ኢሳይያስ
በእናቴ ማህፀን ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ ስሜን ጠርቷል።
የሾለ ፍላጻ አደረገኝ፤
በኮሮጆው ውስጥ ሸሸገኝ።
4 እኔ ግን “የደከምኩት በከንቱ ነው።
ጉልበቴንም ያፈሰስኩት ከንቱ ለሆነና ምንም ፋይዳ ለሌለው ነገር ነው።
በይሖዋ ፊት እከብራለሁ፤
አምላኬም ብርታቴ ይሆናል።
7 እስራኤልን የሚቤዠው፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆነው ይሖዋ፣+ እጅግ ለተናቀውና*+ በሕዝብ ለተጠላው የገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦
8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤+
ለሰዎች ቃል ኪዳን አድርጌ እሰጥህ ዘንድ ጠብቄሃለሁ፤+
ይህም ምድሪቱን ዳግመኛ እንድታቋቁም፣
የወደመውን ርስታቸውን መልሰህ እንድታወርሳቸው፣+
በጨለማ ያሉትንም+ ‘ራሳችሁን ግለጡ!’ እንድትል ነው።
በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤
በተበላሹ መንገዶችም* ሁሉ አጠገብ መሰማሪያ ያገኛሉ።
11 ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤
አውራ ጎዳናዎቼም ከፍ ያሉ ይሆናሉ።+
13 እናንተ ሰማያት፣ እልል በሉ፤ አንቺም ምድር፣ ሐሴት አድርጊ።+
ተራሮች በደስታ እልል ይበሉ።+
ይሖዋም ረስቶኛል”+ ትላለች።
15 እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለች?
ከማህፀኗ ለወጣውስ ልጅ አትራራም?
እነዚህ ሴቶች ቢረሱ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልረሳሽም።+
16 እነሆ፣ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ።
ግንቦችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።
17 ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ።
ያፈራረሱሽና ያወደሙሽ አንቺን ለቀው ይሄዳሉ።
18 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ።
ሁሉም በአንድነት እየተሰበሰቡ ነው።+
ወደ አንቺም እየመጡ ነው።
“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፣
“አንቺም ሁሉንም እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤
እንደ ሙሽራም ትጎናጸፊያቸዋለሽ።
20 የወላድ መሃን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱት ወንዶች ልጆች፣
ጆሮሽ እየሰማ ‘ይህ ቦታ በጣም ጠቦናል።
የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይላሉ።+
21 አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦
‘እኔ ልጆቼን በሞት ያጣሁና መሃን
እንዲሁም በምርኮ የተወሰድኩና እስረኛ የሆንኩ ሴት ሆኜ ሳለ
እነዚህን ልጆች የወለደልኝ ማን ነው?
ያሳደጋቸውስ ማን ነው?+
22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
24 በምርኮ የተያዙ ሰዎች ከኃያል ሰው እጅ ሊወሰዱ ይችላሉ?
ወይስ በጨቋኝ እጅ የወደቁ ምርኮኞችን የሚታደጋቸው ይኖራል?
25 ይሖዋ ግን እንዲህ ይላል፦
አንቺን የሚቃወሙትን እቃወማለሁ፤+
ወንዶች ልጆችሽንም አድናቸዋለሁ።
26 በደል የሚፈጽሙብሽን የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤
ልክ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ።