የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 40
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለአምላክ ሕዝብ የተሰጠ ማጽናኛ (1-11)

        • በምድረ በዳ የተሰማ ድምፅ (3-5)

      • የአምላክ ታላቅነት (12-31)

        • “ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው” (15)

        • ‘አምላክ ክብ ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል’ (22)

        • ከዋክብትን ሁሉ በየስማቸው ይጠራቸዋል (26)

        • አምላክ ፈጽሞ አይደክምም (28)

        • ይሖዋን ተስፋ ማድረግ ኃይል ያድሳል (29-31)

ኢሳይያስ 40:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:13፤ 51:3፤ 2ቆሮ 1:3, 4

ኢሳይያስ 40:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ኢየሩሳሌምን በሚያጽናና ቃል አናግሯት።”

  • *

    ወይም “እጥፍ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 79:8, 9፤ ኤር 31:34፤ 33:8
  • +ኤር 16:18፤ ዳን 9:11, 12

ኢሳይያስ 40:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አዘጋጁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 35:8፤ 57:14፤ ሚል 3:1
  • +ኢሳ 11:16
  • +ማቴ 3:1, 3፤ ማር 1:2-4፤ ሉቃስ 3:3-6፤ ዮሐ 1:23

ኢሳይያስ 40:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 42:16

ኢሳይያስ 40:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰዎችም ሁሉ በአንድነት ያዩታል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 24:15
  • +ኢሳ 49:6፤ 52:10

ኢሳይያስ 40:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሰው ሁሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 14:1, 2፤ መዝ 90:5, 6

ኢሳይያስ 40:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መንፈስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ያዕ 1:11
  • +መዝ 103:15, 16

ኢሳይያስ 40:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 46:10፤ 1ጴጥ 1:24, 25

ኢሳይያስ 40:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 52:7
  • +ኢሳ 12:2፤ 25:9

ኢሳይያስ 40:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 53:1፤ ዮሐ 12:37, 38
  • +ኢሳ 62:11፤ ራእይ 22:12

ኢሳይያስ 40:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:10፤ ሕዝ 34:15, 16፤ 1ጴጥ 2:25
  • +ዘፍ 33:13፤ 1ጴጥ 5:2, 3

ኢሳይያስ 40:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ጣቶች ሲዘረጉ ከአውራ ጣት ጫፍ እስከ ትንሿ ጣት ጫፍ ድረስ ያለውን ርዝመት ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 30:4
  • +ኢዮብ 38:4, 5

ኢሳይያስ 40:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የተረዳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 36:22, 23፤ ሮም 11:34፤ 1ቆሮ 2:16

ኢሳይያስ 40:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 147:5

ኢሳይያስ 40:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 62:9

ኢሳይያስ 40:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሊባኖስ እንኳ በቂ ማገዶ ማቅረብ አትችልም።”

ኢሳይያስ 40:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዳን 4:35
  • +ኢሳ 41:11, 12

ኢሳይያስ 40:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 8:10፤ መዝ 86:8፤ ኤር 10:6, 7
  • +ዘዳ 4:15, 16፤ ሥራ 17:29

ኢሳይያስ 40:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 115:4-8

ኢሳይያስ 40:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 44:14, 15
  • +ኢሳ 41:7፤ 46:6, 7፤ ኤር 10:3, 4

ኢሳይያስ 40:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 19:1፤ ሮም 1:20

ኢሳይያስ 40:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ድቡልቡል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 66:1
  • +ኢሳ 44:24፤ ኤር 10:12፤ ዘካ 12:1

ኢሳይያስ 40:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ገዢዎችንም።”

ኢሳይያስ 40:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 21:20, 21፤ 2ነገ 10:10, 11፤ ኤር 22:24, 30

ኢሳይያስ 40:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 102:25
  • +መዝ 147:4
  • +መዝ 89:13

ኢሳይያስ 40:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 49:14፤ ሕዝ 37:11

ኢሳይያስ 40:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሊደረስበት አይችልም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 21:33፤ መዝ 90:2፤ ኤር 10:10፤ 1ጢሞ 1:17
  • +መዝ 121:4፤ ኢሳ 27:3
  • +መዝ 139:4, 6፤ 147:5፤ ኢሳ 55:9፤ ሮም 11:33፤ 1ቆሮ 2:16

ኢሳይያስ 40:29

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ብርቱ ጉልበት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 29:11፤ ኢሳ 40:26፤ ፊልጵ 4:13፤ ዕብ 11:33, 34

ኢሳይያስ 40:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 103:5
  • +1ነገ 18:46፤ መዝ 84:7

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 40:1ኢሳ 49:13፤ 51:3፤ 2ቆሮ 1:3, 4
ኢሳ. 40:2መዝ 79:8, 9፤ ኤር 31:34፤ 33:8
ኢሳ. 40:2ኤር 16:18፤ ዳን 9:11, 12
ኢሳ. 40:3ኢሳ 35:8፤ 57:14፤ ሚል 3:1
ኢሳ. 40:3ኢሳ 11:16
ኢሳ. 40:3ማቴ 3:1, 3፤ ማር 1:2-4፤ ሉቃስ 3:3-6፤ ዮሐ 1:23
ኢሳ. 40:4ኢሳ 42:16
ኢሳ. 40:5ኢሳ 24:15
ኢሳ. 40:5ኢሳ 49:6፤ 52:10
ኢሳ. 40:6ኢዮብ 14:1, 2፤ መዝ 90:5, 6
ኢሳ. 40:7ያዕ 1:11
ኢሳ. 40:7መዝ 103:15, 16
ኢሳ. 40:8ኢሳ 46:10፤ 1ጴጥ 1:24, 25
ኢሳ. 40:9ኢሳ 52:7
ኢሳ. 40:9ኢሳ 12:2፤ 25:9
ኢሳ. 40:10ኢሳ 53:1፤ ዮሐ 12:37, 38
ኢሳ. 40:10ኢሳ 62:11፤ ራእይ 22:12
ኢሳ. 40:11ኢሳ 49:10፤ ሕዝ 34:15, 16፤ 1ጴጥ 2:25
ኢሳ. 40:11ዘፍ 33:13፤ 1ጴጥ 5:2, 3
ኢሳ. 40:12ምሳሌ 30:4
ኢሳ. 40:12ኢዮብ 38:4, 5
ኢሳ. 40:13ኢዮብ 36:22, 23፤ ሮም 11:34፤ 1ቆሮ 2:16
ኢሳ. 40:14መዝ 147:5
ኢሳ. 40:15መዝ 62:9
ኢሳ. 40:17ዳን 4:35
ኢሳ. 40:17ኢሳ 41:11, 12
ኢሳ. 40:18ዘፀ 8:10፤ መዝ 86:8፤ ኤር 10:6, 7
ኢሳ. 40:18ዘዳ 4:15, 16፤ ሥራ 17:29
ኢሳ. 40:19መዝ 115:4-8
ኢሳ. 40:20ኢሳ 44:14, 15
ኢሳ. 40:20ኢሳ 41:7፤ 46:6, 7፤ ኤር 10:3, 4
ኢሳ. 40:21መዝ 19:1፤ ሮም 1:20
ኢሳ. 40:22ኢሳ 66:1
ኢሳ. 40:22ኢሳ 44:24፤ ኤር 10:12፤ ዘካ 12:1
ኢሳ. 40:241ነገ 21:20, 21፤ 2ነገ 10:10, 11፤ ኤር 22:24, 30
ኢሳ. 40:26መዝ 102:25
ኢሳ. 40:26መዝ 147:4
ኢሳ. 40:26መዝ 89:13
ኢሳ. 40:27ኢሳ 49:14፤ ሕዝ 37:11
ኢሳ. 40:28ዘፍ 21:33፤ መዝ 90:2፤ ኤር 10:10፤ 1ጢሞ 1:17
ኢሳ. 40:28መዝ 121:4፤ ኢሳ 27:3
ኢሳ. 40:28መዝ 139:4, 6፤ 147:5፤ ኢሳ 55:9፤ ሮም 11:33፤ 1ቆሮ 2:16
ኢሳ. 40:29መዝ 29:11፤ ኢሳ 40:26፤ ፊልጵ 4:13፤ ዕብ 11:33, 34
ኢሳ. 40:31መዝ 103:5
ኢሳ. 40:311ነገ 18:46፤ መዝ 84:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 40:1-31

ኢሳይያስ

40 “አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ” ይላል አምላካችሁ።+

 2 “ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤*

የግዳጅ አገልግሎቷ እንዳበቃና

የበደሏ ዋጋ እንደተከፈለ ንገሯት።+

ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ከይሖዋ እጅ ሙሉ* ዋጋ ተቀብላለች።”+

 3 አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦

“የይሖዋን መንገድ ጥረጉ!*+

በበረሃ ለአምላካችን አውራ ጎዳናውን+ አቅኑ።+

 4 ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤

ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል።

ወጣ ገባውም መሬት ይስተካከል፤

ጎርበጥባጣውም ምድር ሸለቋማ ሜዳ ይሁን።+

 5 የይሖዋ ክብር ይገለጣል፤+

ሥጋም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤*+

የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።”

 6 አዳምጥ! አንድ ሰው “ጮክ ብለህ ተናገር!” አለ።

ሌላውም “ምን ብዬ ልናገር?” አለ።

“ሥጋ ሁሉ* ለምለም ሣር ነው።

ታማኝ ፍቅሩ ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።+

 7 ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤

አበባው ይጠወልጋል፤+

ምክንያቱም የይሖዋ እስትንፋስ* ይነፍስበታል።+

ሕዝቡ በእርግጥ ለምለም ሣር ነው።

 8 ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤

አበባው ይጠወልጋል፤

የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”+

 9 አንቺ ለጽዮን ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣+

ከፍ ወዳለ ተራራ ውጪ።

አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣

ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ።

ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ።

ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ።+

10 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በኃይል ይመጣል፤

ክንዱም ስለ እሱ ይገዛል።+

እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤

የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ።+

11 መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል።+

ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤

በእቅፉም ይሸከማቸዋል።

ግልገሎቻቸውን የሚያጠቡትን በቀስታ ይመራል።+

12 ውኃዎችን በእፍኙ የሰፈረ፣+

ሰማያትን በስንዝሩ* የለካ፣

የምድርን አፈር ሰብስቦ በመስፈሪያ የያዘ+

ወይም ተራሮችን በመለኪያ፣

ኮረብቶችንም በሚዛን የመዘነ ማን ነው?

13 የይሖዋን መንፈስ የለካ*

እንዲሁም አማካሪው ሆኖ ሊያስተምረው የሚችል ማን ነው?+

14 ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?

የፍትሕን መንገድ ያስተማረው

አሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?

ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+

15 እነሆ፣ ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤

በሚዛንም ላይ እንዳለ አቧራ ይቆጠራሉ።+

እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ደቃቅ አፈር ያነሳቸዋል።

16 እሳት መንደዱን እንዲቀጥል ለማድረግ የሊባኖስ ዛፎች እንኳ አይበቁም፤*

በውስጡም ያሉት የዱር እንስሳት የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በቂ አይደሉም።

17 ብሔራት ሁሉ በፊቱ የሌሉ ያህል ናቸው፤+

በእሱም ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩና ዋጋ ቢስ ናቸው።+

18 አምላክን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ?+

ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?+

19 የእጅ ጥበብ ባለሙያ ብረት አቅልጦ ጣዖት* ይሠራል፤

አንጥረኛውም በወርቅ ይለብጠዋል፤+

የብር ሰንሰለትም ይሠራለታል።

20 አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠት

የማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል።+

የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለት

በእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል።+

21 ይህን አታውቁም?

ደግሞስ አልሰማችሁም?

ከመጀመሪያ አንስቶስ አልተነገራችሁም?

የምድር መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ማስረጃስ አላስተዋላችሁም?+

22 እሱ ክብ* ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል፤+

በእሷም ላይ የሚኖሩት እንደ ፌንጣ ናቸው።

እሱ ሰማያትን እንደ ስስ ጨርቅ ይዘረጋል፤

እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይወጥራቸዋል።+

23 ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስወግዳል፤

የምድር ፈራጆችንም* እንዳልነበሩ ያደርጋል።

24 ገና እንደተተከለ፣

ገና እንደተዘራ፣

ግንዱም በአፈር ውስጥ ሥር እንዳልሰደደ ተክል ናቸው፤

ሲነፍስባቸውም ይደርቃሉ፤

ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+

25 “እኩያው እሆን ዘንድ ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱሱ።

26 “ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ።

እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው?+

እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤

ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+

ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና ከሚያስደምመው ኃይሉ+ የተነሳ

አንዳቸውም አይጎድሉም።

27 ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣

‘መንገዴ ከይሖዋ ተሰውሯል፤

ከአምላክ ፍትሕ አላገኝም’ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?+

28 ይህን አታውቅም? ደግሞስ አልሰማህም?

የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው።+

እሱ ፈጽሞ አይደክምም ወይም አይዝልም።+

ማስተዋሉ አይመረመርም።*+

29 ለደከመው ኃይል፣

ጉልበት ለሌላቸውም የተሟላ ብርታት* ይሰጣል።+

30 ወንዶች ልጆች ይደክማሉ፤ ደግሞም ይዝላሉ፤

ወጣቶችም ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤

31 ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ኃይላቸው ይታደሳል።

እንደ ንስር በክንፍ ወደ ላይ ይወጣሉ።+

ይሮጣሉ፣ አይዝሉም፤

ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ