የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፍጥረት የመጽሐፉ ይዘት

      • በሰባተኛው ቀን አምላክ ከሥራው አረፈ (1-3)

      • የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ (4)

      • የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት በኤደን ገነት (5-25)

        • ሰው ከአፈር ተሠራ (7)

        • የተከለከለው የእውቀት ዛፍ (15-17)

        • ሴት ከአዳም ተፈጠረች (18-25)

ዘፍጥረት 2:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሠራዊታቸውን ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ነህ 9:6፤ መዝ 146:6

ዘፍጥረት 2:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 31:17፤ ዕብ 4:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 70, 173

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 56

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2012፣ ገጽ 22

    10/1/2001፣ ገጽ 30

    7/15/1998፣ ገጽ 14-16

ዘፍጥረት 2:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2023፣ ገጽ 5-6

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 88

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2012፣ ገጽ 22

    7/15/2011፣ ገጽ 24

    10/1/2001፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 2:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    አምላክ ብቻ የሚጠራበት የግል ስሙ ይኸውም יהוה (የሐወሐ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው እዚህ ላይ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ4ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 45:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው፣ ርዕስ 2

ዘፍጥረት 2:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/1998፣ ገጽ 9

ዘፍጥረት 2:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።” በዕብራይስጥ ነፈሽ ሲሆን ቃል በቃል ሲተረጎም “የሚተነፍስ ፍጥረት” ማለት ነው። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:19፤ መዝ 103:14፤ መክ 3:20
  • +ዘፍ 7:22፤ ኢሳ 42:5፤ ሥራ 17:25
  • +1ቆሮ 15:45, 47

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 71

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 4 2017፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/2009፣ ገጽ 4

    9/1/2009፣ ገጽ 12-13

    4/1/1999፣ ገጽ 14-15

    10/1/1997፣ ገጽ 19

    9/1/1994፣ ገጽ 8

    እውቀት፣ ገጽ 81

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 116

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 72-73

    ማመራመር፣ ገጽ 85

ዘፍጥረት 2:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:15፤ 3:23
  • +ዘፍ 1:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2018፣ ገጽ 3-4

ዘፍጥረት 2:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:22, 24፤ ራእይ 2:7
  • +ዘፍ 2:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1643

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2011፣ ገጽ 7-8

    4/15/1999፣ ገጽ 7-8

    ማመራመር፣ ገጽ 245

ዘፍጥረት 2:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አራት ራስ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2011፣ ገጽ 5-6

ዘፍጥረት 2:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሙጫ በሞቃታማ አካባቢዎች ከሚበቅሉ ትናንሽ ዛፎች የሚገኝ ከርቤ የሚመስል ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ ነው።

ዘፍጥረት 2:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የኩሽ።” ይህ ቦታ ከየት እስከ የት ያለውን አካባቢ እንደሚያመለክት በትክክል አይታወቅም።

ዘፍጥረት 2:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሂዲኬል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 10:4
  • +ዘፍ 10:8, 11
  • +ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 11:24

ዘፍጥረት 2:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:28፤ 2:8፤ መዝ 115:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2023፣ ገጽ 16

ዘፍጥረት 2:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 2:8, 9፤ 3:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 160

    አምላክን አምልክ፣ ገጽ 42-43

    እውቀት፣ ገጽ 57

ዘፍጥረት 2:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:19፤ መዝ 146:4፤ መክ 9:5, 10፤ ሕዝ 18:4፤ ሮም 5:12፤ 1ቆሮ 15:22

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 160

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 3 2019፣ ገጽ 8

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2018፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/2015፣ ገጽ 4

    9/15/2014፣ ገጽ 24-25

    1/1/2003፣ ገጽ 4

    1/15/2001፣ ገጽ 4-5

    3/1/1991፣ ገጽ 5

    ንቁ!፣

    6/2006፣ ገጽ 28-29

    አምላክን አምልክ፣ ገጽ 42-43, 61-62

    ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ ገጽ 21

    እውቀት፣ ገጽ 57-58

ዘፍጥረት 2:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 11:8, 9፤ 1ጢሞ 2:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2023፣ ገጽ 23

    ንቁ!፣

    11/2013፣ ገጽ 15

    3/8/2005፣ ገጽ 22-23

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2012፣ ገጽ 25

    9/1/2012፣ ገጽ 4-5

    5/15/2011፣ ገጽ 8-9

    11/15/2000፣ ገጽ 24-25

    7/15/1995፣ ገጽ 10-11

    7/1/1991፣ ገጽ 9

    የቤተሰብ ደስታ፣ ገጽ 34

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 239

    ማመራመር፣ ገጽ 431

ዘፍጥረት 2:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2023፣ ገጽ 16

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2016፣ ገጽ 29

    ንቁ!፣

    12/2011፣ ገጽ 10

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 94-95

ዘፍጥረት 2:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2011፣ ገጽ 7

    9/1/2009፣ ገጽ 13

ዘፍጥረት 2:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 10:9፤ 1ጢሞ 2:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2011፣ ገጽ 7

    9/1/2009፣ ገጽ 13

    1/1/2004፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 2:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 11:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2004፣ ገጽ 30

ዘፍጥረት 2:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አብሮ ይኖራል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሚል 2:16፤ ማቴ 19:5፤ ማር 10:7, 8፤ ሮም 7:2፤ 1ቆሮ 6:16፤ ኤፌ 5:31፤ ዕብ 13:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 16, 58, 130

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 42

    ንቁ!፣

    ቁጥር 1 2021፣ ገጽ 4

    5/8/2005፣ ገጽ 21

    3/8/2002፣ ገጽ 6

    2/8/2001፣ ገጽ 28-29

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2017፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 8

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2011፣ ገጽ 13

    1/15/2011፣ ገጽ 14-16

    2/1/2010፣ ገጽ 27

    1/1/2004፣ ገጽ 30

    11/15/2000፣ ገጽ 25

    ለሰው ሁሉ፣ ገጽ 23

    ማመራመር፣ ገጽ 249

ዘፍጥረት 2:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 3:7

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፍ. 2:1ነህ 9:6፤ መዝ 146:6
ዘፍ. 2:2ዘፀ 31:17፤ ዕብ 4:4
ዘፍ. 2:4ኢሳ 45:18
ዘፍ. 2:7ዘፍ 3:19፤ መዝ 103:14፤ መክ 3:20
ዘፍ. 2:7ዘፍ 7:22፤ ኢሳ 42:5፤ ሥራ 17:25
ዘፍ. 2:71ቆሮ 15:45, 47
ዘፍ. 2:8ዘፍ 2:15፤ 3:23
ዘፍ. 2:8ዘፍ 1:26
ዘፍ. 2:9ዘፍ 3:22, 24፤ ራእይ 2:7
ዘፍ. 2:9ዘፍ 2:17
ዘፍ. 2:14ዳን 10:4
ዘፍ. 2:14ዘፍ 10:8, 11
ዘፍ. 2:14ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 11:24
ዘፍ. 2:15ዘፍ 1:28፤ 2:8፤ መዝ 115:16
ዘፍ. 2:16ዘፍ 2:8, 9፤ 3:2
ዘፍ. 2:17ዘፍ 3:19፤ መዝ 146:4፤ መክ 9:5, 10፤ ሕዝ 18:4፤ ሮም 5:12፤ 1ቆሮ 15:22
ዘፍ. 2:181ቆሮ 11:8, 9፤ 1ጢሞ 2:13
ዘፍ. 2:19ዘፍ 1:26
ዘፍ. 2:22ማር 10:9፤ 1ጢሞ 2:13
ዘፍ. 2:231ቆሮ 11:8
ዘፍ. 2:24ሚል 2:16፤ ማቴ 19:5፤ ማር 10:7, 8፤ ሮም 7:2፤ 1ቆሮ 6:16፤ ኤፌ 5:31፤ ዕብ 13:4
ዘፍ. 2:25ዘፍ 3:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፍጥረት 2:1-25

ዘፍጥረት

2 በዚህ መንገድ ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ* የመፍጠሩ ሥራ ተጠናቀቀ።+ 2 በሰባተኛውም ቀን አምላክ ይሠራው የነበረውን ሥራ አጠናቀቀ፤ በሰባተኛውም ቀን ይሠራው ከነበረው ሥራ ሁሉ ማረፍ ጀመረ።+ 3 አምላክም ሰባተኛውን ቀን ባረከው እንዲሁም ቀደሰው፤ ምክንያቱም አምላክ ከመፍጠር ሥራው ሁሉ፣ ሊሠራ ካሰበው ነገር ሁሉ ያረፈው ከዚያ ቀን አንስቶ ነው።

4 ሰማያትና ምድር በተፈጠሩበት ጊዜ፣ ይሖዋ* አምላክ ምድርንና ሰማይን በሠራበት+ ቀን የተከናወነው ነገር ይህ ነው።

5 በዚህ ጊዜ በምድር ላይ ምንም ዓይነት የሜዳ ቁጥቋጦ አልነበረም፤ እንዲሁም በሜዳ ላይ ምንም ዓይነት ተክል አልበቀለም፤ ምክንያቱም ይሖዋ አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ አላደረገም ነበር፤ መሬቱን የሚያለማም ሰው አልነበረም። 6 ይሁንና ተን ከምድር እየተነሳ መላውን መሬት ያጠጣ ነበር።

7 ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤+ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤+ ሰውየውም ሕያው ሰው* ሆነ።+ 8 በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ በስተ ምሥራቅ፣ በኤደን የአትክልት ስፍራ ተከለ፤+ የሠራውንም ሰው+ በዚያ አስቀመጠው። 9 ከዚያም ይሖዋ አምላክ ለማየት የሚያስደስተውንና ለምግብነት መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከመሬት አበቀለ። በተጨማሪም በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሕይወት ዛፍ+ እንዲሁም የመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ+ አበቀለ።

10 የአትክልቱን ስፍራ የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ወጥቶ ይፈስ ነበር፤ ከዚያም ተከፋፍሎ አራት ወንዝ* ሆነ። 11 የመጀመሪያው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ ይህ ወንዝ ወርቅ የሚገኝበትን መላውን የሃዊላ ምድር የሚከብ ነው። 12 የዚያ አገር ወርቅ ምርጥ ነው። በተጨማሪም በዚያ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫና* የኦኒክስ ድንጋዮች ይገኛሉ። 13 የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ ይህ ወንዝ መላውን የኢትዮጵያ* ምድር የሚከብ ነው። 14 የሦስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ*+ ነው፤ ይህ ወንዝ ከአሦር+ በስተ ምሥራቅ የሚፈስ ነው። አራተኛው ወንዝ ደግሞ ኤፍራጥስ+ ነው።

15 ይሖዋ አምላክ ሰውየውን ወስዶ እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።+ 16 በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ ለሰውየው ይህን ትእዛዝ ሰጠው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ሁሉ እስክትረካ ድረስ መብላት ትችላለህ።+ 17 ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ግን አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”+

18 ከዚያም ይሖዋ አምላክ “ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም። ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እሠራለታለሁ”+ አለ። 19 ይሖዋ አምላክም እያንዳንዱን የዱር እንስሳ እንዲሁም በሰማያት ላይ የሚበረውን እያንዳንዱን ፍጥረት ከአፈር ሠርቶ ነበር፤ ከዚያም ሰውየው እያንዳንዳቸውን ምን ብሎ እንደሚጠራቸው ለማየት ሁሉንም ወደ እሱ አመጣቸው፤ ሰውየው ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር* የሰጠው መጠሪያም የዚያ ፍጡር ስም ሆነ።+ 20 በመሆኑም ሰውየው ለቤት እንስሳት በሙሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበርሩ ፍጥረታት እንዲሁም ለዱር እንስሳት ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለሰው ግን ማሟያ የሚሆን ረዳት አልነበረውም። 21 ስለሆነም ይሖዋ አምላክ በሰውየው ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ እንቅልፍ ወስዶት ሳለም ከጎድን አጥንቶቹ አንዷን ወሰደ፤ ቦታውንም በሥጋ ደፈነው። 22 ይሖዋ አምላክም ከሰውየው የወሰዳትን የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ሴቲቱንም ወደ ሰውየው አመጣት።+

23 በዚህ ጊዜ ሰውየው እንዲህ አለ፦

“እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣

የሥጋዬም ሥጋ ናት።

እሷ ከወንድ ስለተገኘች+

‘ሴት’ ትባላለች።”

24 በዚህም ምክንያት ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል።* ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።+ 25 ሰውየውም ሆነ ሚስቱ ራቁታቸውን ነበሩ፤+ እንደዚያም ሆኖ ኀፍረት አይሰማቸውም ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ