የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው” (1-6)

      • ማሰናከያ (7-11)

      • የጠፋው በግ ምሳሌ (12-14)

      • “ወንድምህን ታተርፋለህ” (15-20)

      • ይቅር ያላለው ባሪያ ምሳሌ (21-35)

ማቴዎስ 18:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 9:33-37፤ ሉቃስ 9:46-48፤ 22:24

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2021፣ ገጽ 21

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 148

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2007፣ ገጽ 8

ማቴዎስ 18:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ካልተለወጣችሁና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 19:14፤ 1ጴጥ 2:2
  • +ሉቃስ 18:17

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2021፣ ገጽ 21

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 148-149

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2007፣ ገጽ 8-9

    10/15/2005፣ ገጽ 28

    አስተማሪ፣ ገጽ 12

ማቴዎስ 18:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 15:33፤ ማቴ 20:26፤ 23:12፤ ሉቃስ 9:48፤ 14:11፤ 22:26፤ ያዕ 4:10፤ 1ጴጥ 5:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 148-149

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2007፣ ገጽ 8-9

    10/15/2005፣ ገጽ 28

    አስተማሪ፣ ገጽ 12

ማቴዎስ 18:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በአህያ የሚዞር የወፍጮ ድንጋይ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 9:42፤ ሉቃስ 17:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    2/2018፣ ገጽ 8

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2015፣ ገጽ 8

ማቴዎስ 18:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    2/2018፣ ገጽ 8

ማቴዎስ 18:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 3:5
  • +ማቴ 25:41፤ ማር 9:43-48

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    2/2018፣ ገጽ 8

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 150

ማቴዎስ 18:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:22, 29፤ ማር 9:47፤ ሮም 8:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    2/2018፣ ገጽ 8

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 150

ማቴዎስ 18:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 1:19፤ ዕብ 1:7, 14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣

    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)፣

    ቁጥር 5 2017፣ ገጽ 5

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2015፣ ገጽ 8

    11/1/2010፣ ገጽ 16

    “የሰላሙ መስፍን“፣ ገጽ 186

ማቴዎስ 18:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ3ን ተመልከት።

ማቴዎስ 18:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 2:25
  • +ሉቃስ 15:3-7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2020፣ ገጽ 19-20

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/2008፣ ገጽ 10

ማቴዎስ 18:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “አባታችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጴጥ 3:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/15/2015፣ ገጽ 8

    2/1/2008፣ ገጽ 10

ማቴዎስ 18:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ውቀሰው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:17፤ ምሳሌ 25:8, 9፤ ሉቃስ 17:3
  • +ያዕ 5:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የተደራጀ ሕዝብ፣ ገጽ 146-147

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2016፣ ገጽ 18

    5/2016፣ ገጽ 6-7

    ንቁ!፣

    3/2012፣ ገጽ 10-11

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1999፣ ገጽ 17-20

    7/15/1994፣ ገጽ 22-23

    9/1/1991፣ ገጽ 22-23

ማቴዎስ 18:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በሁለት ወይም በሦስት ምሥክሮች አፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 19:15፤ 2ቆሮ 13:1፤ 1ጢሞ 5:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የተደራጀ ሕዝብ፣ ገጽ 146-147

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    5/2016፣ ገጽ 6-7

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1999፣ ገጽ 20-21

    7/15/1994፣ ገጽ 22-23

ማቴዎስ 18:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 18:28፤ ሥራ 10:28፤ 11:2, 3
  • +ሮም 16:17፤ 1ቆሮ 5:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የተደራጀ ሕዝብ፣ ገጽ 146, 147-148

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    5/2016፣ ገጽ 6-7

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 151

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2007፣ ገጽ 27

    10/15/1999፣ ገጽ 19, 21-22

    7/15/1994፣ ገጽ 22-23

    4/15/1991፣ ገጽ 20

ማቴዎስ 18:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 151

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/1996፣ ገጽ 29

    3/15/1991፣ ገጽ 5

ማቴዎስ 18:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 11:24፤ ዮሐ 14:13፤ 16:23, 24፤ 1ዮሐ 3:22፤ 5:14

ማቴዎስ 18:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 5:4, 5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 151

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/2006፣ ገጽ 28

    3/1/1998፣ ገጽ 14

ማቴዎስ 18:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 152

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 196-198

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 21

    12/1/1997፣ ገጽ 15

    10/15/1994፣ ገጽ 25-26

ማቴዎስ 18:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “70 ጊዜ 7።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:12፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:4፤ ኤፌ 4:32፤ ቆላ 3:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 152

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 196-198

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2010፣ ገጽ 21

    12/1/1997፣ ገጽ 15, 20

    10/15/1994፣ ገጽ 25-26

    5/15/1991፣ ገጽ 16

ማቴዎስ 18:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    10,000 የብር ታላንት ከ60,000,000 ዲናር ጋር እኩል ነው። ለ14ን ተመልከት።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ገጽ 1731

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1994፣ ገጽ 25

ማቴዎስ 18:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 21:7፤ ዘሌ 25:39፤ 2ነገ 4:1፤ ነህ 5:8

ማቴዎስ 18:26

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጅ በመንሳት።”

ማቴዎስ 18:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዮሐ 1:9

ማቴዎስ 18:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለ14ን ተመልከት።

ማቴዎስ 18:33

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 55:7፤ ማቴ 6:12፤ 7:12፤ ያዕ 2:13

ማቴዎስ 18:34

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 76

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/1/2008፣ ገጽ 22

ማቴዎስ 18:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:14፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:3፤ ኤፌ 4:32
  • +ሮም 2:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 153

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 18:1ማር 9:33-37፤ ሉቃስ 9:46-48፤ 22:24
ማቴ. 18:3ማቴ 19:14፤ 1ጴጥ 2:2
ማቴ. 18:3ሉቃስ 18:17
ማቴ. 18:4ምሳሌ 15:33፤ ማቴ 20:26፤ 23:12፤ ሉቃስ 9:48፤ 14:11፤ 22:26፤ ያዕ 4:10፤ 1ጴጥ 5:5
ማቴ. 18:6ማር 9:42፤ ሉቃስ 17:1, 2
ማቴ. 18:8ቆላ 3:5
ማቴ. 18:8ማቴ 25:41፤ ማር 9:43-48
ማቴ. 18:9ማቴ 5:22, 29፤ ማር 9:47፤ ሮም 8:13
ማቴ. 18:10ሉቃስ 1:19፤ ዕብ 1:7, 14
ማቴ. 18:121ጴጥ 2:25
ማቴ. 18:12ሉቃስ 15:3-7
ማቴ. 18:142ጴጥ 3:9
ማቴ. 18:15ዘሌ 19:17፤ ምሳሌ 25:8, 9፤ ሉቃስ 17:3
ማቴ. 18:15ያዕ 5:20
ማቴ. 18:16ዘዳ 19:15፤ 2ቆሮ 13:1፤ 1ጢሞ 5:19
ማቴ. 18:17ዮሐ 18:28፤ ሥራ 10:28፤ 11:2, 3
ማቴ. 18:17ሮም 16:17፤ 1ቆሮ 5:11
ማቴ. 18:19ማር 11:24፤ ዮሐ 14:13፤ 16:23, 24፤ 1ዮሐ 3:22፤ 5:14
ማቴ. 18:201ቆሮ 5:4, 5
ማቴ. 18:22ማቴ 6:12፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:4፤ ኤፌ 4:32፤ ቆላ 3:13
ማቴ. 18:25ዘፀ 21:7፤ ዘሌ 25:39፤ 2ነገ 4:1፤ ነህ 5:8
ማቴ. 18:271ዮሐ 1:9
ማቴ. 18:33ኢሳ 55:7፤ ማቴ 6:12፤ 7:12፤ ያዕ 2:13
ማቴ. 18:35ማቴ 6:14፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:3፤ ኤፌ 4:32
ማቴ. 18:35ሮም 2:6
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 18:1-35

የማቴዎስ ወንጌል

18 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው ማን ነው?” አሉት።+ 2 ኢየሱስም አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው በማቆም 3 እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ካልተመለሳችሁና* እንደ ልጆች ካልሆናችሁ+ በምንም ዓይነት ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም።+ 4 ስለዚህ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጠው እንደዚህ ትንሽ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ነው፤+ 5 እንዲሁም እንደዚህ ያለውን ትንሽ ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል። 6 ሆኖም በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከትናንሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ የወፍጮ ድንጋይ* በአንገቱ ታስሮ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ቢሰጥም ይሻለዋል።+

7 “ይህ ዓለም ሰዎችን የሚያሰናክል ነገር ስለሚያስቀምጥ ወዮለት! እርግጥ ማሰናከያ መምጣቱ የማይቀር ነው፤ ነገር ግን በእሱ ጠንቅ ሌሎች እንዲሰናከሉ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት! 8 እንግዲያው እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው።+ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለማዊ እሳት+ ከምትወረወር ጉንድሽ ወይም አንካሳ ሆነህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል። 9 እንዲሁም ዓይንህ ቢያሰናክልህ አውጥተህ ጣለው። ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ እሳታማ ገሃነም* ከምትወረወር አንድ ዓይን ኖሮህ ሕይወት ብታገኝ ይሻልሃል።+ 10 በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው በሰማይ ባለው አባቴ ፊት ዘወትር ስለሚቀርቡ ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ።+ 11 *——

12 “ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው 100 በጎች ቢኖሩትና ከእነሱ አንዷ ብትጠፋ+ 99ኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋችውን ለመፈለግ አይሄድም?+ 13 እውነት እላችኋለሁ፣ የጠፋችውን በግ ካገኛት፣ ካልጠፉት ከ99ኙ ይልቅ በእሷ ይበልጥ ይደሰታል። 14 በተመሳሳይም በሰማይ ያለው አባቴ* ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱም እንኳ እንዲጠፋ አይፈልግም።+

15 “በተጨማሪም ወንድምህ ቢበድልህ አንተና እሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ጥፋቱን በግልጽ ንገረው።*+ ከሰማህ ወንድምህን ታተርፋለህ።+ 16 የማይሰማህ ከሆነ ግን ማንኛውም ጉዳይ ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል* ስለሚጸና አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ ሂድ።+ 17 እነሱንም ካልሰማ ለጉባኤ ተናገር። ጉባኤውንም እንኳ የማይሰማ ከሆነ እንደ አሕዛብና+ እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ+ አድርገህ ቁጠረው።

18 “እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ እንዲሁም በምድር የምትፈቱት ነገር ሁሉ ቀድሞውኑ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። 19 ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር ላይ ከእናንተ መካከል ሁለታችሁ አንድ አስፈላጊ የሆነ ነገር ለመለመን ብትስማሙ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል።+ 20 ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት+ በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና።”

21 ከዚያም ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ “ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ይቅር ልበለው?” አለው። 22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እስከ 77 ጊዜ* እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ ብቻ አልልህም።+

23 “ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከባሪያዎቹ ጋር ሒሳብ መተሳሰብ ከፈለገ አንድ ንጉሥ ጋር ይመሳሰላል። 24 ሒሳቡን መተሳሰብ በጀመረ ጊዜም 10,000 ታላንት* ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው አቀረቡለት። 25 ሆኖም ሰውየው ዕዳውን የሚከፍልበት ምንም መንገድ ስላልነበረው ጌታው እሱም ሆነ ሚስቱ እንዲሁም ልጆቹና ያለው ንብረት ሁሉ ተሸጠው ዕዳው እንዲከፈል አዘዘ።+ 26 ባሪያውም ወድቆ በመስገድ* ‘ጌታዬ ሆይ፣ እባክህ ታገሠኝ፤ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው። 27 ጌታውም እጅግ አዘነለትና ለቀቀው፤ ዕዳውንም ሰረዘለት።+ 28 ሆኖም ይህ ባሪያ ወጥቶ ከሄደ በኋላ 100 ዲናር* ያበደረውን እንደ እሱ ያለ ባሪያ አግኝቶ ያዘውና አንገቱን አንቆ ‘ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ’ አለው። 29 ባልንጀራው የሆነው ያ ባሪያም እግሩ ላይ ወድቆ ‘ወንድሜ ሆይ፣ እባክህ ታገሠኝ፤ እከፍልሃለሁ’ ብሎ ይለምነው ጀመር። 30 እሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ሄዶ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍል ድረስ ወህኒ ቤት አሳሰረው። 31 ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሪያዎች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ነገር ሁሉ ለጌታቸው ነገሩት። 32 በዚህ ጊዜ ጌታው አስጠራውና እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፣ ስለተማጸንከኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውኩልህ። 33 ታዲያ እኔ ምሕረት እንዳደረግኩልህ ሁሉ አንተስ ባልንጀራህ ለሆነው ባሪያ ምሕረት ልታደርግለት አይገባም ነበር?’+ 34 ጌታውም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ያለበትን ዕዳ ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለወህኒ ቤት ጠባቂዎቹ አሳልፎ ሰጠው። 35 እናንተም እያንዳንዳችሁ ወንድማችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ+ በሰማይ ያለው አባቴ እንደዚሁ ያደርግባችኋል።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ