የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 34
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • አዲስ የድንጋይ ጽላቶች ተዘጋጁ (1-4)

      • ሙሴ የይሖዋን ክብር አየ (5-9)

      • ቃል ኪዳኑ የያዘው ዝርዝር ሐሳብ በድጋሚ ተነገረ (10-28)

      • የሙሴ ፊት አንጸባረቀ (29-35)

ዘፀአት 34:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 10:1
  • +ዘፀ 32:19፤ ዘዳ 9:17
  • +ዘዳ 9:10

ዘፀአት 34:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:20፤ 24:12

ዘፀአት 34:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:12, 13

ዘፀአት 34:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 7:38
  • +ዘፀ 6:3፤ 33:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 10/2020፣ ገጽ 3

ዘፀአት 34:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቸር።”

  • *

    ወይም “ፍቅራዊ ደግነቱና።”

  • *

    ወይም “ታማኝነቱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 6:36
  • +ዘፀ 22:27፤ 2ዜና 30:9፤ ነህ 9:17፤ መዝ 86:15፤ ኢዩ 2:13
  • +ዘኁ 14:18፤ 2ጴጥ 3:9
  • +ኤር 31:3፤ ሰቆ 3:22፤ ሚክ 7:18
  • +መዝ 31:5፤ ሮም 2:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 276-278

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    11/2021፣ ገጽ 2-3

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 7

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2017፣ ገጽ 8

    ንቁ!፣

    7/2011፣ ገጽ 6-7

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2009፣ ገጽ 18

    5/15/2005፣ ገጽ 23-25

    1/15/2002፣ ገጽ 13-15, 17-18

    10/1/1998፣ ገጽ 8, 12-13

    እውቀት፣ ገጽ 28-30

ዘፀአት 34:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 9:4
  • +መዝ 103:12፤ ኢሳ 55:7፤ ኤፌ 4:32፤ 1ዮሐ 1:9
  • +ዘዳ 32:35፤ ኢያሱ 24:19፤ ሮም 2:5፤ 2ጴጥ 2:4፤ ይሁዳ 14, 15
  • +ዘፀ 20:5፤ ዘዳ 30:19፤ 1ሳሙ 15:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 114-117

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2009፣ ገጽ 18

    5/15/2005፣ ገጽ 23-25

    1/15/2002፣ ገጽ 13-15, 17-18

    እውቀት፣ ገጽ 28-30

ዘፀአት 34:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:9፤ 33:3
  • +ዘፀ 33:14
  • +ዘኁ 14:19

ዘፀአት 34:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተፈጥረው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:23፤ መዝ 147:19, 20
  • +ዘፀ 33:16፤ ዘዳ 10:21

ዘፀአት 34:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:5, 6፤ ዘዳ 12:28
  • +ዘፀ 3:8፤ 33:2፤ ዘዳ 7:1

ዘፀአት 34:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 7:2
  • +ዘፀ 23:32, 33

ዘፀአት 34:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:24፤ ዘዳ 12:3

ዘፀአት 34:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ተቀናቃኞቹን የማይታገሥ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:3፤ 1ቆሮ 10:14፤ 1ዮሐ 5:21
  • +ኢያሱ 24:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 125

    ንጹሕ አምልኮ፣ ገጽ 164-165

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1657-1658

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2002፣ ገጽ 28

    9/15/1995፣ ገጽ 8-9

ዘፀአት 34:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 10:20
  • +ዘኁ 25:2፤ 2ቆሮ 6:14

ዘፀአት 34:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 9:2
  • +ዘዳ 7:4፤ 31:16፤ መሳ 2:17፤ 8:33፤ 1ነገ 11:2፤ ነህ 13:26፤ መዝ 106:28

ዘፀአት 34:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:8፤ ዘሌ 19:4

ዘፀአት 34:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ15ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 23:6
  • +ዘፀ 23:15

ዘፀአት 34:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ማህፀን የሚከፍተው ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:2፤ ሉቃስ 2:23
  • +ዘፀ 22:30

ዘፀአት 34:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:15፤ ዘኁ 18:15, 16

ዘፀአት 34:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰንበትን ታከብራለህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:12

ዘፀአት 34:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የዳስ (የማደሪያ ድንኳን) በዓል በመባልም ይታወቃል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:16፤ ዘሌ 23:34

ዘፀአት 34:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወንድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:16

ዘፀአት 34:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/1998፣ ገጽ 20

ዘፀአት 34:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:18
  • +ዘፀ 12:10፤ ዘኁ 9:12

ዘፀአት 34:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 18:8, 12፤ ዘዳ 26:2፤ ምሳሌ 3:9
  • +ዘፀ 23:19፤ ዘዳ 14:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2004፣ ገጽ 27

ዘፀአት 34:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 24:8፤ ዘዳ 4:13
  • +ዘፀ 24:4፤ ዘዳ 31:9, 11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 108

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 179-181

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2012፣ ገጽ 26

ዘፀአት 34:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    እዚህ ላይ “እሱ” የሚለው ቃል ይሖዋን እንደሚያመለክት መረዳት ይቻላል። ዘፀ 34:1ን ተመልከት።

  • *

    ቃል በቃል “አሥርቱን ቃላት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 9:18
  • +ዘፀ 31:18፤ ዘዳ 10:2

ዘፀአት 34:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 32:15

ዘፀአት 34:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 3:7

ዘፀአት 34:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 24:3፤ ዘዳ 1:3

ዘፀአት 34:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 3:13

ዘፀአት 34:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 3:16
  • +ዘዳ 27:10

ዘፀአት 34:35

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እሱን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 3:7, 13

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 34:1ዘዳ 10:1
ዘፀ. 34:1ዘፀ 32:19፤ ዘዳ 9:17
ዘፀ. 34:1ዘዳ 9:10
ዘፀ. 34:2ዘፀ 19:20፤ 24:12
ዘፀ. 34:3ዘፀ 19:12, 13
ዘፀ. 34:5ሥራ 7:38
ዘፀ. 34:5ዘፀ 6:3፤ 33:19
ዘፀ. 34:6ሉቃስ 6:36
ዘፀ. 34:6ዘፀ 22:27፤ 2ዜና 30:9፤ ነህ 9:17፤ መዝ 86:15፤ ኢዩ 2:13
ዘፀ. 34:6ዘኁ 14:18፤ 2ጴጥ 3:9
ዘፀ. 34:6ኤር 31:3፤ ሰቆ 3:22፤ ሚክ 7:18
ዘፀ. 34:6መዝ 31:5፤ ሮም 2:2
ዘፀ. 34:7ዳን 9:4
ዘፀ. 34:7መዝ 103:12፤ ኢሳ 55:7፤ ኤፌ 4:32፤ 1ዮሐ 1:9
ዘፀ. 34:7ዘዳ 32:35፤ ኢያሱ 24:19፤ ሮም 2:5፤ 2ጴጥ 2:4፤ ይሁዳ 14, 15
ዘፀ. 34:7ዘፀ 20:5፤ ዘዳ 30:19፤ 1ሳሙ 15:2
ዘፀ. 34:9ዘፀ 32:9፤ 33:3
ዘፀ. 34:9ዘፀ 33:14
ዘፀ. 34:9ዘኁ 14:19
ዘፀ. 34:102ሳሙ 7:23፤ መዝ 147:19, 20
ዘፀ. 34:10ዘፀ 33:16፤ ዘዳ 10:21
ዘፀ. 34:11ዘፀ 19:5, 6፤ ዘዳ 12:28
ዘፀ. 34:11ዘፀ 3:8፤ 33:2፤ ዘዳ 7:1
ዘፀ. 34:12ዘዳ 7:2
ዘፀ. 34:12ዘፀ 23:32, 33
ዘፀ. 34:13ዘፀ 23:24፤ ዘዳ 12:3
ዘፀ. 34:14ዘፀ 20:3፤ 1ቆሮ 10:14፤ 1ዮሐ 5:21
ዘፀ. 34:14ኢያሱ 24:19
ዘፀ. 34:151ቆሮ 10:20
ዘፀ. 34:15ዘኁ 25:2፤ 2ቆሮ 6:14
ዘፀ. 34:16ዕዝራ 9:2
ዘፀ. 34:16ዘዳ 7:4፤ 31:16፤ መሳ 2:17፤ 8:33፤ 1ነገ 11:2፤ ነህ 13:26፤ መዝ 106:28
ዘፀ. 34:17ዘፀ 32:8፤ ዘሌ 19:4
ዘፀ. 34:18ዘሌ 23:6
ዘፀ. 34:18ዘፀ 23:15
ዘፀ. 34:19ዘፀ 13:2፤ ሉቃስ 2:23
ዘፀ. 34:19ዘፀ 22:30
ዘፀ. 34:20ዘፀ 13:15፤ ዘኁ 18:15, 16
ዘፀ. 34:21ዘዳ 5:12
ዘፀ. 34:22ዘፀ 23:16፤ ዘሌ 23:34
ዘፀ. 34:23ዘዳ 16:16
ዘፀ. 34:24ዘፀ 34:11
ዘፀ. 34:25ዘፀ 23:18
ዘፀ. 34:25ዘፀ 12:10፤ ዘኁ 9:12
ዘፀ. 34:26ዘኁ 18:8, 12፤ ዘዳ 26:2፤ ምሳሌ 3:9
ዘፀ. 34:26ዘፀ 23:19፤ ዘዳ 14:21
ዘፀ. 34:27ዘፀ 24:8፤ ዘዳ 4:13
ዘፀ. 34:27ዘፀ 24:4፤ ዘዳ 31:9, 11
ዘፀ. 34:28ዘዳ 9:18
ዘፀ. 34:28ዘፀ 31:18፤ ዘዳ 10:2
ዘፀ. 34:29ዘፀ 32:15
ዘፀ. 34:302ቆሮ 3:7
ዘፀ. 34:32ዘፀ 24:3፤ ዘዳ 1:3
ዘፀ. 34:332ቆሮ 3:13
ዘፀ. 34:342ቆሮ 3:16
ዘፀ. 34:34ዘዳ 27:10
ዘፀ. 34:352ቆሮ 3:7, 13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 34:1-35

ዘፀአት

34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጥረብ፤+ እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው+ በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።+ 2 አንተም በጠዋት ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው አናት ላይ በፊቴ ስለምትቆም በጠዋት ለመሄድ ተዘጋጅ።+ 3 ሆኖም ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይውጣ፤ ደግሞም በተራራው ላይ በየትኛውም ቦታ ሌላ ማንም ሰው አይታይ። ሌላው ቀርቶ በጎችም ሆኑ ከብቶች እንኳ በተራራው ፊት ለፊት አይሰማሩ።”+

4 በመሆኑም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ከጠረበ በኋላ በጠዋት ተነስቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር። 5 ከዚያም ይሖዋ በደመና ውስጥ ወርዶ+ በዚያ ከእሱ ጋር ሆነ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሙን አወጀ።+ 6 ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና+ ሩኅሩኅ*+ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣+ ታማኝ ፍቅሩና*+ እውነቱ*+ እጅግ ብዙ የሆነ፣ 7 ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣+ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፣+ ጥፋተኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ+ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በልጅ ልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ።”+

8 ሙሴም ወዲያውኑ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። 9 ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ይሖዋ፣ እኛ ግትር* ሕዝብ ብንሆንም+ በመካከላችን ሆነህ አብረኸን ሂድ፤+ ደግሞም ስህተታችንንና ኃጢአታችንን ይቅር በል፤+ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።” 10 እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፦ በመላው ምድርም ሆነ በብሔራት ሁሉ መካከል ፈጽሞ ተደርገው* የማያውቁ ድንቅ ነገሮችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ፤+ ለአንተ ስል የማደርገው ነገር የሚያስፈራ ስለሆነ በመካከላቸው የምትኖረው ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋን ሥራ ያያሉ።+

11 “እኔ ዛሬ የማዝህን ነገር ልብ በል።+ እኔም አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አስወጣቸዋለሁ።+ 12 በምትሄድበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤+ አለዚያ ወጥመድ ይሆንብሃል።+ 13 ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ትቆራርጣላችሁ።+ 14 ይሖዋ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ* አምላክ በመሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ ለሌላ አምላክ አትስገድ።+ አዎ፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።+ 15 ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት+ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ።+ 16 ከዚያም ሴቶች ልጆቻቸውን ከወንዶች ልጆችህ ጋር ታጋባለህ፤+ ሴቶች ልጆቻቸውም አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር መፈጸማቸው እንዲሁም ወንዶች ልጆችህ የእነሱን አማልክት በማምለክ ምንዝር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው አይቀርም።+

17 “ከቀለጠ ብረት አማልክት አትሥራ።+

18 “የቂጣን በዓል ታከብራለህ።+ ልክ ባዘዝኩህ መሠረት ቂጣ ትበላለህ፤ ከግብፅ የወጣኸው በአቢብ* ወር+ ስለሆነ በአቢብ ወር በተወሰነው ጊዜ ላይ ለሰባት ቀን ይህን ታደርጋለህ።

19 “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው፤+ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው።+ 20 የአህያን በኩር በበግ ዋጀው። የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ትዋጀዋለህ።+ ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ።

21 “ስድስት ቀን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ።*+ በሚታረስበትም ሆነ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅትም እንኳ ታርፋለህ።

22 “የሳምንታት በዓልህን መጀመሪያ በደረሰው የስንዴ በኩር አክብር፤ የአዝመራ መክተቻን በዓልም* በዓመቱ ማብቂያ ላይ አክብር።+

23 “የአንተ የሆነ ሰው* ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ የእስራኤል አምላክ በሆነው በእውነተኛው ጌታ በይሖዋ ፊት ይቅረብ።+ 24 ብሔራትን ከፊትህ አስወጣለሁና፤+ ክልልህንም ሰፊ አደርገዋለሁ፤ የአምላክህን የይሖዋን ፊት ለማየት በዓመት ሦስቴ በምትወጣበት ጊዜ ማንም ምድርህን አይመኝም።

25 “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር አድርገህ አታቅርብ።+ የፋሲካ በዓል መሥዋዕት እስከ ጠዋት ድረስ መቆየት የለበትም።+

26 “መጀመሪያ የደረሰውን የአፈርህን ምርጥ ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አምጣ።+

“የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።”+

27 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው+ በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ”+ አለው። 28 እሱም በዚያ ከይሖዋ ጋር 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆየ። እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም።+ እሱም* በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃላት ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት* ጻፈ።+

29 ከዚያም ሙሴ ከሲና ተራራ ወረደ፤ ሁለቱንም የምሥክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ነበር።+ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር ስለቆየ ከተራራው በወረደበት ጊዜ ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አላወቀም ነበር። 30 አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ሲያዩት ፊቱ እንደሚያንጸባርቅ አስተዋሉ፤ ወደ እሱ ለመቅረብም ፈሩ።+

31 ሙሴ ግን ጠራቸው፤ በመሆኑም አሮንና የማኅበረሰቡ አለቆች በሙሉ ወደ እሱ መጡ፤ ሙሴም አነጋገራቸው። 32 ከዚያም እስራኤላውያን በሙሉ ወደ እሱ ቀረቡ፤ እሱም ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ሰጣቸው።+ 33 ሙሴም ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን ነበር።+ 34 ሙሴ፣ ይሖዋ ፊት ቀርቦ ከእሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ግን ከዚያ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያነሳ ነበር።+ ከዚያም ወጥቶ የተቀበለውን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን ይነግራቸው ነበር።+ 35 እስራኤላውያንም የሙሴ ፊት እንደሚያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ ከዚያም ሙሴ አምላክን* ለማነጋገር ወደ ውስጥ እስከሚገባበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ ፊቱ ላይ አደረገው።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ