም። 10 ሆኖም በሌሊት የሚሄድ ሰው በእሱ ዘንድ ብርሃን ስለሌለ ይደናቀፋል።”

11 ይህን ከነገራቸው በኋላም “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤+ እኔም ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” አላቸው። 12 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶ ከሆነ ይሻለዋል” አሉት። 13 ይሁንና ኢየሱስ የተናገረው ስለመሞቱ ነበር። እነሱ ግን ለማረፍ ብሎ እንቅልፍ ስለመተኛቱ የተናገረ መሰላቸው። 14 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ እንዲህ አላቸው፦ “አልዓዛር ሞቷል፤+ 15 ታምኑ ዘንድ በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። ያም ሆነ ይህ ወደ እሱ እንሂድ።” 16 በዚህ ጊዜ ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ ለተቀሩት ደቀ መዛሙርት “ከእሱ ጋር እንድንሞት አብረነው እንሂድ” አላቸው።+

17 ኢየሱስ እዚያ በደረሰ ጊዜ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን እንደሆነው አወቀ። 18 ቢታንያ ለኢየሩሳሌም ቅርብ የነበረች ሲሆን ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል* ርቀት ላይ ትገኝ ነበር። 19 ወንድማቸውን በሞት ያጡትን ማርታንና ማርያምን ለማጽናናት ብዙ አይሁዳውያን መጥተው ነበር። 20 ማርታ፣ ኢየሱስ እየመጣ መሆኑን ስትሰማ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም+ ግን እዚያው ቤት ቀረች። 21 ማርታም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር። 22 አሁንም ቢሆን አምላክ የጠየቅከውን ነገር ሁሉ እንደሚሰጥህ አምናለሁ።” 23 ኢየሱስም “ወንድምሽ ይነሳል” አላት። 24 ማርታም “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንደሚነሳ አውቃለሁ” አለችው።+ 25 ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ።+ በእኔ የሚያምን* ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል፤ 26 በሕይወት ያለና በእኔ የሚያምን ሁሉ ደግሞ ፈጽሞ አይሞትም።+ ይህን ታምኛለሽ?” 27 እሷም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆንህን አምናለሁ” አለችው። 28 ይህን ካለች በኋላም ሄዳ እህቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታት “መምህሩ+ መጥቷል፤ እየጠራሽ ነው” አለቻት። 29 ማርያምም ይህን ስትሰማ በፍጥነት ተነስታ ወደ እሱ ሄደች።

30 ይሁንና ኢየሱስ እዚያው ማርታ ያገኘችው ቦታ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር። 31 እሷን እያጽናኑ በቤት አብረዋት የነበሩ አይሁዳውያንም ማርያም ፈጥና ተነስታ ስትወጣ ሲያዩ ወደ መቃብሩ+ ሄዳ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት። 32 ማርያምም ኢየሱስ የነበረበት ቦታ ደርሳ ባየችው ጊዜ እግሩ ላይ ተደፋች፤ ከዚያም “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። 33 ኢየሱስ እሷ ስታለቅስና አብረዋት የመጡት አይሁዳውያን ሲያለቅሱ ሲያይ እጅግ አዘነ፤* ተረበሸም። 34 እሱም “የት ነው ያኖራችሁት?” አለ። እነሱም “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት። 35 ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።+ 36 በዚህ ጊዜ አይሁዳውያኑ “እንዴት ይወደው እንደነበር ተመልከቱ!” አሉ። 37 ሆኖም ከእነሱ መካከል አንዳንዶች “የዓይነ ስውሩን ዓይን ያበራው ይህ ሰው+ ይሄኛውንም እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ።

38 ከዚያም ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ታውኮ ወደ መቃብሩ መጣ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን በድንጋይም ተዘግቶ ነበር። 39 ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” አለ። የሟቹ እህት ማርታም “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል” አለችው። 40 ኢየሱስም “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?” አላት።+ 41 ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመልክቶ+ እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። 42 እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።”+ 43 ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ።+ 44 የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው።

45 በመሆኑም ወደ ማርያም መጥተው ከነበሩትና ያደረገውን ነገር ካዩት አይሁዳውያን መካከል ብዙዎቹ በእሱ አመኑ፤+ 46 አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ነገሯቸው። 47 ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሳንሄድሪንን ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች እያደረገ ስለሆነ ምን ብናደርግ ይሻላል?+ 48 እንዲሁ ብንተወው ሁሉም በእሱ ያምናሉ፤ ሮማውያንም መጥተው ቦታችንንና* ሕዝባችንን ይወስዱብናል።” 49 ሆኖም ከመካከላቸው አንዱ፣ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ+ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ምንም አታውቁም፤ 50 ደግሞም ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ፣ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት እንደሚሻል ማሰብ ተስኗችኋል።” 51 ይሁንና ይህን የተናገረው ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት ስለነበረ ኢየሱስ ለሕዝቡ እንደሚሞት ትንቢት መናገሩ ነበር፤ 52 የሚሞተውም ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ተበታትነው ያሉትን የአምላክ ልጆችም አንድ ላይ መሰብሰብ ይችል ዘንድ ነው። 53  ስለዚህ ከዚያን ቀን አንስቶ ሊገድሉት አሴሩ።

54 በመሆኑም ኢየሱስ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በአይሁዳውያን መካከል በይፋ መንቀሳቀስ አቆመ፤ ከዚህ ይልቅ በምድረ በዳ አቅራቢያ ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ በዚያም ኤፍሬም+ ተብላ በምትጠራ ከተማ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። 55 በዚህ ወቅት የአይሁዳውያን ፋሲካ+ ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከፋሲካ በፊት የመንጻት ሥርዓት ለመፈጸም ከገጠር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። 56 ኢየሱስንም ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደሱም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ጭራሽ ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” ይባባሉ ነበር። 57  የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን መያዝ* እንዲችሉ እሱ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሁሉ እንዲጠቁማቸው አዘው ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ