የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጳውሎስና ሲላስ በተሰሎንቄ (1-9)

      • ጳውሎስና ሲላስ በቤርያ (10-15)

      • ጳውሎስ በአቴንስ (16-22ሀ)

      • ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ ያቀረበው ንግግር (22ለ-34)

የሐዋርያት ሥራ 17:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 2:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 133

የሐዋርያት ሥራ 17:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 9:19, 20፤ 13:13, 14፤ 14:1፤ 18:4
  • +ሥራ 18:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 88

    መመሥከር፣ ገጽ 134-135

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 18-19

    12/1/2008፣ ገጽ 30

    የአገልግሎት ትምህርት ቤት፣ ገጽ 251-252

የሐዋርያት ሥራ 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 22:7፤ 34:20፤ 69:21፤ 118:22፤ ኢሳ 50:6፤ 53:3, 5
  • +መዝ 16:10፤ ሉቃስ 24:45, 46

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 134-135

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 19

    12/1/2008፣ ገጽ 30

    ንቁ!፣

    7/8/1994፣ ገጽ 6

የሐዋርያት ሥራ 17:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 15:22, 40

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 135

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 19

    11/1/1997፣ ገጽ 10-11

የሐዋርያት ሥራ 17:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:45

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 135-136, 139

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 19

የሐዋርያት ሥራ 17:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ያወኩት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:19-21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 135-136

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 19-20

    6/1/1993፣ ገጽ 3

የሐዋርያት ሥራ 17:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 23:1, 2፤ ዮሐ 19:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 135-136

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 20

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 17፣ ገጽ 4

የሐዋርያት ሥራ 17:8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 16፣ ገጽ 15

የሐዋርያት ሥራ 17:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዋስ ተቀብለው።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 136

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2012፣ ገጽ 20

የሐዋርያት ሥራ 17:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 136-137

የሐዋርያት ሥራ 17:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 137-138

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 2

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/2011፣ ገጽ 25

    4/15/2007፣ ገጽ 14-15

    10/15/1998፣ ገጽ 6

    5/15/1996፣ ገጽ 16-17

    ንቁ!፣

    3/2008፣ ገጽ 8-9

    8/2007፣ ገጽ 10-11

የሐዋርያት ሥራ 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 14:2, 19

የሐዋርያት ሥራ 17:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:23

የሐዋርያት ሥራ 17:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:1, 2፤ 1ተሰ 3:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2004፣ ገጽ 19

የሐዋርያት ሥራ 17:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 140

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1998፣ ገጽ 26-27

የሐዋርያት ሥራ 17:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሰዎች የሚገበያዩበት እንዲሁም ሕዝባዊ ስብሰባ የሚካሄድበት ገላጣ ስፍራ።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 140-141

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 18

የሐዋርያት ሥራ 17:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 5:28, 29፤ 11:25፤ 1ቆሮ 15:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 141-142

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2003፣ ገጽ 22

    8/1/2001፣ ገጽ 8

    7/15/1998፣ ገጽ 25, 27

የሐዋርያት ሥራ 17:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በጥንቷ አቴና የሚገኝ ኮረብታ ሲሆን በዚህ ቦታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ይሰበሰብ ነበር።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1638

የሐዋርያት ሥራ 17:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ለጉብኝት የመጡ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ንቁ!፣

    3/2011፣ ገጽ 18

የሐዋርያት ሥራ 17:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሃይማኖተኞች እንደሆናችሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 17:33, 34
  • +ሥራ 17:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ሰዎችን ውደዱ፣ ትምህርት 5

    መመሥከር፣ ገጽ 142-143

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    9/1/2007፣ ገጽ 14

    የአገልግሎት ትምህርት ቤት፣ ገጽ 252

የሐዋርያት ሥራ 17:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ሰዎችን ውደዱ፣ ትምህርት 5

    መመሥከር፣ ገጽ 143

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/2012፣ ገጽ 18

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    7/15/2002፣ ገጽ 32

    ንቁ!፣

    3/2011፣ ገጽ 18

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 64

የሐዋርያት ሥራ 17:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 146:6
  • +1ነገ 8:27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 144

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    7/1/2008፣ ገጽ 10

የሐዋርያት ሥራ 17:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 42:5
  • +መዝ 50:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 144

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 38

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    7/1/2008፣ ገጽ 10

የሐዋርያት ሥራ 17:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:28
  • +ዘፍ 5:2
  • +ዘዳ 2:5, 19፤ 32:8፤ መዝ 74:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች፣ ርዕስ 64

    መመሥከር፣ ገጽ 144-145

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    7/1/2008፣ ገጽ 10

    9/15/1998፣ ገጽ 12

    ለሰው ሁሉ፣ ገጽ 24-25

    ንቁ!፣

    10/8/1995፣ ገጽ 9

የሐዋርያት ሥራ 17:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:29፤ መዝ 145:18፤ ሮም 1:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 42

    መመሥከር፣ ገጽ 145

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30

    7/1/2008፣ ገጽ 10

የሐዋርያት ሥራ 17:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 145-146

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 38

    ንቁ!፣

    3/2011፣ ገጽ 18

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30-31

    6/15/2004፣ ገጽ 14

የሐዋርያት ሥራ 17:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:27
  • +ዘዳ 5:8፤ ኢሳ 37:19፤ 40:18-20፤ 46:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 146

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 30-31

    1/15/2004፣ ገጽ 32

የሐዋርያት ሥራ 17:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤፌ 4:17, 18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 146

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 31

የሐዋርያት ሥራ 17:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 96:13፤ 98:9፤ ዮሐ 5:22፤ ሥራ 10:42
  • +ዮሐ 11:25፤ ሥራ 2:24፤ 13:32, 33

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 147

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 31

    1/15/2008፣ ገጽ 20

    ራእይ፣ ገጽ 295-296

    ለዘላለም መኖር፣ ገጽ 175

የሐዋርያት ሥራ 17:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 1:23

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 147

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 31

    7/1/1998፣ ገጽ 12

የሐዋርያት ሥራ 17:34

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2010፣ ገጽ 31

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 17:11ተሰ 2:1
ሥራ 17:2ሥራ 9:19, 20፤ 13:13, 14፤ 14:1፤ 18:4
ሥራ 17:2ሥራ 18:19
ሥራ 17:3መዝ 22:7፤ 34:20፤ 69:21፤ 118:22፤ ኢሳ 50:6፤ 53:3, 5
ሥራ 17:3መዝ 16:10፤ ሉቃስ 24:45, 46
ሥራ 17:4ሥራ 15:22, 40
ሥራ 17:5ሥራ 13:45
ሥራ 17:6ሥራ 16:19-21
ሥራ 17:7ሉቃስ 23:1, 2፤ ዮሐ 19:12
ሥራ 17:13ሥራ 14:2, 19
ሥራ 17:14ማቴ 10:23
ሥራ 17:15ሥራ 16:1, 2፤ 1ተሰ 3:2
ሥራ 17:18ዮሐ 5:28, 29፤ 11:25፤ 1ቆሮ 15:12
ሥራ 17:22ሥራ 17:33, 34
ሥራ 17:22ሥራ 17:16
ሥራ 17:24መዝ 146:6
ሥራ 17:241ነገ 8:27
ሥራ 17:25ኢሳ 42:5
ሥራ 17:25መዝ 50:12
ሥራ 17:26ዘፍ 1:28
ሥራ 17:26ዘፍ 5:2
ሥራ 17:26ዘዳ 2:5, 19፤ 32:8፤ መዝ 74:17
ሥራ 17:27ዘዳ 4:29፤ መዝ 145:18፤ ሮም 1:20
ሥራ 17:29ዘፍ 1:27
ሥራ 17:29ዘዳ 5:8፤ ኢሳ 37:19፤ 40:18-20፤ 46:5
ሥራ 17:30ኤፌ 4:17, 18
ሥራ 17:31መዝ 96:13፤ 98:9፤ ዮሐ 5:22፤ ሥራ 10:42
ሥራ 17:31ዮሐ 11:25፤ ሥራ 2:24፤ 13:32, 33
ሥራ 17:321ቆሮ 1:23
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 17:1-34

የሐዋርያት ሥራ

17 ከዚያም በአምፊጶሊስና በአጶሎንያ በኩል ተጉዘው የአይሁዳውያን ምኩራብ ወዳለበት ወደ ተሰሎንቄ መጡ።+ 2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ+ ወደ ምኩራብ ገባ፤ ለሦስት ሰንበትም ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ፤+ 3 ክርስቶስ መከራ መቀበሉና+ ከሞት መነሳቱ+ አስፈላጊ እንደነበር ማስረጃ እየጠቀሰ በማብራራትና በማስረዳት “ይህ እኔ የማውጅላችሁ ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ ነው” አላቸው። 4 ከዚህም የተነሳ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ አማኞች በመሆን ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤+ ከግሪካውያንም መካከል አምላክን የሚያመልኩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የታወቁ ሴቶች እንዲሁ አደረጉ።

5 ሆኖም አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው+ በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ። 6 ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ “ዓለምን ሁሉ ያናወጡት* እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤+ 7 ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።”+ 8 ሕዝቡና የከተማዋ ገዢዎች ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ፤ 9 ያሶንን እና ሌሎቹን የዋስትና ገንዘብ እንዲያስይዙ ካደረጓቸው በኋላ* ለቀቋቸው።

10 ወንድሞችም እንደመሸ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤርያ ላኳቸው። እነሱም እዚያ እንደደረሱ ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ። 11 በቤርያ የነበሩት አይሁዳውያን በተሰሎንቄ ከነበሩት ይልቅ ቀና አስተሳሰብ ስለነበራቸው የሰሙት ነገር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በየዕለቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጉጉት ተቀበሉ። 12 ስለዚህ ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የተከበሩ ግሪካውያን ሴቶችና የተወሰኑ ወንዶች አማኞች ሆኑ። 13 ሆኖም በተሰሎንቄ ያሉት አይሁዳውያን ጳውሎስ የአምላክን ቃል በቤርያም እንዳወጀ ባወቁ ጊዜ ሕዝቡን ለማነሳሳትና ለማወክ ወደዚያ መጡ።+ 14 በዚህ ጊዜ ወንድሞች ወዲያውኑ ጳውሎስን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ላኩት፤+ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቀሩ። 15 ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴንስ አደረሱት፤ ከዚያም ጳውሎስ ‘ሲላስና ጢሞቴዎስ+ በተቻለ ፍጥነት ወደ እኔ እንዲመጡ ንገሯቸው’ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤ ሰዎቹም ተመልሰው ሄዱ።

16 ጳውሎስ በአቴንስ እየጠበቃቸው ሳለ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆኗን አይቶ መንፈሱ ተረበሸ። 17 ስለዚህ በምኩራብ ከአይሁዳውያንና አምላክን ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎች ጋር እንዲሁም በየዕለቱ በገበያ ስፍራ* ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይወያይ ጀመር። 18 ሆኖም ከኤፊቆሮስና ከኢስጦይክ ፈላስፎች መካከል አንዳንዶቹ ይከራከሩት ጀመር፤ ሌሎቹ ደግሞ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊያወራ ፈልጎ ነው?” ይሉ ነበር። “ስለ ባዕዳን አማልክት የሚያውጅ ይመስላል” የሚሉም ነበሩ። ይህን ያሉት ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤ የሚገልጸውን ምሥራች ያውጅ ስለነበር ነው።+ 19 ስለዚህ ይዘው ወደ አርዮስፋጎስ* ከወሰዱት በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ ልታስረዳን ትችላለህ? 20 ምክንያቱም ለጆሯችን እንግዳ የሆነ ነገር እያሰማኸን ነው፤ ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን።” 21 የአቴንስ ሰዎችና በዚያ የሚገኙ* የባዕድ አገር ሰዎች ትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ስለ አዳዲስ ነገሮች በማውራትና በመስማት ብቻ ነበር። 22 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ+ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦

“የአቴንስ ሰዎች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ እናንተ አማልክትን እንደምትፈሩ* ማየት ችያለሁ።+ 23 ለአብነት ያህል፣ እየተዘዋወርኩ ሳለሁ የምታመልኳቸውን ነገሮች በትኩረት ስመለከት ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። ስለዚህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ አሳውቃችኋለሁ። 24 ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ+ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም፤+ 25 በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው+ እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም።+ 26 በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም+ የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤+ የተወሰኑትን ዘመናትና የሰው ልጆች የሚኖሩበትንም ድንበር ደነገገ፤+ 27 ይህን ያደረገው ሰዎች አምላክን እንዲፈልጉትና አጥብቀው በመሻት እንዲያገኙት ብሎ ነው፤+ እንዲህ ሲባል ግን እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ ነው ማለት አይደለም። 28 ምክንያቱም ከእናንተ ባለቅኔዎች አንዳንዶቹ ‘እኛም የእሱ ልጆች ነንና’ ብለው እንደተናገሩት ሁሉ ሕይወት ያገኘነው፣ የምንንቀሳቀሰውና የምንኖረው በእሱ ነው።

29 “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች+ ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።+ 30 እርግጥ አምላክ ሰዎች ባለማወቅ የኖሩበትን ጊዜ+ ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ እያሳሰበ ነው። 31 ምክንያቱም በሾመው ሰው አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ+ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እሱንም ከሞት በማስነሳት ለሰዎች ሁሉ ዋስትና ሰጥቷል።”+

32 እነሱም ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ አንዳንዶቹ ያሾፉበት ጀመር፤+ ሌሎቹ ግን “ስለዚሁ ጉዳይ በድጋሚ መስማት እንፈልጋለን” አሉት። 33 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ትቷቸው ሄደ፤ 34 አንዳንድ ሰዎች ግን ከእሱ ጋር በመተባበር አማኞች ሆኑ። ከእነሱም መካከል የአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነው ዲዮናስዮስና ደማሪስ የተባለች ሴት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ይገኙበታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ