የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 28
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • ማልታ ደሴት ደረሱ (1-6)

      • የፑፕልዮስ አባት ተፈወሰ (7-10)

      • ወደ ሮም ጉዟቸውን ቀጠሉ (11-16)

      • ጳውሎስ በሮም የሚገኙ አይሁዳውያንን አነጋገረ (17-29)

      • ጳውሎስ ለሁለት ዓመት ያህል በድፍረት ሰበከ (30, 31)

የሐዋርያት ሥራ 28:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 27:26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 209-210

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/15/2004፣ ገጽ 30-31

የሐዋርያት ሥራ 28:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ባዕድ ቋንቋ የሚናገሩት ሰዎችም።”

  • *

    ወይም “ሰብዓዊ ደግነት።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/15/2002፣ ገጽ 19

    5/1/1999፣ ገጽ 30

የሐዋርያት ሥራ 28:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

የሐዋርያት ሥራ 28:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ግሪክኛ ዳይክ፣ የበቀል እርምጃ የምትወስድን ሴት አምላክ ወይም የፍትሕን ጽንሰ ሐሳብ ሊያመለክት ይችላል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2015፣ ገጽ 9

    5/1/1999፣ ገጽ 30-31

የሐዋርያት ሥራ 28:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

የሐዋርያት ሥራ 28:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 16፣ ገጽ 15

የሐዋርያት ሥራ 28:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 4:38, 39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 210

የሐዋርያት ሥራ 28:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:8

የሐዋርያት ሥራ 28:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/1991፣ ገጽ 20

የሐዋርያት ሥራ 28:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 211

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/2009፣ ገጽ 9

የሐዋርያት ሥራ 28:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 211

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2007፣ ገጽ 30

የሐዋርያት ሥራ 28:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 211

የሐዋርያት ሥራ 28:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 211-212

የሐዋርያት ሥራ 28:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሰዎች የሚመገቡበት እና የሚያርፉበት ቦታ ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 1:3, 4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 212-213

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2020፣ ገጽ 16-17

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/1/2010፣ ገጽ 11

    10/15/2006፣ ገጽ 14, 16-17

    12/15/2004፣ ገጽ 16-17

የሐዋርያት ሥራ 28:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 213

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2013፣ ገጽ 14

የሐዋርያት ሥራ 28:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 24:11, 12፤ 25:8
  • +ሥራ 21:33

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 213-214

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 24

የሐዋርያት ሥራ 28:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 24:10
  • +ሥራ 23:26, 29፤ 25:24, 25፤ 26:31, 32

የሐዋርያት ሥራ 28:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 25:11, 12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 213-214

የሐዋርያት ሥራ 28:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 23:6፤ 26:6፤ ኤፌ 6:19, 20፤ 2ጢሞ 1:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 214

የሐዋርያት ሥራ 28:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 213-214

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2001፣ ገጽ 24

የሐዋርያት ሥራ 28:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 24:14
  • +ሉቃስ 2:34፤ ዮሐ 15:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/1994፣ ገጽ 5

    7/1/1993፣ ገጽ 3, 13

የሐዋርያት ሥራ 28:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በተሟላ ሁኔታ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:2, 3
  • +ዮሐ 5:46
  • +ሥራ 26:22, 23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 215

    መጠበቂያ ግንብ፣

    1/15/2012፣ ገጽ 12-13

የሐዋርያት ሥራ 28:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2003፣ ገጽ 22-23

የሐዋርያት ሥራ 28:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 215

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 100

የሐዋርያት ሥራ 28:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 11:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 100

የሐዋርያት ሥራ 28:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 6:9, 10፤ ማቴ 13:14, 15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 215

    የኢሳይያስ ትንቢት 1፣ ገጽ 100

የሐዋርያት ሥራ 28:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 3:4, 6፤ ሥራ 13:45, 46፤ 22:21፤ ሮም 11:11
  • +መዝ 67:2፤ 98:3፤ ኢሳ 11:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 215

የሐዋርያት ሥራ 28:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።

የሐዋርያት ሥራ 28:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 28:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 216-217

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2013፣ ገጽ 14-15

    1/15/2007፣ ገጽ 32

    12/15/2001፣ ገጽ 24

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 17፣ ገጽ 6

የሐዋርያት ሥራ 28:31

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በድፍረት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 6:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 216-217

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2013፣ ገጽ 14-15

    1/15/2007፣ ገጽ 32

    5/15/2006፣ ገጽ 14

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 28:1ሥራ 27:26
ሥራ 28:8ሉቃስ 4:38, 39
ሥራ 28:9ማቴ 10:8
ሥራ 28:152ቆሮ 1:3, 4
ሥራ 28:17ሥራ 24:11, 12፤ 25:8
ሥራ 28:17ሥራ 21:33
ሥራ 28:18ሥራ 24:10
ሥራ 28:18ሥራ 23:26, 29፤ 25:24, 25፤ 26:31, 32
ሥራ 28:19ሥራ 25:11, 12
ሥራ 28:20ሥራ 23:6፤ 26:6፤ ኤፌ 6:19, 20፤ 2ጢሞ 1:16
ሥራ 28:22ሥራ 24:14
ሥራ 28:22ሉቃስ 2:34፤ ዮሐ 15:19
ሥራ 28:23ሥራ 17:2, 3
ሥራ 28:23ዮሐ 5:46
ሥራ 28:23ሥራ 26:22, 23
ሥራ 28:26ሮም 11:8
ሥራ 28:27ኢሳ 6:9, 10፤ ማቴ 13:14, 15
ሥራ 28:28ሉቃስ 3:4, 6፤ ሥራ 13:45, 46፤ 22:21፤ ሮም 11:11
ሥራ 28:28መዝ 67:2፤ 98:3፤ ኢሳ 11:10
ሥራ 28:30ሥራ 28:16
ሥራ 28:31ኤፌ 6:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 28:1-31

የሐዋርያት ሥራ

28 እኛም በደህና ወደ የብስ ደረስን፤ ደሴቲቱም ማልታ ተብላ እንደምትጠራ አወቅን።+ 2 የአካባቢው ነዋሪዎችም* የተለየ ደግነት* አሳዩን። ዝናብ መዝነብ ጀምሮ ስለነበረና ብርድ ስለነበር እሳት በማቀጣጠል ሁላችንንም በደግነት አስተናገዱን። 3 ይሁን እንጂ ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ውስጥ ሲጨምር ከሙቀቱ የተነሳ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች። 4 ባዕድ ቋንቋ የሚናገሩትም ሰዎች እፉኝቷ እጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ መሆን አለበት፤ ከባሕሩ ተርፎ በደህና ቢወጣም እንኳ ፍትሕ* በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ይባባሉ ጀመር። 5 እሱ ግን እፉኝቷን እሳቱ ላይ አራገፋት፤ አንዳችም ጉዳት አልደረሰበትም። 6 ሆኖም ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ወድቆ ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ብዙ ጠብቀው ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ይህ ሰው አምላክ ነው ይሉ ጀመር።

7 በዚያ አካባቢ፣ ፑፕልዮስ የተባለ የደሴቲቱ አስተዳዳሪ ርስት ነበረው፤ እሱም በእንግድነት ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን። 8 የፑፕልዮስ አባት ትኩሳትና ተቅማጥ ይዞት ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስም ወደ እሱ ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም ጫነበትና ፈወሰው።+ 9 ይህ ከሆነ በኋላ በደሴቲቱ የሚኖሩ የታመሙ ሌሎች ሰዎችም ወደ እሱ እየመጡ ይፈወሱ ጀመር።+ 10 በተጨማሪም ብዙ ስጦታ በመስጠት አክብሮታቸውን ገለጹልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ ጫኑልን።

11 ከሦስት ወር በኋላም “የዙስ ልጆች” የሚል ዓርማ ባለው መርከብ ጉዞ ጀመርን። ይህ መርከብ ከእስክንድርያ የመጣ ሲሆን ክረምቱን ያሳለፈው በዚህች ደሴት ነበር። 12 በስራኩስ ወደሚገኘው ወደብ ከደረስን በኋላ በዚያ ሦስት ቀን ቆየን፤ 13 ከዚያም ተነስተን በመጓዝ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ ስለተነሳ በሁለተኛው ቀን ፑቲዮሉስ ደረስን። 14 በዚያም ወንድሞችን አገኘን፤ እነሱም ሰባት ቀን አብረናቸው እንድንቆይ ለመኑን፤ እነሱ ጋር ከቆየን በኋላ ወደ ሮም አመራን። 15 በዚያ የነበሩ ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዩስ የገበያ ስፍራና ሦስት ማደሪያ* እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ። ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ አምላክን አመሰገነ፤ እንዲሁም ተበረታታ።+ 16 በመጨረሻም ሮም በደረስን ጊዜ ጳውሎስ አንድ ወታደር እየጠበቀው ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።

17 ይሁን እንጂ ከሦስት ቀን በኋላ የአይሁዳውያንን ታላላቅ ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። ሰዎቹም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ ምንም እንኳ ሕዝቡን ወይም የአባቶቻችንን ልማድ የሚጻረር ነገር ያልፈጸምኩ+ ቢሆንም በኢየሩሳሌም አስረው ለሮማውያን አሳልፈው ሰጥተውኛል።+ 18 እነሱም ከመረመሩኝ+ በኋላ ለሞት የሚያበቃ ምንም ጥፋት ስላላገኙብኝ ሊፈቱኝ ፈልገው ነበር።+ 19 ሆኖም አይሁዳውያን ይህን በተቃወሙ ጊዜ ለቄሳር ይግባኝ ለማለት ተገደድኩ፤+ ይህን ያደረግኩት ግን ሕዝቤን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም። 20 እናንተንም ለማየትና ለማነጋገር ጥያቄ ያቀረብኩት ለዚህ ነው፤ በዚህ ሰንሰለት የታሰርኩትም ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።”+ 21 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ስለ አንተ የተጻፈ ከይሁዳ የመጣ ምንም ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከዚያ ከመጡት ወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ክፉ ነገር የተናገረ ወይም ያወራ አንድም ሰው የለም። 22 ሆኖም ስለዚህ ኑፋቄ+ በየቦታው መጥፎ ነገር እንደሚወራ ስለምናውቅ+ የአንተን ሐሳብ ደግሞ መስማት ተገቢ ይመስለናል።”

23 በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ከእሱ ጋር ቀን ከወሰኑ በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ስፍራው መጡ። እሱም በኢየሱስ እንዲያምኑ ለማድረግ+ ከሙሴ ሕግና+ ከነቢያት+ እየጠቀሰ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ* በመመሥከር ጉዳዩን አብራራላቸው። 24 አንዳንዶቹ የተናገረውን ነገር ሲያምኑ ሌሎቹ ግን አላመኑም። 25 እርስ በርስ ሊስማሙ ስላልቻሉም ለመሄድ ተነሱ፤ በዚህ ጊዜ ጳውሎስ የሚከተለውን የመጨረሻ ሐሳብ ተናገረ፦

“መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ለአባቶቻችሁ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ትክክል ነበር፦ 26 ‘ወደዚህ ሕዝብ ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ “መስማቱን ትሰማላችሁ፤ ግን በፍጹም አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ፤ ግን በፍጹም ልብ አትሉም።+ 27 ምክንያቱም በዓይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው እንዲሁም በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል፤ በጆሯቸው ሰምተው ምላሽ አልሰጡም፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።”’+ 28 ስለዚህ አምላክ ሰዎችን ስለሚያድንበት መንገድ የሚናገረው ይህ መልእክት ለአሕዛብ እንደተላከ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤+ እነሱም በእርግጥ ይሰሙታል።”+ 29 *——

30 ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤+ ወደ እሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደግነት ያስተናግዳቸው ነበር፤ 31 ያለምንም እንቅፋት በታላቅ የመናገር ነፃነት* ስለ አምላክ መንግሥት ይሰብክላቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራቸው ነበር።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ