የ1999 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያዎች
በ1999 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ትምህርቶቹ የተወሰዱባቸው ጽሑፎች፦ ክፍሎቹ በሚከተሉት ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ:- መጽሐፍ ቅዱስ [1954]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ ንቁ! [g-AM] “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si]፣ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? [fy-AM]፣ እና እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው? [gt-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና በሰላምታ ይከፈትና እንደሚከተለው ይቀጥላል:-
ክፍል ቁ. 1፦ 15 ደቂቃ። ይህ ክፍል በሽማግሌ ወይም በጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ ወይም በንቁ! መጽሔት አለዚያም “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! በሚቀርብበት ጊዜ ለ15 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ሆኖ ይቀርባል። የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ” ከተባለው መጽሐፍ በሚቀርብበት ጊዜ ከ10 እስከ 12 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርብና በጽሑፉ ላይ ባሉት ጥያቄዎች በመጠቀም ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የሚፈጅ የክለሳ ጥያቄ ይቀርባል። ዓላማው የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለጉባኤው በጣም ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ በትምህርቱ ተግባራዊ ተቀሜታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይገባል። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም ይገባል።
ይህንን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች በተወሰነው ጊዜ ለመጨረስ ንቁ መሆን አለባቸው። በግል ምክር ከተሰጣቸው በምክር መስጫ ቅጻቸው ላይ ተገቢው ምልክት ሊደረግ ይገባል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 6 ደቂቃ። ይህ ክፍል ትምህርቱን ለጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በጥሩ ሁኔታ ማዛመድ በሚችል ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ሊቀርብ ይገባል። የተመደቡትን ምዕራፎች ሐሳብ በመከለስ ብቻ መቅረብ የለበትም። የተመደቡትን ምዕራፎች አጠቃላይ ሐሳብ ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ውስጥ መከለስ ይቻላል። ቢሆንም ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት ሊጠቅመን እንደሚችል እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ከዚህ በኋላ ተማሪዎቹ ወደየክፍላቸው መሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ወንድም የሚቀርብ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ነው። ትምህርት ቤቱ በሚካሄድበት በዋናው አዳራሽም ይሁን በተጨማሪዎቹ ቡድኖች ዘንድ ይህ ክፍል በዚሁ መንገድ ይቀርባል። ምንባቡ ብዙውን ጊዜ አጠር ያለ ስለሚሆን ተማሪው በመግቢያውና በመደምደሚያው ላይ መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት ያስችለዋል። ከበስተኋላ ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ትንቢታዊ ወይም መሠረተ ትምህርታዊ ትርጉሙንና የመሠረታዊ ሥርዓቶቹን ተግባራዊነት መጥቀስ ይቻላል። የተመደቡት ጥቅሶች በሙሉ ሳይቆራረጡ መነበብ ይኖርባቸዋል። የሚነበቡት ጥቅሶች ተከታታይ ካልሆኑ ግን ተማሪው ቀጥሎ የሚያነበውን ጥቅስ ቁጥር መናገር ይችላል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፍ ላይ ነው። መቼቱ መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት፣ ተመላልሶ መጠይቅ፣ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም ሌላ ዓይነት የመስክ አገልግሎት ገጽታ ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ጊዜ አንዲት ወላጅ ከትንሽ ልጅዋ ጋር ስትወያይ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። በክፍሉ ውስጥ የሚሳተፉ ክፍሉን ሲያቀርቡ መቀመጥ ወይም መቆም ይችላሉ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተለይ ተማሪዋ የቤቱን ባለቤት ወይም ልጅዋን ስለ ትምህርቱ እንዲያስቡና ጥቅሶቹ እንዴት በሥራ ላይ እንደሚውሉ እንዲገነዘቡ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል፤ ሆኖም ተጨማሪ ረዳት ማዘጋጀት ይቻላል። ተማሪዋ የቤቱ ባለቤት የተወሰኑ አንቀጾችን እንዲያነብ ማድረግ ወይም አለማድረግ ትችላለች። በአንደኛ ደረጃ ሊታሰብበት የሚገባው መቼቱ ሳይሆን ትምህርቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ መቅረቡ ነው።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም ወይም ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው እስከ ዛሬ ድረስ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው በተባለው መጽሐፍ ላይ ነው። የእያንዳንዱ ክፍል ጭብጥ በፕሮግራሙ ላይ ሰፍሯል። ክፍሉ ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ ለጠቅላላው ጉባኤ በንግግር መልክ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ ለእህት ከተሰጠ ለሦስተኛው ክፍል በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል።
ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም፦ ይህ ክፍል በእያንዳንዱ ሳምንት ከመዝሙር ቁጥር በኋላ በቅንፍ ውስጥ ተቀምጧል። ፕሮግራሙን በመከተል በየሳምንቱ አሥር የሚሆኑ ገጾችን በማንበብ መላውን መጽሐፍ ቅዱስ በሦስት ዓመት ውስጥ አንብቦ መጨረስ ይቻላል። በትምህርት ቤቱ ፕሮግራም ውስጥም ይሁን በክለሳ ጥያቄዎች ውስጥ ከተጨማሪው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ምንም ክፍል አይወሰድም።
ማሳሰቢያ፦ ምክር መስጠትን፣ ጊዜ መጠበቅን፣ የክለሣ ጥያቄዎችንና ክፍሎች መዘጋጀትን በሚመለከት ተጨማሪ ሐሳብ ወይም መመሪያ ለማግኘት የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3ን ተመልከቱ።
ፕሮግራም
ጥር 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 16–18
መዝሙር ቁ. 80 (180) [2 ነገሥት 16-19]
ቁ. 1፦ አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ አነሳሽነት ያስጻፈበት መንገድ (w97 6/15 ገጽ 4-8)
ቁ. 2፦ ራእይ 16:1-16
ቁ. 3፦ የቤተሰብ ሕይወት አደጋ ተጋርጦበታል (fy ገጽ 5-9 አን. 1-14)
ቁ. 4፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠውን ታላቅ ሰው ለይቶ ማወቅ (gt መግቢያው አን. 1-4)
ጥር 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ራእይ 19–22
መዝሙር ቁ. 44 (105) [2 ነገሥት 20–25]
ቁ. 1፦ ራእይ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 268–9 አን. 28–34)
ቁ. 2፦ ራእይ 22:1-15
ቁ. 3፦ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ቁልፍ (fy ገጽ 10-12 አን. 15-23)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው ነውን? (gt መግቢያው አን. 5-11)
ጥር 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 1–3
መዝሙር ቁ. 78 (175) [1 ዜና 1–6]
ቁ. 1፦ የዘፍጥረት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 13-14 አን. 1-8)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 1:1-13
ቁ. 3፦ ትዳር ለመመሥረት ዝግጁ ናችሁን? (fy ገጽ 13-15 አን. 1-6)
ቁ. 4፦ በእርግጥ ኢየሱስ ማን ነበር? (gt መግቢያው አን. 12-15)
ጥር 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 4–6
መዝሙር ቁ. 71 (163) [1 ዜና 7–13]
ቁ. 1፦ የሌሎችን ሐሳብ በመጥፎ ከመተርጎም ተጠንቀቁ (w97 5/15 ገጽ 26-29)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 4:1-16
ቁ. 3፦ ራሳችሁን ማወቅና ሐቁን መቀበል የሚኖርባችሁ ለምንድን ነው? (fy ገጽ 16-18 አን. 7-10)
ቁ. 4፦ ኢየሱስን ከሁሉ የበለጠ ታላቅ ሰው ያደረገው ነገር (gt መግቢያው አን. 16-19)
የካቲት 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 7–9
መዝሙር ቁ. 19 (43) [1 ዜና 14–21]
ቁ. 1፦ ክርስቲያኖች ቁማር መጫወት ይገባቸዋልን? (g95 ሚያዝያ-ሰኔ ገጽ 28-9)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 7:1-16
ቁ. 3፦ ለማግባት የምትፈልጉት ሰው ሊያሟላው የሚገባ ብቃት (fy ገጽ 18-22 አን. 11-15)
ቁ. 4፦ ስለ ኢየሱስ መማር የሚገባን ለምንድን ነው? እንዴትስ መማር እንችላለን? (gt መግቢያው አን. 20-23)
የካቲት 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 10–12
መዝሙር ቁ. 54 (132) [1 ዜና 22–29]
ቁ. 1፦ የውሸት እውነተኛ ገጽታ (g98 ጥር ገጽ 23-25)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 12:1-20
ቁ. 3፦ ዘላቂ የሆነ ቃል ኪዳን ከመግባት በፊት ሊታሰቡባቸው የሚገቡ ነገሮች (fy ገጽ 22-24 አን. 16-19)
ቁ. 4፦ ገብርኤል ለዘካርያስና ለማርያም ተገለጠላቸው (gt ምዕ. 1)
የካቲት 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 13-15
መዝሙር ቁ. 13 (33) [2 ዜና 1-8]
ቁ. 1፦ የሰው ልጅ ደካማነት የይሖዋን ኃይል አጉልቶ ያሳያል (w97 6/1 ገጽ 24-27)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 14:8-20
ቁ. 3፦ በመጠናናት የምታሳልፉት ጊዜ ንጽሕ ይሁን፤ ከሠርጉ ቀን ባሻገር ተመልከቱ (fy ገጽ 24-26 አን. 20-23)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ክብር ተሰጥቶታል (gt ምዕ. 2)
የካቲት 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 16-19
መዝሙር ቁ. 20 (45) [2 ዜና 9-17]
ቁ. 1፦ ጸሎቶችህ ምን ያረጋግጣሉ (w97 7/1 ገጽ 27-30)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 18:1-15
ቁ. 3፦ የተሳካ ትዳር ለመመሥረት ዝግጁ እንድትሆን ሊረዱህ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች (fy ገጽ 26 የክለሳ ሣጥን)
ቁ. 4፦ የዮሐንስ መወለድ (gt ምዕ. 3)
መጋቢት 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 20-23
መዝሙር ቁ. 88 (200) [2 ዜና 18-24]
ቁ. 1፦ ሕሊናህን ማሰልጠን የምትችልበት መንገድ (w97 8/1 ገጽ 4-6)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 23:1-13
ቁ. 3፦ ትዳርን ዘላቂ ለማድረግ የሚረዳ የመጀመሪያው ቁልፍ (fy ገጽ 27-9 አን. 1-6)
ቁ. 4፦ ዮሴፍ የጸነሰችውን ማርያምን አገባ (gt ምዕ. 4)
መጋቢት 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 24-25
መዝሙር ቁ. 85 (191) [2 ዜና 25-31]
ቁ. 1፦ እውነት ነፃ የሚያወጣን ከምን ነገር ነው? (w97 2/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 24:1-4, 10-21
ቁ. 3፦ ትዳርን ዘላቂ ለማድረግ የሚረዳ ሁለተኛው ቁልፍ (fy ገጽ 30-1 አን. 7-10)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ የተወለደው የትና መቼ ነው? (gt ምዕ. 5)
መጋቢት 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 26-28
መዝሙር ቁ. 57 (136) [2 ዜና 32-36]
ቁ. 1፦ ሙዚቃ በዘመናዊ አምልኮ ውስጥ ያለው ቦታ (w97 2/1 ገጽ 24-28)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 26:1-14
ቁ. 3፦ የወንዶች የራስነት ሥልጣን አጠቃቀም የክርስቶስ ዓይነት መሆን ይኖርበታል (fy ገጽ 31–34 አን. 11-15)
ቁ. 4፦ ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተሰጠበት ልጅ (gt ምዕ. 6)
መጋቢት 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 29-31
መዝሙር ቁ. 2 (4) [ዕዝራ 1-7]
ቁ. 1፦ ጭንቀትን ለመቋቋም ምን ሊረዳህ ይችላል? (g95 ሐምሌ-መስከረም ገጽ 12-13)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 31:1-18
ቁ. 3፦ ሚስት ለባሏ ማሟያ የሆነችው እንዴት ነው? (fy ገጽ 34-5 አን. 16-19)
ቁ. 4፦ ኢየሱስና ኮከብ ቆጣሪዎች (gt ምዕ. 7)
መጋቢት 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 32-35
መዝሙር ቁ. 60 (143) [ዕዝራ 8–ነህምያ 4]
ቁ. 1፦ አምላክ ተአምራዊ ፈውሶችን የሚያከናውነው መቼ ነው? (w97 7/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 35:1-15
ቁ. 3፦ ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ ሲባል ምን ማለት ነው? (fy ገጽ 35-8 አን. 20-6)
ቁ. 4፦ ከጨካኝ ገዥ እጅ ማምለጥ (gt ምዕ. 8)
ሚያዝያ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 36-38
መዝሙር ቁ. 45 (106) [ነህምያ 5-11]
ቁ. 1፦ መዳን በእርግጥ ምን ማለት ነው? (w97 8/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 38:6-19, 24-26
ቁ. 3፦ ዘላቂና አስደሳች የሆነ ትዳር ለመመሥረት የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች (fy ገጽ 38 የክለሳ ሣጥን)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ በቤተሰብ ውስጥ ያሳለፈው የልጅነት ሕይወት (gt ምዕ. 9)
ሚያዝያ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 39-41
መዝሙር ቁ. 14 (34) [ነህምያ 12–አስቴር 5]
ቁ. 1፦ ኃጢአትን መግለጥ ለምን አስፈለገ? (w97 8/15 ገጽ 26-30)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 40:1-15
ቁ. 3፦ እንደ አቅማችሁ ኑሩ (fy ገጽ 39-41 አን. 1-6)
ቁ. 4፦ በ12 ዓመቱ በኢየሩሳሌም (gt ምዕ. 10)
ሚያዝያ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 42-44
መዝሙር ቁ. 29 (62) [አስቴር 6–ኢዮብ 5]
ቁ. 1፦ ለክብርህ የምትቆመው እስከ ምን ድረስ ነው? (w98 2/15 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 42:1-17
ቁ. 3፦ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ማከናወን የሁሉም የቤተሰብ አባላት ተግባር ነው (fy ገጽ 42-44 አን. 7-11)
ቁ. 4፦ ዮሐንስ ለኢየሱስ መንገዱን አዘጋጀ (gt ምዕ. 11)
ሚያዝያ 26 የጽሑፍ ክለሳ። ከራእይ 16 እስከ ዘፍጥረት 44 ድረስ ያለውን ጨርሱ
መዝሙር ቁ. 7 (19) [ኢዮብ 6-14]
ግንቦት 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 45-47
መዝሙር ቁ. 23 (48) [ኢዮብ 15-23]
ቁ. 1፦ የመከር በዓላት አምላክን ያስደስታሉን? (w97 9/15 ገጽ 8-9)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 45:16–46:4
ቁ. 3፦ ይሖዋ ንጹሕ እንድንሆን የሚጠብቅብን ለምንድን ነው? (fy ገጽ 45-9 አን. 12-20)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ሲጠመቅ ምን ነገር ተከሰተ? (gt ምዕ. 12)
ግንቦት 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 48-50
መዝሙር ቁ. 34 (77) [ኢዮብ 24-33]
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 17-19 አን. 30-5)
ቁ. 2፦ ዘፍጥረት 49:13-28
ቁ. 3፦ ልባዊ ማበረታቻና ምስጋና በቤተሰብ ውስጥ የሚኖረው ሚና (fy ገጽ 49-50 አን. 21-22)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ከቀረቡለት ፈተናዎች መማር (gt ምዕ. 13)
ግንቦት 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 1-4
መዝሙር ቁ. 1 (3) [ኢዮብ 34-42]
ቁ. 1፦ የዘጸአት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 19-20 አን. 1-8)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 4:1-17
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልጆችና ስለ ቤተሰብ ኃላፊነት ያለው አመለካከት (fy ገጽ 51-3 አን. 1-5)
ቁ. 4፦ የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት (gt ምዕ. 14)
ግንቦት 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 5-8
መዝሙር ቁ. 18 (42) [መዝሙር 1-17]
ቁ. 1፦ ድሃ ግን ሀብታም—እንዴት? (w97 9/15 አን. 3-7)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 7:1-13
ቁ. 3፦ ልጃችሁ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማሟላት ሲባል ምን ማለት ነው? (fy ገጽ 53-5 አን. 6-9)
ቁ. 4፦ የመጀመሪያው የኢየሱስ ተዓምር (gt ምዕ. 15)
ግንቦት 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 9-12
መዝሙር ቁ. 35 (79) [መዝሙር 18-28]
ቁ. 1፦ የዓለም ክፍል አለመሆን ሲባል ምን ማለት ነው? (g98 የካቲት ገጽ 28-29)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 12:21-36
ቁ. 3፦ በልጆቻችሁ አእምሮ ውስጥ እውነትን ቅረጹ (fy ገጽ 55-7 አን. 10-15)
ቁ. 4፦ ኢየሱስ ለይሖዋ አምልኮ ያሳየው ቅንዓት (gt ምዕ. 16)
ሰኔ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 13-16
መዝሙር ቁ. 28 (58) [መዝሙር 29-38]
ቁ. 1፦ ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሁኔታዎች ሥር በተስፋ መኖር (w97 5/15 ገጽ 22-5)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 15:1-13
ቁ. 3፦ የይሖዋን መንገዶች ለልጃችሁ አስተምሩ (fy ገጽ 58-9 አን. 16-19)
ቁ. 4፦ ኒቆዲሞስን አስተማረ (gt ምዕ. 17)
ሰኔ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 17-20
መዝሙር ቁ. 39 (86) [መዝሙር 39-50]
ቁ. 1፦ ክርስቲያኖች አረጋውያን ወላጆችን የሚያከብሩበት መንገድ (w97 9/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 17:1-13
ቁ. 3፦ በተለያዩ መንገዶች የሚሰጥ ተግሣጽ ያለው ከፍተኛ ጥቅም (fy ገጽ 59–60 አን. 20-23)
ቁ. 4፦ ዮሐንስ እየቀነሰ ኢየሱስ ግን እየጨመረ ሄደ (gt ምዕ. 18)
ሰኔ 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 21-24
መዝሙር ቁ. 94 (212) [መዝሙር 51-65]
ቁ. 1፦ ይቅር ማለትና መርሳት የሚቻለው እንዴት ነው? (g95 ጥቅምት-ታኅሣሥ ገጽ 27-29)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 21:1-15
ቁ. 3፦ ልጆቻችሁን ከአደጋ ጠብቁ (fy ገጽ 61-3 አን. 24-8)
ቁ. 4፦ አንዲት ሳምራዊት ሴት አስተማረ (gt ምዕ. 19 አን. 1-14)
ሰኔ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 25-28
መዝሙር ቁ. 22 (47) [መዝሙር 66-74]
ቁ. 1፦ ሕያው አምላክ የሆነውን ይሖዋን እወቅ (w97 10/1 ገጽ 4-8)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 25:17-30
ቁ. 3፦ ወላጆች—ሐሳብ የምትለዋወጡበትን መሥመር ክፍት አድርጉት (fy ገጽ 64-7 አን. 1-7)
ቁ. 4፦ ብዙ ሳምራውያን ያመኑበት ምክንያት (gt ምዕ. 19 አን. 15-21)
ሐምሌ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 29-32
መዝሙር ቁ. 77 (174) [መዝሙር 75-85]
ቁ. 1፦ የዓለም መንፈስ እንዲመርዛችሁ አትፍቀዱለት (w97 10/1 ገጽ 25-9)
ቁ. 2፦ ዘጸአት 29:1-14
ቁ. 3፦ ለልጆቻችሁ ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ እሴቶችን አስተምሯቸው (fy ገጽ 67-71 አን. 8-14)
ቁ. 4፦ በቃና የፈጸመው ሁለተኛ ተዓምር (gt ምዕ. 20)
ሐምሌ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 33-36
መዝሙር ቁ. 69 (160) [መዝሙር 86-97]
ቁ. 1: እምነት የሚጣልብህ ሁን፤ ጽኑ አቋምህን ጠብቅ (w97 5/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2: ዘጸአት 34:17-28
ቁ. 3: ተግሣጽና አክብሮት ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (fy ገጽ 71-2 አን. 15-18)
ቁ. 4: ኢየሱስ ባደገባት ከተማ ሰበከ (gt ምዕ. 21)
ሐምሌ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘጸአት 37-40
መዝሙር ቁ. 17 (38) [መዝሙር 98-106]
ቁ. 1: ዘጸአት—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 24-5 አን. 26-31)
ቁ. 2: ዘጸአት 40:1-16
ቁ. 3: ልጆቻችሁ ለሥራና ለጨዋታ አምላካዊ አመለካከት እንዲኖራቸው አስተምሯቸው (fy ገጽ 72-5 አን. 19-25)
ቁ. 4: አራት ደቀ መዛሙርት ተጠሩ (gt ምዕ. 22)
ሐምሌ 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 1-4
መዝሙር ቁ. 9 (26) [መዝሙር 107-118]
ቁ. 1: የዘሌዋውያን መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 25-6 አን. 1-10)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 2:1-13
ቁ. 3: የልጆች ዓመፅና መንስኤዎቹ (fy ገጽ 76-9 አን. 1-8)
ቁ. 4: በቅፍርናሆም የተፈጸሙ ተጨማሪ ተዓምራት (gt ምዕ. 23)
ነሐሴ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 5-7
መዝሙር ቁ. 53 (130) [መዝሙር 119-125]
ቁ. 1: እውነተኛ ደስታ የሚገኝበት ቁልፍ (w97 10/15 ገጽ 5-7)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 6:1-13
ቁ. 3: ልልም አትሁኑ፤ እጅግም ጥብቅ አትሁኑ (fy ገጽ 80-2 አን. 9-13)
ቁ. 4: ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ምክንያት (gt ምዕ. 24)
ነሐሴ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 8-10
መዝሙር ቁ. 50 (123) [መዝሙር 126-143]
ቁ. 1: መሠረታዊ ሥርዓትን መረዳት ጉልምስናን ያንጸባርቃል (w97 10/15 ገጽ 28-30)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 10:12-20
ቁ. 3: ለአንድ ልጅ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት ዓመፅን ሊያስቀር ይችላል (fy ገጽ 82-5 አን. 14-18)
ቁ. 4: የሥጋ ደዌ ለያዘው ሰው ርኅራኄ ማሳየት (gt ምዕ. 25)
ነሐሴ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 11-13
መዝሙር ቁ. 45 (106) [መዝሙር 144–ምሳሌ 5]
ቁ. 1: “ከኤፊቆሮሳውያን” ተጠንቀቁ (w97 11/1 ገጽ 23-5)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 13:1-17
ቁ. 3: ችግር ውስጥ የገባን ልጅ መርዳት የሚቻልባቸው መንገዶች (fy ገጽ 85-7 አን. 19-23)
ቁ. 4: ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር በማለት ፈወሰ (gt ምዕ. 26)
ነሐሴ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 14-15
መዝሙር ቁ. 5 (10) [ምሳሌ 6-14]
ቁ. 1: በእርግጥ የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ ነው (w97 4/1 ገጽ 4-8)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 14:33-47
ቁ. 3: የለየለትን ዓመፀኛ ልጅ እንዴት መያዝ ይገባል? (fy ገጽ 87-9 አን 24-7)
ቁ. 4: ማቴዎስ ተጠራና ግብዣ አዘጋጀ (gt ምዕ. 27)
ነሐሴ 30 የጽሑፍ ክለሳ። ከዘፍጥረት 45 እስከ ዘሌዋውያን 15 ያለውን ጨርሱ
መዝሙር ቁ. 8 (21) [ምሳሌ 15-22]
መስከረም 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 16-18
መዝሙር ቁ. 100 (222) [ምሳሌ 23-31]
ቁ. 1: ሥቃይና መከራ የማይኖርበት ጊዜ (w97 2/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 16:20-31
ቁ. 3: ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ (fy ገጽ 90-2 አን. 1-7)
ቁ. 4: ስለ ጾም ተጠየቀ (gt ምዕ. 28)
መስከረም 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 19-21
መዝሙር ቁ. 24 (50) [መክብብ 1-12]
ቁ. 1: ቁጣን መቆጣጠር ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው? (g98 ኅዳር ገጽ 18-20)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 19:16-18, 26-37
ቁ. 3: አምላክ ስለ ፆታ ያለው አመለካከት (fy ገጽ 92-5 አን. 8-13)
ቁ. 4: በሰንበት መልካም ሥራ መሥራት (gt ምዕ. 29)
መስከረም 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 22-24
መዝሙር ቁ. 4 (8) [መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 1–ኢሳይያስ 5]
ቁ. 1: ማማረር ፈጽሞ ስህተት ነውን? (w97 12/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 23:15-25
ቁ. 3: ልጆቻችሁ ጥሩ ጓደኞችን እንዲመርጡ እርዷቸው (fy ገጽ 95-7 አን. 14-18)
ቁ. 4: ኢየሱስ ለከሳሾቹ መልስ ሰጠ (gt ምዕ. 30)
መስከረም 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 25-27
መዝሙር ቁ. 52 (129) [ኢሳይያስ 6-14]
ቁ. 1: ዘሌዋውያን—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 28-30 አን. 28-39)
ቁ. 2: ዘሌዋውያን 25:13-28
ቁ. 3: ጤናማ የቤተሰብ መዝናኛ መምረጥ (fy ገጽ 97-102 አን. 19-27)
ቁ. 4: በሰንበት ቀን እሸት መቅጠፍ በሕግ ተፈቅዷልን? (gt ምዕ. 31)
ጥቅምት 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 1-3
መዝሙር ቁ. 67 (156) [ኢሳይያስ 15-25]
ቁ. 1: የዘኁልቁ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 30-1 አን. 1-10)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 1:44-54
ቁ. 3: በነጠላ ወላጅ ለሚተዳደሩ ቤተሰቦች የሚሆን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስተዋል (fy ገጽ 103-6 አን. 1-8)
ቁ. 4: በሰንበት የተፈቀደው ምንድን ነው? (gt ምዕ. 32)
ጥቅምት 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 4-6
መዝሙር ቁ. 66 (155) [ኢሳይያስ 26-33]
ቁ. 1: ይሖዋ የሚገዛው በርኅራኄ ነው (w97 12/15 ገጽ 28-9)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 4:17-33
ቁ. 3: ነጠላ ወላጆች የሚገጥማቸው መተዳደሪያ የማግኘት ችግር (fy ገጽ 106-8 አን. 9-12)
ቁ. 4: የኢሳይያስን ትንቢት መፈጸም (gt ምዕ. 33)
ጥቅምት 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 7-9
መዝሙር ቁ. 87 (195) [ኢሳይያስ 34-41]
ቁ. 1: እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? (w97 3/15 ገጽ 23)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 9:1-14
ቁ. 3: በነጠላ ወላጅ ቤተሰብ ውስጥ ተግሣጽ መስጠት (fy ገጽ 108-10 አን. 13-17)
ቁ. 4: ሐዋርያቱን መምረጥ (gt ምዕ. 34)
ጥቅምት 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 10-12
መዝሙር ቁ. 28 (58) [ኢሳይያስ 42-49]
ቁ. 1: ይሖዋ መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች ያስባል (w97 4/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 10:11-13, 29-36
ቁ. 3: የብቸኝነትን ስሜት ማሸነፍ (fy ገጽ 110-13 አን. 18-22)
ቁ. 4: ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ዝነኛ ስብከት (gt ምዕ. 35 አን. 1-6)
ኅዳር 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 13-15
መዝሙር ቁ. 61 (144) [ኢሳይያስ 50-58]
ቁ. 1: ተዓምር ብቻውን እምነት የማይገነባበት ምክንያት (w97 3/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 14:13-25
ቁ. 3: በነጠላ ወላጅ ለሚተዳደሩ ቤተሰቦች እርዳታ ማበርከት የሚቻልበት መንገድ (fy ገጽ 113-15 አን. 23-7)
ቁ. 4: እውነተኛ ደስታ ያላቸው እነማን ናቸው? (gt ምዕ. 35 አን. 7-17)
ኅዳር 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 16-19
መዝሙር ቁ. 48 (113) [ኢሳይያስ 59-66]
ቁ. 1: ድህነት ለስርቆት ማሳበቢያ የማይሆነው ለምንድን ነው? (g98 መጋቢት ገጽ 22-3)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 18:1-14
ቁ. 3: የአምላክ ዓይነት ዝንባሌ በመያዝ ሕመምን መቋቋም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች (fy ገጽ 116-20 አን. 1-9)
ቁ. 4: ለተከታዮቹ ያወጣው ከፍተኛ የአቋም ደረጃ (gt ምዕ. 35 አን. 18-27)
ኅዳር 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 20-22
መዝሙር ቁ. 21 (46) [ኤርምያስ 1-6]
ቁ. 1: መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ዘመናችን የደረሰው እንዴት ነው?—ክፍል አንድ (w97 8/15 ገጽ 8-11)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 20:14-26
ቁ. 3: ፈዋሽ የሆነ መንፈስ ያለው ጠቀሜታ (fy ገጽ 120-22 አን. 10-13)
ቁ. 4: ጸሎትና በአምላክ መተማመን (gt ምዕ. 35 አን. 28-37)
ኅዳር 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 23-26
መዝሙር ቁ. 98 (220) [ኤርምያስ 7-13]
ቁ. 1: መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ዘመናችን የደረሰው እንዴት ነው?—ክፍል ሁለት (w97 9/15 ገጽ 25-9)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 23:1-12
ቁ. 3: ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ማስቀደም፤ ልጆችም በቤታቸው የተከሰተው ሕመም የፈጠረውን ችግር እንዲቋቋሙ መርዳት (fy ገጽ 122-24 አን. 14-18)
ቁ. 4: ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ (gt ምዕ. 35 አን. 38-49)
ኅዳር 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 27-30
መዝሙር ቁ. 80 (180) [ኤርምያስ 14-21]
ቁ. 1: መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ዘመናችን የደረሰው እንዴት ነው?—ክፍል ሦስት (w97 10/15 ገጽ 8-12)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 27:1-11
ቁ. 3: ሕክምናን በተመለከተ ሊኖረን የሚገባው አመለካከት (fy ገጽ 124-7 አን. 19-23)
ቁ. 4: አንድ የሠራዊት አለቃ ያሳየው ትልቅ እምነት (gt ምዕ. 36)
ታኅሣሥ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 31-32
መዝሙር ቁ. 43 (98) [ኤርምያስ 22-28]
ቁ. 1: የዘመናዊው የገና በዓል አመጣጥ (w97 12/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 31:13-24
ቁ. 3: አንዲት አማኝ ሚስት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ሰላም ማስፈን የምትችለው እንዴት ነው? (fy ገጽ 128-32 አን. 1-9)
ቁ. 4: ኢየሱስ የአንዲትን መበለት ሐዘን አስወገደ (gt ምዕ. 37)
ታኅሣሥ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኁልቁ 33-36
መዝሙር ቁ. 86 (193) [ኤርምያስ 29-34]
ቁ. 1: ዘኁልቁ ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 34-5 አን. 32-8)
ቁ. 2: ዘኁልቁ 36:1-13
ቁ. 3: አንድ አማኝ ባል በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ የሚችለው እንዴት ነው? (fy ገጽ 132-3 አን. 10-11)
ቁ. 4: ዮሐንስ እምነት ጎድሎት ነበርን? (gt ምዕ. 38)
ታኅሣሥ 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 1-3
መዝሙር ቁ. 84 (190) [ኤርምያስ 35-41]
ቁ. 1: የዘዳግም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 36-7 አን. 1-9)
ቁ. 2: ዘዳግም 2:1-15
ቁ. 3: በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ለልጆች የሚሰጥ ቅዱስ ጽሑፋዊ ሥልጠና (fy ገጽ 133-4 አን. 12-15)
ቁ. 4: ኩሩዎቹ እና ትሑቶቹ (gt ምዕ. 39)
ታኅሣሥ 27 የጽሑፍ ክለሳ። ከዘሌዋውያን 16 እስከ ዘዳግም 3 ድረስ ያሉትን ጨርሱ
መዝሙር ቁ. 96 (215) [ኤርምያስ 42-48]